ምእራፍ
2
በእራስ መተማመን
ለብዙ ሰው፤ ፊትን በሜክአፕ አሳብዶ ወይም ውድ በሆነ ልብስ አስጊጦ መታየት የሚመስለው አለ፡፡ በቃ ጠላቴን የማሸንፈው ውጫዊ ማንነትን
በማሳየት ነው፡፡ ሰይጣን በውጪው ማንነትህ አይመታም፤ እልብህ በተከልከው የእግዚአብሄር ጦር እንጂ፡፡ እንደእውነቱ ግን ራስ መተማመን የሚባለው የሚፈጠረው የተረጋጋ የፖለቲካ ስራአት፤
አድሎ የለለበት የፖለቲካ እድገት በዜግነትህ አገር ላይ ሲመሰረት ብቻ ነው፡፡ የእራስ መተማመን ወሳኙ፤ በማንነትህ ላይ እንጂ በውጫዊ
አካልህ ላይ አየድደለም፡፡ ውጫዊ አካልህን ማሳመር የሚረዳው እራስን ለመሸንገል እና ለእይታ ብቻ ነው፡፡
ብዙ ግዜ ሕይወቴ በፍርሃት የተሞላ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ይህም
ምንጩ የእራስ መተማመን ማጠቴ ነው፡፡ አውቀዋለሁ ይህንን፤ መኪና መያዜ መንዳቴ ወይም ውድ ልብስ መልበሴ የማይሰጠኝ የእራስ መተማመን፤
በውስጤ መፍጠር አለብኝ፡፡ ይህንን ብዙው አያውቀውም፡፡ በእራስ መተማመን ይሰጣል ብዬ የማምነው ፤ ጥሩ የፖለቲካ ስርአት የሚያስከብረው
ህግ እና በሰዎች ህሊና ባልተጻፈ ህግ የሚቀመጠው ፈሪሃ እግዚአብሄር ነው፡፡ በስርአቱ የእራስ መተማመኔ የጠፋብኝ የህግ የበላይነትን በአካባቢው ስለማይታወቅ ሁሉም ነው ብሎ በሚጠረጥረው ፍርደገምድልነት የተጠመደ ባህሪ በመላበሱ ነው፡፡ ባላደረከው መወንጀል በጣም ቀላል የሆነበት
አካባቢ እንደኢትዮጲያ ያለ አገር ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ፤ የስቃይ ተካፋይ ደግሞም ተመልካች በመሆን ተለማምጀዋለሁ፡፡ ፡፡ እዚህ
ላይ ግን ወገንተኝነት ተሰምቶአችሁ ኢትዮጲያ ስሙዋ ስትነሳ በመከላከል የወደቅንበትን ሽርተቴ መንገድ እንዳናይ በማድረግ አትሩጡ፡፡
የአገር ፍቅር ከስሙ ጋር ብቻ ያለን እንዳንሆን ልብ እንበል፡፡ የታመመ መድሃኒት የሚያገኘው በሽታውን አይነቱን ሲያውቀው ነው፡፡
እንግዲህ በእናንተ ውስጥ ወሳኙ የሚሆነው፤ እውን በአገሬ ለውጥ ማየት እፈልጋለሁ ወይስ እራሴን በንዋይ ከለወጥኩ ዲግሪ ከያዝኩ
ይበቃኛል ነው የምትሉት ? አንድ ሰው መጎዳቱን እኮ የሚያውቀው፤ ስብእናን የሚጎዳውን እና ስሜትን የሚነካውን ነገር ክፉና በጎውን
መለየት ሲያውቅ ብቻ ነው፡፡
የፈለከው ዩኒቨርሲቲ ብትማር፤
የፈለከውን ዲግሪም ብትጨብጥ፤ ስብእናን የተዳፈርክም ልትሆን እንደምትችል እወቅ፡፡ ስንት የተማረ አለ አይደለም እንዴ ለአምባገነን
ለነፍሰገዳይ ተቀጥሮ የሚሰራ፡፡ አይመቸኝም የምትለው እኮ ስለተማርክ ሳይሆን ተፈጥሮ የሰጠችህን አይምሮ ክፉና በጎውን ሲያውቅ ብቻ
ነው፡፡ ስለእግዚአብሄር፤ እውነት ከተናገርን ስንት ሰው አለ ስሙን መጻፍ እና ማንበብ የማይችል የማይስገበገብ፤ የሰውን ማንነት
የሚጠብቅ፡፡ እኛ እኮ ዛሬ ብዙ ሰው ያቃል ተምሮአል ዲግሪ ጨብጦአል በተባለበት ዘመን ነው፤ አብሮ ለመኖር የተቸገርነው፡፡ ድሮ
ተስማምቶ ተጋብቶ ተዋልዶ የለ ሰው፡፡ ካልሆነ በደል ልብስ ሆኖት የሚኖር ሞልቶል፡፡ ተስፋ መቁረጥም የሚመጣው ከዚህ የተነሳ ነው፡፡
ለምሳሌ ጥንት አንድ ሴት ስትጠለፍ እና አስገድዶ መድፈር ሲደርስባት ቆንጆ
ስለሆነች ነው ተብሎ የሆነ ባህላዊ መጽናናትን እያገኘች ኖራለች፡፡ አለማወቅም በእራሱ አንዱ እራስን የማረጋጋት መንገድ ሆኖ አልፎአል፡፡
በዚህም የተነሳ እንዳውም ጠላፊዋን አግብታ የመኖር ያለ እና የኖረ
ነበር፡፡ ማን የጀመረውን ማን ይረከባል ስለሚባል፤ የሽማግሌ ፍርድ
ያግባት ተብሎ ይወሰናል፡፡ ድሮ ብዙ ህጎች ከባህል እና በአካባቢው እድገት የተወሰነ ነበር፡፡ የትም አለም በአንድ አይነት ፖለቲካ
ተነስቶ አድጎ ወደግሎባል ዛሬ የተሸጋገረ ነው፡፡ ፈረንጅ አገር የነበረው ኢትዮፒያም የነበረ ነው፡፡ ንጉስ በሁሉም አለም ተጠቅመውበታል፡፡
አገርን እና ህዝብን ለማስፋት ሲያድግ ደግሞ ንጉሰነግስት እየተባለ፤ ከዛ ኮሚኒዚም ሶሻሊዝም ካፒታሊዝም ….እያለ አደገ፡፡ ታዲያ
ስለአስገድዶ መደፈር ካወራን ለጋብቻ ሕግ ያላት ልጃገረድ ወሳኝነት ነበር እና፡፡ ውጭም ይህ ነበር፡፡ በቃ፡፡
ሁሉ በእድገት ነው የተለወጠው፡፡ ከደርግ ዘመን ወዲህ ግን እያንዳንዱ
ሴት መጠለፍ፤ አስገድዶ መደፈር ወንጀል መሆኑን ማወቅ እና መማር
ጀመረ፡፡ ለምሳሌ አንድ ልጃገረድ ስትዳር ህግ ከለላት እኮ ወደቤተሰቦችዋ በበነገታው ባል ይመልስ ነበር፡፡ ደም የተነከረ ጨርቅ
በሰርግ ማግስት ካልመጣ ወላጅ ባለጌ ልጅ ወልደው ተብሎ ይወቀሳል፡፡ ጥሩ የተራመደ ባል ከተገኘ፤ ቢፈታትም፤ ግን በሰርግ ማግስት
ነጩን ጨርቅ በበግም ሆነ በበግ ደም ለውሶ ቤተሰቡዋን ከእፍረት ያወጣል፡፡ የልጅ አገረድ ህግ ወሳኝነት ነበረው፡፡ ለዚህ ነው አስገድዶ
ደፋሪ አግባ ተብሎ የሚገደደው፡፡
ለብዙ የሴቶች መብት፤ በዘመኑ የታገሉት ሁሉ እነ ኢሕአፓ፤ ሚኤሶን ደርግ፤
እራሱ ወያኔም ቢሆን በታጋዮቹ ደረጃ ሲታይ በጣም የተራመደ አስተዋጽኦ ምእራፍ ለሴቶች ከፍተውለታል ባይ ነኝ፡፡ እማያስፈልግን ባህልን፤
ወይም ሴቶችን የሚያዋርደው እና ሜዳ ላይ የሚጥለውን፤ ሴቶችን የበታች የሚያደርገውን የተለምዶ ባህል ለመናድ ደፍረዋል፡፡ መብት የሚለው ነገር በጋብቻ እና በመሳሰሉት ፖለቲካውንም አነቃንቀውታል፡፡
ይህም ክፉና በጎውን የመለየት ግንባታ ያመጣው ነገር፤ መጠለፍ ወንጀል በመሆኑ፤ ዛሬ እነዛ የሚጠለፉ አልያም አስገድዶ መደፈር የሚደረግባቸው፤
እንኩዋን ደፋሪዋን አግብታ ልትኖር ቀርቶ፤ ያለፉበት ሁኔታ እና ድርጊቱ ታማሚ ያደርጋታል፡፡ ግፍ የሚያሳምምህ ግፍ መሆኑን
ስትገነዘብ ብቻ ነው፡፡ ካልሆነ ባርነትም እኮ ጌጥ ይሆናል፡፡
ስለዚህ መጎዳት የሚታወቀው እና
የሚያመው፤ ክፉና በጎው በህብረተሰብ ውስጥ መለየት ሲጀመር ነው፡፡
ያነዬም እምቢተኝነት ይፈጠራል፡፡ በግል ሳይሆን በማህበርም ደረጃ ነውር ነውር ብሎ ሰውን ከማህበር እስከማግለል ድረስ መደረስ የሚገባውን
ግንባታ አይምሮ መፍቀድ አለበት፡፡ መጎዳትን ግን ምንነቱን የማያውቅ
ያልተረዳ ሰው የሰውን ስንልቦና በቀላሉ ይጎዳል ከጎጂም ጋር ግብረአበር ይሆናል፡፡ሙስና የተዘፈቀ ሰው ቤት ገብተህ ትበላላህ ትጠጣለህ፡፡
ስለበላህ በማንካ መላስህ እራሱ አፍህን እንድትዘጋ ያደርጋሃል፡፡ ይህ እንግዲህ አይምሮህ ማገናዘብ አልቻለም ማለት ነው፡፡ ወዳጄ
ማህበራዊ ሕይወት ነው እያልክ እታች አብረህ እየኖርክ፡፡ በረከት አዳኖም መንግስቱ ብርሃኑ ናቸሰው እያልን መጮሕ ለውጥ አያመጣም፡፡
አበበ ቢሄድ ገብረተንሳይ አልያም ኢብሳ ወይም ቢራራ ዋጋ የለውም፡፡ ለውጥ አንተ ነህ፡፡
በዚህም የተነሳ እኔ መጎዳትን
በጣም እፈረዋለሁ፡፡ ከልጅነቴ አገርን ለቅቄ በሰለጠነው አለም እና ስሜትን መጎዳትን እና መደሰትን ከለየው ህብረተሰብ መኖሬ እና
የህግ የበላይነት ሃይሉን ጉልበቱን መረዳቴ ክፉና በጎውን እንድለይ አድርጎኛል፡፡ የምጎዳውንም እንዳይ የሚጎዳኝንም እዳይ ሆኛለሁ፡፡
አገሬ ተመልሸ ስኖር የተጎዳሁት ነገር ቁጥር ስፍር የለውም፡፡ ለብዙዎች
ይህ እኔ ጉዳት የምለው እንደጤነኛ በመሆኑ ያለ ነው በማለት በፌዝ ያዩታል፡፡ ጉዳት ለብዙዎች የሚመስለው በንዋይ ማግኘት እና ማጣት
ብቻ የተወሰነ ሆኖአል፡፡ ይህን ያደረገው ድህነታችን፤ እራባችን ጥማታችን ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ሆዱ የሞላ ሰው የሚያስበው ስለእራሱ
እንዳይጎድልበት እንጂ ስለአልበላው አይደለም፡፡ ይህ ነገሩ ሁሉ ያመጣው የአስተሳሰብ እድገታችን ላይ፤ ምንም አይነት ስራ ስላልሰራን
ነው፡፡ በዚህም የተነሳ እንዴት ሆዳችንን እንደሞላን እና/ እንዳገኘን/ ፤ ለምን እንደተራበ /እንዳጣን/ ለማወቅ እንቸገራለን፡፡
መፍተሄም አምጪ ልንሆን አንችልም፡፡ አይምሮ የሚሰራውን እንዳያውቅ እድገቱን ለስጋችን ብቻ እንዲውል አድርገነዋል ባይ ነኝ፡፡
ሰው የሚጎዳው ብሩ ሲወሰድበት
ንብረቱ ሲወሰድበት ብቻ ነው ብሎ ማመን የዋሕነት ነው፡፡ እሱ እንዳውም የዘላለም ጉዳት አይሆንም ጊዜያዊ ጉዳት ነው፡፡ ለስነልቦና
ፈታኝ ሊሆን አይችልም ብዬ አምናለሁ፡፡ እኛን ግን አስተሳሰባችንን ጨርግዶ የጣለው የስነልቦና ጉዳቶች የሚያመጡትን ቀውስ አለመረዳት
እና አለማወቅ ነው፡፡ እንጎዳዳለን፤ ግን ይህንን መገንዘብ ተቸግረናል፡፡በክፍል 3 ቀጣዩን ይዠ እቀርባለሁ ፡፡
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen