አንድ ለአምስት በውስጣችን የሚኖር እንጂ ኢሕአዴግ የመሰረተው አይደለም
ከግሩፕ መሽከርከር ያልወጣ አይምሮ በማህበራዊ ሚዲያ የሚደረገው ልውውጥ የአስተሳሰብ ለውጥ ያመ›ጣል ብሎ መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ እንዳውም ተስፋ አስቆራጭ የሆነ ተጽእና እንዳያመጣ ልብ ማድረግ እራሴ
አለብኝ፡፡ ከፌስ ቡክ ሚዲያ ያተረፍኩትን እና የተጎዳሁትን ለማመዛዘን፡፡ እራሴን መመርመር አለብኝ፡፡ ሁሉም የቴክኖሎጂ ጥቅም ይዞ የሚሄደው የአካባቢውን የአስተሳሰብ እድገት መሰረት በማድረግ እንጂ፤ የሚዲያውን አገልግሎት ከመረዳት አይደለም፡፡ ፌስቡኩን የምጠቀምበት፤ ከእራሴ አስተሳሰብ ጋር ብቻ የሚሄደውን ሰው ለመገናኘት ከሆነ ፌስ ቡክ ለአገራችን ከሚያመጣው እድገት ይልቅ እንቅፋትነቱ ሊጎላ ይችላል፡፡ ማመዛዘን እና ለምን እና እንዴት የሚሉ ጥያቄዎችን ጠይቆ እራስን ለለውጥ ለማዘጋጀት፤ በእኛነታችን ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ለውጥ የዘጋነው ወይም ያላስተዋልነው ይመስላል፡፡
የፌስቡክ ሚዲያ የተናጠል አስተሳሰብን መጀመሪያ ብንስተናገድበት ጀኔራል የሆነውን ችግራችንን ሊገልጽልን አልያም ሊያስታውሰን ይችል ነበር፡፤ አሁን ግን እንደማየው እኔ ማንነትን ሳይሆን እኛነታችንን ያንኑ ጀኔራል ማድረግ እና የማጆሪቲ የምንለውን ነገር ይዘን መጉዋዝ ብቻ ነው፡፡ ለምን እና እንዴት የሚለውን ነገር እራሰችንን ለመጠየቅ እንኩዋን የአፍታ ያህል ምንም አይነት መሪት ሊሆነን አልቻለም፡፡ ይህም ጉዳይ አንተ እኔ ነኝ አንተ እኔ ነሕ እንጂ፤ ማንንም ሰው ወደልዩነት ንግግር ሊያመጣ ሊያወያይ አይችልም፡፡ አስተሳሰቤን የሆነ ነገር ትንሽ ሊያነቃንቀው ሊያፋጨው የሚችል ነገር የኢትዮጲያ ማህበራዊ ሚዲያ ሊፈጥር አይችልም፡፡ ልክ ፖለቲካውም እንደእምነት የሚሄድበት ሁኔታ፤ ነሕ ወይም አይደለህም አይነት ነገር ነው፡፡ መቀበል አለመቀበል ብቻ ነው ያለው ጉዳይ፡፡ በ ዚህም ሁኔታ ፌስቡክን እንደኢትዮጲያ ማህበራዊ ሚዲያ ለመጠቀም ምን ጠቀመኝ የሚለውን ነገር ሳየው፤ እንዳውም የለለኝን ሹመት የሚያከናንብ በፍርድ የሚያስጠምድ ወይ ውርደት
የሚያመጣ የፍርድ መሳሪያ እንጂ የሰውን እውነተኛ አስተሳሰብ ሊያሳይ የሚችል አይደለም፡፡ ሰው አንድ ነገር ተብሎ ከተፈረጀ፤ ያንኑ ሳየወድ በግድ የማንጸባረቅ ባህሪ በውስጡ ሊገነባ ይችላል፡፡ በፌስ ቡክ፤ ወይ ተቃዋሚ ነሕ አልያም የገዢው ፓርቲ ነሕ፡፡ እንግዲሕ ይህን የሚያስወስን ንግግር ወይም ውይይት የሚጋብዝ ሳይሆን የሚዘጋ እና ነኝ አይደለሁም ብሎ ሰው አንድ ጥግ ይዞ የሚቀመጥበት ብቻ ነው፡፡
ይህን ሳይገሉ ጎፈሬ የሚያሰኝ ነገር፤ ሁላችንም አስተሳሰባችንን የምንመረምርበት እና ከጊዜው እድገት ጋር ልናስኬደው ቀርቶ የደረስንበትን እንኩዋን እድገት እንድንንደው ያደረገን እውነታ መሰረቱ ይህ ከጥቃቅን ግሩፕ እና ማህበር መደራጀት ጉዳይ አለመውታታችን ነው፡፡ ሁሉም የሚያከብረው የእኔ የሚለውን ብቻ ነው፡፡ በእምነትም ብንሄድ በፖለቲካም ብንሄድ በዘርም ብንሄድ ሰው የእኔ ብሎ የሚያምንበትን ብቻ እንዳይነካበት መከላከል አልያም የተለዬ አዋቂ አድርጎ በማቅረብ ሁሉም በእየራሱ ግሩፕ ብሎ በፈጠረው ነገር ምሽግ ሲሰራ እና ሲደበቅ እናያለን፡፡ እውን ግን ሁላችንም ዲሞክራሲን እንፈልገዋለን ወይ ብሎ እራስን ለመጠየቅ ተቸግረናል፡፡ ስለዚህ እውን እኔ አስተሳሰቤን ወደምፈልገው ደረጃ ወይም ለዘመኑ ይገባዋል ወደሚለው ግሎባል እንዲመች እያደረኩት ነውእን ወይስ በፖለቲካ ፓርቲ በዘር እና በእምነት በስውር አጀንዳ በተተበተበ ምሽግ ውስጥ እየከተትኩት እራሴን እየገደልኩት ነው ብዬ ማሰብ አለብኝ፡፡ አንድ ነገር ግን የተረዳሁት ሰው ሌላው የሆነውን በመሆን ሌላውን ሊያስደስት ይችል ይሆናል እንጂ ለእራሱ ግን ሀዘን ነው፡፡
በዚህም በዛም የተረዳሁት ነገር ቢኖር ኢትዮጲያ ላይ ችግራችን ይሆናል ብዬ የገመትኩት፤ በማህበር የተቃቀፈ ማህበራዊ ህይወት የአስተሳሰብ እድገታችንን የገደለው ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡ በማህበር መተቃቀፍ ሳይሰሩ የሰሩ፣ ሳያውቁ አዋቂ፣ ሳይፋቀሩ ተፈቃሪ እና እርስ በእርስ ነውርን መደባበቅ ብቻ ይሆናል፡፡ እከክልኝ ልከክልህ የሆነ በትንንሽ ሰዎች የታመገ ቡድን ከጥንት ጀምሮ በመመስረት የምንኖር መሆናችን እራሳችን መመርመር አለብን፡፡ ሁሉም የምናደርገው የማህበራዊ ሕይወት ተብዬ ማህበር የማንነታችን መደበቂያ ነው፡፤ ሌላው ደግሞ ከሌላው ጋር ካልተቀላቀለ ምንግዜም ተከላካይ እንጂ አጥቂ ሊሆን አይችልም፡፡ ለምሳሌ ብዙ ሰዎች፤ ኢሕአዴግን አንድ ለአምስት መስርቶ ብለው ይተቻሉ፡፡ ለነገሩ ድሮም እኛም አንድ ለአምስት ነን፡፡ ከዛ በላይ እንደእውነቱ ተግባብተን መጉዋዝ አንችልም፡፡ ትርፉ መጩዋጩዋህ ብቻ ነው፡፡ ግን እኔ የምለው ኢህአዴግ ይህንን አንድ ለአምስት የሆነ ባህል ሊጠቀምበት የሚጥር ነው፡፡
አሁንም ሳይ አንድ ለአምስት በፌስቡክም ውስጥ መሰዳደቢያ መወራረጃ፤ መመሰጋገኛ ሆኖ የሰውን የአስተሳሰብ እድገት እያጨደው እየገደለው ነው፡፡ ይህንን ሁሉም አሜን ብሎ የተቀበለው ከጥንት ጀምሮ የለመድነው፤ በግሩፕ አለቃ መነዳትን ነው፡፡ እኔ ለአስተሳሰቤ አለቃ እንዲኖረኝ አልፈልግም፡፡ ግን የምፈልገው ነገር ቢኖር እንዴት የሌላውንም አስተሳሰብ ልጋራ የሚለው ላይ መሆን አለበት፡፡ ኢትዮጲያ ልትለወጥ ትችላላች ብዬ የምገምተው ይህ የግሩፕ አይነት ማህበር ከነአካቴው ጠፍቶ ነገሮችን በስፋት ለማየት ስንዘጋጅ ብቻ ነው፡፡ ካልሆነ በግሩፕ የሚታቀፉ ማህበራት እንኩዋን ለውጥ ሊያመጡልን ቀርቶ ለውጥ እንኩዋን እንደሚያስፈልጉን ሊያሳየን የማይችል እውር አድርጎ ያኖረን፤ ዛሬም እያኖረን ነገም የምንኖርበት አስተሳሰብን የሚያደቅ ቫይረስ ተሸክመን እንደምንኖር ነው፡፡
በኢትዮጲያ ማንኛውም ፖለቲከኛ የሚያደርገው የሚፈጽመው ህዝብ የሚፈልገውን እና አዳብት ያደረገውን ነው፡፡ የግሩፕ መሪ የለለው ማንም በኢትዮጲያ ውስጥ ሊኖር አይችልም፡፤ ይህንንም የግሩፕ ማህበር ዘወትር በማንኛውም ማህበራዊ መሰህበር መስርተን የምንጠቀምበት ነው፡፡ ለምሳሌ ከቤተሰብ ማህበር፣ የአካባቢ ማህበር ለምሳላ የአምባሰል የቦረና የአገው የጎንደር የአክሱም የአዳዋ…….እያለ ከድሮ ጀምሮ በመረዳጃ ስም ያለ እና የተለመደ ያደረጉ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ኢህአዴግ ሳይፈጠር ጀምሮ ያለ ነበር፡፡ በቤተክርስቲያንም ጥቃቅን ማህበር አለ፡፡ እያለ ብዙ ነገር መሰረታችን በጥቃቅን ማህበር ሲጉዋዝ ሲቀራረብ ሲረዳዳ የነበረ ነው፡፡ ማህበር የለለው ሰው መኖር የሚቸገርበት ሁኔታ ብዙ አለ፡፡ ስለዚህ ፖለቲከኞች የተጉዋዙት የህዝቡን የልብ ትርታ እና ፍላጎት በማስተዋል እንጂ ዝም ብለው አይደለም፡፡ የጥቅም ነገር ሲመጣ ነው አንዱ ተስማሚ ሌላው የማይስማማ የሚሆነው፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ ልንነጋገራቸው የሚገባ ነገሮች እያሉ እኛ ግን አሁንም የምንነጋገረው የጣለንን ነገር ልክ እንዳነሳን ሆነን ነው፡፡ ይህ አይመችም፡፡ ሰው መቼም ሌላን አካባቢም ሲያይ ከዛም የሚማረው ነገር ይኖራል እና፡፡ ለመማር ግን መጀመሪያ ሰው እማያውቀው እንዳለ መረዳት አለበት፡፡ እምንማረው ፈተና ለማለፍ ሳይሆን፤ እንዴት መኖር እንዳለብን ለማወቅ መሆን አለበት፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen