Mittwoch, 11. März 2015

እባካችሁ ተርዱኝ



ምእራፍ----    አንድ

 
አንድ ነገር አለ ዛሬ ዛሬ ያመንኩበት፡፡ ምንአልባት እኔን እራሴ አስተሳሰቤ ገሎኝ አልፎ ሊሆን ይችላል፡፡ በጭራሽ አድርባይ ሆኘ አላውቅም፡፡ ግን አድርባይን የምፈራ ሴት ነበርኩ፡፡ አሁንም እደፍራቸዋለሁ ማለት አይደለም፡፡ አድርባይ በሰው አይምሮ ላይ የፈረደ ውሸታም አስመሳይ እና እበላ ባይ ነው፡፡ እባካችሁ ተረዱኝ፡፡ ይህንን ስላችሁ ሆነ ብዬ የኢሕአዴግ አልያም የተቃዋሚንም ደጋፊ ተብዬ አወናባጅ ሁሉ ለመምታት አይደለም፡፡ አድርባይ የትም ብትሄድ የትም አለ፡፡ በጥቃቅን ማሃበራት ውስጥ እራሱ ስንት አለ እንደውሻ የሚያነፈንፍ፡፡ አድርባይ አቁዋም የለለው እና አገር ወገን ዘመድ አዝማድን ሁሉ አማሽ ነው፡፡ አድርባይነት የህይወት ፍርሃት እና ዋስትና ማጣት ለስጋዊ  ኑሮ ሲባል ፤በእራስ መተማመን ማጣት የሚፈጠር የሰው ልጅ ባህሪ ነው፡፡ ታዲያ እኔ ልነግራችሁ የፈለኩት፤ እከሌ እንዲሕ እንዲያ ነው ብዬ ወደሶስተኛ ሰው ከማስተላልፍ የእራሴን የህይወት ልምድ ያስፈሩኝኝ እና ያስጨነቁኝን ያሳዘኑኝን በእራሴው በዚሁ በሚዲያዬ/ በፌስቡክ ድረገጼእና በብሎጌ በኩል ላጫውታችሁ ፈልኩ፡፡ እኔ መቸም ኢሳትንም ሆነ የነሚሚ ስባሀቱን ፋና ሚዲያ አገኝቼ እናንተ ጋር መገናኘት አልችልም፡፡ ለዚህ እራሴን ምርቻ ውስጥ አቅርቤ የተወዳደርኩ አይደለሁም፡፡ በወረቀትም፣ በገንዘብም፣ በእውቀትም፣ ደግሞም በአድርባይነትም  እኔ ስለማልታወቅ እንዚህ ሚዲያዎች ለእኔ በሩን አይከፍቱትም፡፡ ስለዚህ የእራሴን ማህበራዊ ሚዲያ ማዘጋጀቱ ወሳኝነት እንዳለሁ ተረድቻለሁ፡፡ ይህን ቴክኖሎጂ ያዘጋጁልን ባለአይምሮዎች ይባረኩ፡፡ ተንፍሶ መሞት እንዴት ጥሩ ነገር መሰላችሁ፡፡ ስለዚህ እንድተነፍስ ከአየር ጋር እንድገናኝ አጋዥ ሆነውኛልእና፡፡ አዎ አሁንም ይባረኩ፡፡
                   እንግዲህ የትኛው ምስክርነት ይደምቃል ካላችሁ ከእራስ ወደሁለተኛ ወገን የሚተላለፍ ብቻ ነው፡፡ አሉባልታም አይሆንም፡፡ ከዚያ ምን ትምህርት አገኛችሁ ብቻ ሳይሆን ሰውም የወደቀውን ባህሪውን በውስጡ እንዲያይ ለማድረግ ነው ጥረቴ፡፡ ግልጽነቴ ለእኔ  የተጎዳውን ውስጤን ለማከም የምጠቀምበት ዘዴዬ ነው፡፡ መጻፍ ይጠግናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ማንበብ ደግሞ የጨለመ አይምሮን ባትሪ ሆኖ የብርሃን ጭላጭል ያበጅለታል፡፡ አይምሮ ነው ወሳኙ፤ ለመጉዳትም ለመጎዳትም፡፡ የተጎዳውን ማንነታችንን ለመጠገን መጀመሪያ መጎዳታችን እንዴት እና ለምን እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ ብዙ ግዜ ጠላትህ ጋር ሽማግሌ ያስታርቀሃል፡፡ የባህል አፋኝነት ሸንጋይነት እዚህ ላይ ነው፡፡ ግን ጠላትህ የሰበረው ማንነት ሽማግሌው ከአንተ ውስጥ ሊያወጣው ችሎታ የለውም፡፡ እንዳውም የሚያደርግህ በውስጥህ በደልን አምቀሕ እንድትኖር ነው፡፡ እሱ በውነት ምላች እንዳስቀመጥቅ አይነት ነገር ነው፡፡ ማንኛውም በደል መሰራት ያለበት ነገር እንጂ የምታስቀምተው መሆን አይገባም፡፡ ስለዚህ ውስጥህን እያደቀቀ ስነልቦናህን ጨርግዶ ይበላሃል፡፡ ይቅር የምትለው እኮ፤ ጠላትህ እውነትም ተሰምቶት ይቅርታ አድርግልኝ ብሎ ሲሰማው ሲጸጽተው ነው፡፡ ሽማግሌ ግን የሚያስተርቅህ ከሰውዬው ስለመጣ ሳይሆን እነሱ መልካም ነው ብለው ስላሰቡ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በኢትዮጲያ ያልተጎዳ ሰው አለ ብዬ ለመገመት ያዳግተኛል፡፡ ይህን ልል ያልኩበት ምክናያት በቃ እንደባህል ማንም ተነስቶ የፈለገውን የሚያደርግብህ እና ምንም አይነት የመጎዳት ስሜት ሊረዳ የማይችል ብዙ ስላየሁ ነው፡፡
ምንአልባት እኔም ያጠፋሁት ጥፋት ሊኖር ይችላል፡፡ ግን ያ የሆነው መጎዳትን ምን ያህል ስብርብር እንደሚያደርግ ባልተረዳሁበት ወቅት ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ ብዙ ነገሮች አሉ ባለማወቅ ጤነኛ የሚመስሉን፤ ግን ጤነኞች እኮ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ ባዩሽ እንዲህ እንዲህ ናት ቢሉዋችሁ፤ አይቶኝም ሰምቶኝም የማያውቀው አምኖ ተቀብሎ እሱም ለሌላ ያስተላልፋል፡፡ ይህ ያየሁት እና የተለማመድኩት ስለሆነ ደብቄ ወይም በብሄራዊ ስሜት አፍኘ ላልፈው የሚገባኝ አይደለሁም፡፡ „አትፍረድ“ የሚለውን እንኩዋን  ያነበብነውን መተግበር አንችልም፡፡ ይህ አይነት ባህሪ በቤተክርስቲያን ምእመናንም ሆነ በፖለቲካው አለም አቀንቃኞች ያየሁት ነው፡፡ በቃ በቀላሉ ከጭዋታ ውጭ ትደረጋለሕ፡፡ ለምን ያሰው ያቺ ሴት ይህንን አወራችባት ይህንን አወሩበት ብሎ የሚጠይቅ እና የእራሱን ግንዛቢ ሊጠቀም የሚችል እጅግም አላየሁም፡፡
በልጅነቴ ኢትዮጲያን የለቀቁት ሴት፤ ከወጣሁበት ግዜ እና ከሌላው አለም ህብረተሰብ ጋር የተቀላቀልኩበት ግዜ ጀምሬ ፤ይቅርታ እና ምስጋና በቀን ስንት ግዜ እየተናገርናቸው እንደምንውል የማይለዩን ዘመናዊ እና የሰለጠኑ ቃላቶች መሆናቸውን ተምሬአለሁ፡፡ በሚሊዮን ግዜ በላይ እነዚህን ቃላቶች እንደሌላው የሰለጠነ ህዝብ እስከአሁን እጠቀምባቸዋለሁ፡፡ እንዳውም በዘመኔ በፍቅር የማወጣው ቃል ቢኖር፤ ይቅርታ መጠየቅ እና ማመስገን ናቸው፡፡ ብርጭቆም ልጆቼ አንስተው ቢሰጡኝ፤ ውሃ ቢያጠጡኝ አመሰግናለሁ ካላልኩ ይታዘቡኛል፡፡ ከትዝብቱ በፊት ግን ማውጣት እንዴት አይነት መከበርን እንደሚያስገኝ አውቀዋለሁ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ቃላቶች ማንም ጤነኛ አይምሮ ያለው ሰው ሊላመደው ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ እናት ነኝ እና ሁልግዜ ለልጆቼ ምግብ ሰርቼ ስሰጥ“ አመሰግናለሁ ማዘር“ የሚሉኝ ምላሽ በውነቱ መማርስ ይህንን ያሰኛል፡፡ በቃ ስሜትን ማስደሰት እና ማሳዘን የሚቻል ነገር መሆኑን ገና ከሕጻንነት መማር እንዴት ደስ ይላል፡፡ እናትነትም ግዳጅ አይደለም እኮ፡፡ እናትነትም ስሜት አለው፡፡ የስሜት መግለጫውም ማንም ሰው ይቅርታ መጠየቅ እና መመስገን የሚፈልግበት ስሜት አለው፡፡ ካልሆነ እየበደለህ እንደባህል ነውሩን እየሸፈንክለት፤ አድም ሲልህ አብረህ እያደምክ፡፡ የወዳጅህን ነውር እያወደስክ እነዴት ይለመዳል፡፡ በውነቱ ይህ አስፈርቶኛል በኢትዮጲያ፡፡
 ይቅርታ እና ምስጋና  በኢትዮጲያ ውስጥ የተለመዱ አይደሉም፡፡ እንዳውም የሚገርመኝ ልኩዋን ነገረቻት ብለው በመጥፎ ደፋር ቃላት ተናገሪ ሲያወኩ ሲስቁ አይ ነበር፡፡ ከአፉ የደፈረ የሰፈር ጀግን ብዙ አፍርተናል፡፡  ስለዚህ የምንጎዳዳውን እያደገ እያደገ የገዛ ንብረትህንም ተዘርፈህ አጥተህ የምትሸሽበት እላይ ጣራ ዘለል ጉዳቶች በሽ ነው፡፡ እኛው እራሳችን በማዳነቅ መጥፎ ባህልን ይለፍ ሰጥተናል እና፡፡  በዚህ የተነሳ ከብዙው በጥቂቱ ጎድተውኛል የምላቸውን ነገሮች አልፎ አልፎ እራሴን ግልጽ በማድረግ ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡ ዛሬ የማጫውታችሁ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተከወነውን ነው፡፡ ቀጣዩን በክፍል 2 ተከታተሉ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen