Sonntag, 29. März 2015

በመከፋፈል ላይ ትንቢተ ግንዛቤ

ኢትዮጲያ በብሄር ብትከፋፈል፤ ኦሮሞው  ከደቡብ ህዝብ፣ ከአማራው፣ ከጉራጌው እና ከአካባቢውም ትንንሽ ብሄሮች ጋር ሰላም አይኖረውም፡፡ ስለዚህ አካባቢው ሁሉ እንደፓልስቲያን እና እስራኤል ልጆች፤ ልጆቻችሁ እርስ በእርሳቸው  አካባቢውን ዲንጋ መወራወሪያ ያደርጉታል፡፡ ከመዋለድም አልፎ የድንበር ከለላው አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ትግራይ ግን ከራያ በላይ ያለውን ግራካሶ ገደል አልፎ ዲነጋ መወርወር ስለማይቻል፤ የትግራይ ነባር ክልሎች በሰላም ይኖራሉ፡፡ ይሁንእና ግን፤ የትግራይ ህዝብ ወደመሃል ኢትዮጲያ እንደልቡ መጉዋዝ እና የፈለገውን እህል እና ጥራጥሬ ሸምቶ ለመመለስ አይችልም፡፡ ይህ የሚሆንበትም ምክናያት፤ ውሎ አድሮ ለብሄር መተራመስ በወያኔ የተነሳ በትግራይ ህዝብ ላይ የሚኖረው አመለካከት የደፈረሰ ስለሚሆን ነው፡፡

 የመገዛት ትእግስት ፡፡---- አገሪቱ ብትገነጣጠል፤ አማራው አካባቢ ሰላም ይሆናል፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክናያት፤ የአማራው ህዝብ የማተርያል ጉጉት የለለው እና፤ በአንድ ልብስ ብዙ አመት መኖር የሚችል እና ካለጫማም መሬትን የሚደፍር ስለሆነ ነው፡፡ ይህም ደግሞ የሚሆነው ለእምነት የተገዛ ሙስሊም እና ኦርቶዶክስ፤ አምላኩን ተስፋ አድርጎ የሚኖር ልምድ ያካበተ በመሆኑ ነው፡፡ ለዚህም መረጃዎች በአማራው ክልል የሚገኙ ገዳማት ሲሆን በገዳሙ አካባቢ የሚኖረው ነዋሪ ህዝብም ንዋይ ሰፍ የማያደርገው በመሆኑ ነው፡፡ አማራው ህዝብ ለህግ መገዛቱም፤ እና ለሰላም ለአንድነት በባዶ ኪሱ መጣሩ በእራሱ ለአካባቢው ሰላም አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ ወያኔ ኢሕአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ ወዲህ፤ በአማራው ላይ ያለፈው ስርአት ገዢ፣ በዳይ እና ጨቁዋኝ እየተባለ እንደተፈረጀ እና ፤ የዘመናት ጥፋት በዚህ  ብሄር ላይ እንደተጠቃለለ የ24 አመቱ ሲወራ ሲዘከር የነበረው ታሪክ መረጃ ነው፡፤ ይሁን እና ግን አማራው ደግሞ ከማንኛውም ዘር የበለጠ በትምህርት ቤትም ሆነ በኢኮኖሚው ከሌላው ክልል የተሻለ እና፤ የተለዬ ተጠቃሚ ያደረገው ምንም አይነት መረጃ አልተገኘም፡፡ አማራው ግን አንድነት ሰላም ነው ብሎ ደምድሞ ይዞ እየተጉዋዘ ነው፡፡ ይህም መረጃ የሚሆነው፤ ወደፊትም ኢትዮጲያ ብትገነጣጠል፤ አማራው ለተሰጠው ጥዋ ሰላሙን እና አስተዳደሩን አስተካክሎ መኖር ይችላል፡፡ የሚቀርበት ከሌላው ብሄር ጋር የሚለዋወጠው ፍቅር ብቻ እንጂ፤ ንዋይ ሊሆን አይችልም፡፡

 ወጣቱ፡፡------ኢትዮጲያ ብትገነጣጠል ያለፉት መንግስታቶች እስከመንግስቱ ሀይለማርያም ድረስ ይመሰገናሉ ይወደሳሉ፡፡ ምክናያቱም በመከፋፈል ሰላም አይኖርም፡፡ ትውልዱም ያለፈውን ታሪክ ሲሰማ የተገነጣጠለበትን ዘመን ግን ይረግማል ይወቅሳል ይጠላል፡፡ ሰላም ይናፍቀዋል እና፡፡

እምነት፡፡-----ፔንጤ በኢትዮጲያ ውስጥ የገነነው በወያኔ ኢሕአዴግ ዘመን ነው፡፡ በዚህ  በወያኔ ዘመን፤ ስለዘር ወይም ብሄር የሚባልበት ገኖ በሚወራበት አዲስ ዘመን ፤   የፔንጤ እምነት ተከታይ የሆኑ ባለስልጣናት እና ስራ አስፈጻሚዎች የሚገኙበት እና በአስተዳደሩም የተካፈሉበት ወቅት ነው፡፡ ይህ አዲስ የሆነ ነገር፤ ብዙ ፔንጤዎችንም ይህንን አሁን ያለውን አስተዳደር እንደሚደግፉ በሰፊው ይነገራል፡፡ ደግሞም ሰው ነጻነቴን አግኝቸበታለሁ የሚለውን ስርአት መደገፉ ትክክል ቢሆንም፤ ግን የሁሉንም መብት እኩል ያልጠበቀውን ስርአት መደገፍ በብዙዎች ላይ ልዩነት  እንደፈጠረ የማንክደው ሀቅ ሆኖአል፡፡ ስለዚህ የምንኖርበት አካባቢ ሰላሙን ለመጠበቅ ሁሉም በመብቱ እኩል መስተናገድ እንደሚኖርበት፤ የሰው ልጅ ሁሉ ለሌላውም መቆም አለበት፡፡ ኢትዮጲያ የሁሉም ዘር እና ሃይማኖት እኩል መስተናገጃ ካልሆነች ሁከት እንጂ ሰላም አይኖርም፡፡ እንደአማኝ  ስናስብ፤ ለእምነት የአካባቢ ሰላም ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህ እኔን ተመችቶኛል እና ለሌላው ዴንታ የለኝምም ማለት አንችልም፡፡ አልያም ትናንት እኔ ተገፍቻለሁ እና፤ ዛሬ እኔ ሌላውን ልግፋም ማለት ሀጢያት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ኢትዮጲያ በተጋረጠባት የብሄር ክፍፍል እውን ሆኖ ብትገነጣጠል፤ ፔንጤ በኢትዮጲያ ውስጥ ፈታኝ የሆነ ግዜ ሊገጥመው ይችላል፡፡ ብዙ የቤተክርስቲያን አባል ሊያጣ ይችላል፡፡ ይህን የሚያደርገውም፤  ኢትዮጲያ ብትከፋፈል የአካባቢው ሰላም ስለሚደፈርስ ነው፡፡ በብሄር የተነሳ አገሪቱን መከፋፈል የሚያመጣው ትርፍ፤ የተዋለደው የጉላላል፤ ከየአካባቢውም ይገለላል፡፡ የወሰን ክፍፍሉም አካባቢውን የጦርነት አውድማ ያደርገዋል፡፡ በዚሀወም የተነሳ ወጣቶችም አብረው እንዳይውሉ የሚያደረግ የመበቃቀል ሁኔታ ይከሰታል፡፡ ስለዚህ ፔንጤ የሆነ ሁሉ ይህ የብሄር ክፍፍል እውን እንዳይሆን እና ኢትዮጲያ እንዳትገነጣጠል የፍቅር ስበካውን ሁሉም በየብሄሩ ማስተናገድ እና፤ የአንድነት ጥቅምንም ማስረዳት አለበት፡፡ በአካባቢው የሁሉ ግንዛቤ እኩል ስላልሆነ ይህ ከመሆኑ በፊት ቀድሞ አገሪቱን መጠበቅ ግድ ይላል፡፡ ክርስቶስ ሰላም ነው፡፡ ክርስቶስ ፍቅር ነው፡፡ አገሪቱ ድህነት ቢኖራትም፤ ኦርቶዶክስ እና ሙስሊሙ እስከአሁን  ምንም ንዋይ ሳይበግረው በሰላም እና በአንድነት አገሪትን ጠብቆዋት ኑሮአል እና፡፡ ሰው ይጠፋል ያለው፤ ይለመልማል፡፡ ሰው ያገነነው ይወድቃል፡፡ አንድ አገር የገነነ ነገር ስትሰራ የመውደቁዋ ምክናያት ይሆናል፡፡  አንድ መሪ ፎቶውን እና ሀውልቱን ሲያቆምም ይቀሰፋል፡፡ ቤተክርስቲያን ልትጠለፍ ትችላለች፡፡ አንተ ግን የእራስህ በመሆንህ ለእግዚአብሄር እውነት ተውስናለህ፡፡ በልብህ ውስጥ ያለውን ማን ይጠልፋልእና፡፡ያለፈው ዘመን የኦርቶዶክስ እና በሙስሊሙአንድነት ያለፈ ይመስላል፡፡ የዛሬው ደግሞ በአዲስ ተተክቶአል፡፡ አዲሱ ያለፈውን በየት ላግኘው የሚያስብል ሊሆን ይችላል እና፡፡

ሁላችንም የኢትዮጲያን አንድነት የምንፈልገው ከሆነ፤ ስራ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ የማንፈልገውም ከሆነ ሁሉም የእራሱን ፍላጎት ይጠይቃል፡፡ አሁን ወያኔ ጥሩ ነው መጥፎ ነው የሚለው ሳይሆን፤ በአገሪቱ ውስጥ ያለው ክፍተት ከየት ወደየት እየወሰደን እንደሆነ ማስተዋል ግድ ይለናል፡፡ እምነት ላላቸው ሰዎች ሁሉ በአገሪቱ ውስጥ ፖለቲከኞች ተቀራርበው የሚሰሩበትን አጀንዳ እንዲከፍቱ ማስገደድ ግድ ይለናል፡፡ አገሪቱን ማዳን ማለት ሰላምን መጠበቅ ነውእና፡፡ ፖለቲከኞች አንድ ቀን ከስልጣን ይለያሉ፡፡ ግን ትተውልን የሚያልፉትን ቀውስ  ለትውልዱ እንደእርግማን መተው እና መሄድ የማይገባን እኛ ሕዝብ ነን፡፡ ጦርነት የረሳው እና የማያውቀው ትውልድ ጦርነትን በአገሩ አሳልፎ በየሰፈሩ እንዳይሆንበት፤ ለአንድነት፤ ለዲሞክራሲ ፤ ለሰላም መወሰን እና ማስተዋል አለበት፡፡
ባዩሽ

Mittwoch, 18. März 2015

እባካችሁ ተረዱኝ "2"

ምእራፍ 2

በእራስ መተማመን ለብዙ ሰው፤ ፊትን በሜክአፕ አሳብዶ ወይም ውድ በሆነ ልብስ አስጊጦ መታየት የሚመስለው አለ፡፡ በቃ ጠላቴን የማሸንፈው ውጫዊ ማንነትን በማሳየት ነው፡፡ ሰይጣን በውጪው ማንነትህ አይመታም፤ እልብህ በተከልከው የእግዚአብሄር ጦር እንጂ፡፡  እንደእውነቱ ግን ራስ መተማመን የሚባለው የሚፈጠረው የተረጋጋ የፖለቲካ ስራአት፤ አድሎ የለለበት የፖለቲካ እድገት በዜግነትህ አገር ላይ ሲመሰረት ብቻ ነው፡፡ የእራስ መተማመን ወሳኙ፤ በማንነትህ ላይ እንጂ በውጫዊ አካልህ ላይ አየድደለም፡፡ ውጫዊ አካልህን ማሳመር የሚረዳው እራስን ለመሸንገል እና ለእይታ ብቻ ነው፡፡ 
  
          ብዙ ግዜ ሕይወቴ በፍርሃት የተሞላ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ይህም ምንጩ የእራስ መተማመን ማጠቴ ነው፡፡ አውቀዋለሁ ይህንን፤ መኪና መያዜ መንዳቴ ወይም ውድ ልብስ መልበሴ የማይሰጠኝ የእራስ መተማመን፤ በውስጤ መፍጠር አለብኝ፡፡ ይህንን ብዙው አያውቀውም፡፡ በእራስ መተማመን ይሰጣል ብዬ የማምነው ፤ ጥሩ የፖለቲካ ስርአት የሚያስከብረው ህግ እና በሰዎች ህሊና ባልተጻፈ ህግ የሚቀመጠው ፈሪሃ እግዚአብሄር ነው፡፡  በስርአቱ የእራስ መተማመኔ የጠፋብኝ  የህግ የበላይነትን በአካባቢው ስለማይታወቅ ሁሉም ነው ብሎ በሚጠረጥረው ፍርደገምድልነት የተጠመደ ባህሪ በመላበሱ ነው፡፡ ባላደረከው መወንጀል በጣም ቀላል የሆነበት አካባቢ እንደኢትዮጲያ ያለ አገር ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ፤ የስቃይ ተካፋይ ደግሞም ተመልካች በመሆን ተለማምጀዋለሁ፡፡ ፡፡ እዚህ ላይ ግን ወገንተኝነት ተሰምቶአችሁ  ኢትዮጲያ ስሙዋ ስትነሳ  በመከላከል የወደቅንበትን ሽርተቴ መንገድ እንዳናይ  በማድረግ  አትሩጡ፡፡ የአገር ፍቅር ከስሙ ጋር ብቻ ያለን እንዳንሆን ልብ እንበል፡፡ የታመመ መድሃኒት የሚያገኘው በሽታውን አይነቱን ሲያውቀው ነው፡፡ እንግዲህ በእናንተ ውስጥ ወሳኙ የሚሆነው፤ እውን በአገሬ ለውጥ ማየት እፈልጋለሁ ወይስ እራሴን በንዋይ ከለወጥኩ ዲግሪ ከያዝኩ ይበቃኛል ነው የምትሉት ? አንድ ሰው መጎዳቱን እኮ የሚያውቀው፤ ስብእናን የሚጎዳውን እና ስሜትን የሚነካውን ነገር ክፉና በጎውን መለየት ሲያውቅ ብቻ ነው፡፡ 

የፈለከው ዩኒቨርሲቲ ብትማር፤ የፈለከውን ዲግሪም ብትጨብጥ፤ ስብእናን የተዳፈርክም ልትሆን እንደምትችል እወቅ፡፡ ስንት የተማረ አለ አይደለም እንዴ ለአምባገነን ለነፍሰገዳይ ተቀጥሮ የሚሰራ፡፡ አይመቸኝም የምትለው እኮ ስለተማርክ ሳይሆን ተፈጥሮ የሰጠችህን አይምሮ ክፉና በጎውን ሲያውቅ ብቻ ነው፡፡ ስለእግዚአብሄር፤ እውነት ከተናገርን ስንት ሰው አለ ስሙን መጻፍ እና ማንበብ የማይችል የማይስገበገብ፤ የሰውን ማንነት የሚጠብቅ፡፡ እኛ እኮ ዛሬ ብዙ ሰው ያቃል ተምሮአል ዲግሪ ጨብጦአል በተባለበት ዘመን ነው፤ አብሮ ለመኖር የተቸገርነው፡፡ ድሮ ተስማምቶ ተጋብቶ ተዋልዶ የለ ሰው፡፡ ካልሆነ በደል ልብስ ሆኖት የሚኖር ሞልቶል፡፡ ተስፋ መቁረጥም የሚመጣው ከዚህ የተነሳ ነው፡፡

 ለምሳሌ ጥንት አንድ ሴት ስትጠለፍ እና አስገድዶ መድፈር ሲደርስባት ቆንጆ ስለሆነች ነው ተብሎ የሆነ ባህላዊ መጽናናትን እያገኘች ኖራለች፡፡ አለማወቅም በእራሱ አንዱ እራስን የማረጋጋት መንገድ ሆኖ አልፎአል፡፡  በዚህም የተነሳ እንዳውም ጠላፊዋን አግብታ የመኖር ያለ እና የኖረ ነበር፡፡  ማን የጀመረውን ማን ይረከባል ስለሚባል፤ የሽማግሌ ፍርድ ያግባት ተብሎ ይወሰናል፡፡ ድሮ ብዙ ህጎች ከባህል እና በአካባቢው እድገት የተወሰነ ነበር፡፡ የትም አለም በአንድ አይነት ፖለቲካ ተነስቶ አድጎ ወደግሎባል ዛሬ የተሸጋገረ ነው፡፡ ፈረንጅ አገር የነበረው ኢትዮፒያም የነበረ ነው፡፡ ንጉስ በሁሉም አለም ተጠቅመውበታል፡፡ አገርን እና ህዝብን ለማስፋት ሲያድግ ደግሞ ንጉሰነግስት እየተባለ፤ ከዛ ኮሚኒዚም ሶሻሊዝም ካፒታሊዝም ….እያለ አደገ፡፡ ታዲያ ስለአስገድዶ መደፈር  ካወራን  ለጋብቻ ሕግ ያላት ልጃገረድ ወሳኝነት ነበር እና፡፡ ውጭም ይህ ነበር፡፡ በቃ፡፡ ሁሉ በእድገት ነው የተለወጠው፡፡ ከደርግ ዘመን ወዲህ  ግን እያንዳንዱ ሴት መጠለፍ፤ አስገድዶ መደፈር  ወንጀል መሆኑን ማወቅ እና መማር ጀመረ፡፡ ለምሳሌ አንድ ልጃገረድ ስትዳር ህግ ከለላት እኮ ወደቤተሰቦችዋ በበነገታው ባል ይመልስ ነበር፡፡ ደም የተነከረ ጨርቅ በሰርግ ማግስት ካልመጣ ወላጅ ባለጌ ልጅ ወልደው ተብሎ ይወቀሳል፡፡ ጥሩ የተራመደ ባል ከተገኘ፤ ቢፈታትም፤ ግን በሰርግ ማግስት ነጩን ጨርቅ በበግም ሆነ በበግ ደም ለውሶ ቤተሰቡዋን ከእፍረት ያወጣል፡፡ የልጅ አገረድ ህግ ወሳኝነት ነበረው፡፡ ለዚህ ነው አስገድዶ ደፋሪ አግባ ተብሎ የሚገደደው፡፡

 ለብዙ የሴቶች መብት፤ በዘመኑ የታገሉት ሁሉ እነ ኢሕአፓ፤ ሚኤሶን ደርግ፤ እራሱ ወያኔም ቢሆን በታጋዮቹ ደረጃ ሲታይ በጣም የተራመደ አስተዋጽኦ ምእራፍ ለሴቶች ከፍተውለታል ባይ ነኝ፡፡ እማያስፈልግን ባህልን፤ ወይም ሴቶችን የሚያዋርደው እና ሜዳ ላይ የሚጥለውን፤ ሴቶችን የበታች የሚያደርገውን የተለምዶ ባህል ለመናድ ደፍረዋል፡፡  መብት የሚለው ነገር በጋብቻ እና በመሳሰሉት ፖለቲካውንም አነቃንቀውታል፡፡ ይህም ክፉና በጎውን የመለየት ግንባታ ያመጣው ነገር፤ መጠለፍ ወንጀል በመሆኑ፤ ዛሬ እነዛ የሚጠለፉ አልያም አስገድዶ መደፈር የሚደረግባቸው፤ እንኩዋን ደፋሪዋን አግብታ   ልትኖር ቀርቶ፤  ያለፉበት ሁኔታ እና ድርጊቱ ታማሚ ያደርጋታል፡፡ ግፍ የሚያሳምምህ ግፍ መሆኑን ስትገነዘብ ብቻ ነው፡፡ ካልሆነ ባርነትም እኮ ጌጥ ይሆናል፡፡ 

ስለዚህ መጎዳት የሚታወቀው እና የሚያመው፤  ክፉና በጎው በህብረተሰብ ውስጥ መለየት ሲጀመር ነው፡፡ ያነዬም እምቢተኝነት ይፈጠራል፡፡ በግል ሳይሆን በማህበርም ደረጃ ነውር ነውር ብሎ ሰውን ከማህበር እስከማግለል ድረስ መደረስ የሚገባውን ግንባታ አይምሮ መፍቀድ አለበት፡፡  መጎዳትን ግን ምንነቱን የማያውቅ ያልተረዳ ሰው የሰውን ስንልቦና በቀላሉ ይጎዳል ከጎጂም ጋር ግብረአበር ይሆናል፡፡ሙስና የተዘፈቀ ሰው ቤት ገብተህ ትበላላህ ትጠጣለህ፡፡ ስለበላህ በማንካ መላስህ እራሱ አፍህን እንድትዘጋ ያደርጋሃል፡፡ ይህ እንግዲህ አይምሮህ ማገናዘብ አልቻለም ማለት ነው፡፡ ወዳጄ ማህበራዊ ሕይወት ነው እያልክ እታች አብረህ እየኖርክ፡፡ በረከት አዳኖም መንግስቱ ብርሃኑ ናቸሰው እያልን መጮሕ ለውጥ አያመጣም፡፡ አበበ ቢሄድ ገብረተንሳይ አልያም ኢብሳ ወይም ቢራራ ዋጋ የለውም፡፡ ለውጥ አንተ ነህ፡፡

በዚህም የተነሳ እኔ መጎዳትን በጣም እፈረዋለሁ፡፡ ከልጅነቴ አገርን ለቅቄ በሰለጠነው አለም እና ስሜትን መጎዳትን እና መደሰትን ከለየው ህብረተሰብ መኖሬ እና የህግ የበላይነት ሃይሉን ጉልበቱን መረዳቴ ክፉና በጎውን እንድለይ አድርጎኛል፡፡ የምጎዳውንም እንዳይ የሚጎዳኝንም እዳይ ሆኛለሁ፡፡  አገሬ ተመልሸ ስኖር የተጎዳሁት ነገር ቁጥር ስፍር የለውም፡፡ ለብዙዎች ይህ እኔ ጉዳት የምለው እንደጤነኛ በመሆኑ ያለ ነው በማለት በፌዝ ያዩታል፡፡ ጉዳት ለብዙዎች የሚመስለው በንዋይ ማግኘት እና ማጣት ብቻ የተወሰነ ሆኖአል፡፡ ይህን ያደረገው ድህነታችን፤ እራባችን ጥማታችን ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ሆዱ የሞላ ሰው የሚያስበው ስለእራሱ እንዳይጎድልበት እንጂ ስለአልበላው አይደለም፡፡ ይህ ነገሩ ሁሉ ያመጣው የአስተሳሰብ እድገታችን ላይ፤ ምንም አይነት ስራ ስላልሰራን ነው፡፡ በዚህም የተነሳ እንዴት ሆዳችንን እንደሞላን እና/ እንዳገኘን/ ፤ ለምን እንደተራበ /እንዳጣን/ ለማወቅ እንቸገራለን፡፡ መፍተሄም አምጪ ልንሆን አንችልም፡፡ አይምሮ የሚሰራውን እንዳያውቅ እድገቱን ለስጋችን ብቻ እንዲውል አድርገነዋል ባይ ነኝ፡፡
  
ሰው የሚጎዳው ብሩ ሲወሰድበት ንብረቱ ሲወሰድበት ብቻ ነው ብሎ ማመን የዋሕነት ነው፡፡ እሱ እንዳውም የዘላለም ጉዳት አይሆንም ጊዜያዊ ጉዳት ነው፡፡ ለስነልቦና ፈታኝ ሊሆን አይችልም ብዬ አምናለሁ፡፡ እኛን ግን አስተሳሰባችንን ጨርግዶ የጣለው የስነልቦና ጉዳቶች የሚያመጡትን ቀውስ አለመረዳት እና አለማወቅ ነው፡፡ እንጎዳዳለን፤ ግን ይህንን መገንዘብ ተቸግረናል፡፡በክፍል 3 ቀጣዩን ይዠ እቀርባለሁ ፡፡

እባካችሁ ተረዱኝ " 2 "

ክፍል 2

ሰው የሚጎዳው ብሩ ሲወሰድበት ንብረቱ ሲወሰድበት ብቻ ነው ብሎ ማመን የዋሕነት ነው፡፡ እሱ እንዳውም የዘላለም ጉዳት አይሆንም ጊዜያዊ ጉዳት ነው፡፡ ለስነልቦና ፈታኝ ሊሆን አይችልም ብዬ አምናለሁ፡፡ እኛን ግን አስተሳሰባችንን ጨርግዶ የጣለው የስነልቦና ጉዳቶች የሚያመጡትን ቀውስ አለመረዳት እና አለማወቅ ነው፡፡ እንጎዳዳለን፤ ግን ይህንን መገንዘብ ተቸግረናል፡፡በክፍል 3 ፡፡

Mittwoch, 11. März 2015

እባካችሁ ተርዱኝ

ምእራፍ----    አንድ

አንድ ነገር አለ ዛሬ ዛሬ ያመንኩበት፡፡ ምንአልባት እኔን እራሴ አስተሳሰቤ ገሎኝ አልፎ ሊሆን ይችላል፡፡ በጭራሽ አድርባይ ሆኘ አላውቅም፡፡ ግን አድርባይን የምፈራ ሴት ነበርኩ፡፡ አሁንም እደፍራቸዋለሁ ማለት አይደለም፡፡ አድርባይ በሰው አይምሮ ላይ የፈረደ ውሸታም አስመሳይ እና እበላ ባይ ነው፡፡ እባካችሁ ተረዱኝ፡፡ ይህንን ስላችሁ ሆነ ብዬ የኢሕአዴግ አልያም የተቃዋሚንም ደጋፊ ተብዬ አወናባጅ ሁሉ ለመምታት አይደለም፡፡ አድርባይ የትም ብትሄድ የትም አለ፡፡ በጥቃቅን ማሃበራት ውስጥ እራሱ ስንት አለ እንደውሻ የሚያነፈንፍ፡፡ አድርባይ አቁዋም የለለው እና አገር ወገን ዘመድ አዝማድን ሁሉ አማሽ ነው፡፡ አድርባይነት የህይወት ፍርሃት እና ዋስትና ማጣት ለስጋዊ  ኑሮ ሲባል ፤በእራስ መተማመን ማጣት የሚፈጠር የሰው ልጅ ባህሪ ነው፡፡ ታዲያ እኔ ልነግራችሁ የፈለኩት፤ እከሌ እንዲሕ እንዲያ ነው ብዬ ወደሶስተኛ ሰው ከማስተላልፍ የእራሴን የህይወት ልምድ ያስፈሩኝኝ እና ያስጨነቁኝን ያሳዘኑኝን በእራሴው በዚሁ በሚዲያዬ/ በፌስቡክ ድረገጼእና በብሎጌ በኩል ላጫውታችሁ ፈልኩ፡፡ እኔ መቸም ኢሳትንም ሆነ የነሚሚ ስባሀቱን ፋና ሚዲያ አገኝቼ እናንተ ጋር መገናኘት አልችልም፡፡ ለዚህ እራሴን ምርቻ ውስጥ አቅርቤ የተወዳደርኩ አይደለሁም፡፡ በወረቀትም፣ በገንዘብም፣ በእውቀትም፣ ደግሞም በአድርባይነትም  እኔ ስለማልታወቅ እንዚህ ሚዲያዎች ለእኔ በሩን አይከፍቱትም፡፡ ስለዚህ የእራሴን ማህበራዊ ሚዲያ ማዘጋጀቱ ወሳኝነት እንዳለሁ ተረድቻለሁ፡፡ ይህን ቴክኖሎጂ ያዘጋጁልን ባለአይምሮዎች ይባረኩ፡፡ ተንፍሶ መሞት እንዴት ጥሩ ነገር መሰላችሁ፡፡ ስለዚህ እንድተነፍስ ከአየር ጋር እንድገናኝ አጋዥ ሆነውኛልእና፡፡ አዎ አሁንም ይባረኩ፡፡
                   እንግዲህ የትኛው ምስክርነት ይደምቃል ካላችሁ ከእራስ ወደሁለተኛ ወገን የሚተላለፍ ብቻ ነው፡፡ አሉባልታም አይሆንም፡፡ ከዚያ ምን ትምህርት አገኛችሁ ብቻ ሳይሆን ሰውም የወደቀውን ባህሪውን በውስጡ እንዲያይ ለማድረግ ነው ጥረቴ፡፡ ግልጽነቴ ለእኔ  የተጎዳውን ውስጤን ለማከም የምጠቀምበት ዘዴዬ ነው፡፡ መጻፍ ይጠግናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ማንበብ ደግሞ የጨለመ አይምሮን ባትሪ ሆኖ የብርሃን ጭላጭል ያበጅለታል፡፡ አይምሮ ነው ወሳኙ፤ ለመጉዳትም ለመጎዳትም፡፡ የተጎዳውን ማንነታችንን ለመጠገን መጀመሪያ መጎዳታችን እንዴት እና ለምን እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ ብዙ ግዜ ጠላትህ ጋር ሽማግሌ ያስታርቀሃል፡፡ የባህል አፋኝነት ሸንጋይነት እዚህ ላይ ነው፡፡ ግን ጠላትህ የሰበረው ማንነት ሽማግሌው ከአንተ ውስጥ ሊያወጣው ችሎታ የለውም፡፡ እንዳውም የሚያደርግህ በውስጥህ በደልን አምቀሕ እንድትኖር ነው፡፡ እሱ በውነት ምላች እንዳስቀመጥቅ አይነት ነገር ነው፡፡ ማንኛውም በደል መሰራት ያለበት ነገር እንጂ የምታስቀምተው መሆን አይገባም፡፡ ስለዚህ ውስጥህን እያደቀቀ ስነልቦናህን ጨርግዶ ይበላሃል፡፡ ይቅር የምትለው እኮ፤ ጠላትህ እውነትም ተሰምቶት ይቅርታ አድርግልኝ ብሎ ሲሰማው ሲጸጽተው ነው፡፡ ሽማግሌ ግን የሚያስተርቅህ ከሰውዬው ስለመጣ ሳይሆን እነሱ መልካም ነው ብለው ስላሰቡ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በኢትዮጲያ ያልተጎዳ ሰው አለ ብዬ ለመገመት ያዳግተኛል፡፡ ይህን ልል ያልኩበት ምክናያት በቃ እንደባህል ማንም ተነስቶ የፈለገውን የሚያደርግብህ እና ምንም አይነት የመጎዳት ስሜት ሊረዳ የማይችል ብዙ ስላየሁ ነው፡፡
ምንአልባት እኔም ያጠፋሁት ጥፋት ሊኖር ይችላል፡፡ ግን ያ የሆነው መጎዳትን ምን ያህል ስብርብር እንደሚያደርግ ባልተረዳሁበት ወቅት ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ ብዙ ነገሮች አሉ ባለማወቅ ጤነኛ የሚመስሉን፤ ግን ጤነኞች እኮ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ ባዩሽ እንዲህ እንዲህ ናት ቢሉዋችሁ፤ አይቶኝም ሰምቶኝም የማያውቀው አምኖ ተቀብሎ እሱም ለሌላ ያስተላልፋል፡፡ ይህ ያየሁት እና የተለማመድኩት ስለሆነ ደብቄ ወይም በብሄራዊ ስሜት አፍኘ ላልፈው የሚገባኝ አይደለሁም፡፡ „አትፍረድ“ የሚለውን እንኩዋን  ያነበብነውን መተግበር አንችልም፡፡ ይህ አይነት ባህሪ በቤተክርስቲያን ምእመናንም ሆነ በፖለቲካው አለም አቀንቃኞች ያየሁት ነው፡፡ በቃ በቀላሉ ከጭዋታ ውጭ ትደረጋለሕ፡፡ ለምን ያሰው ያቺ ሴት ይህንን አወራችባት ይህንን አወሩበት ብሎ የሚጠይቅ እና የእራሱን ግንዛቢ ሊጠቀም የሚችል እጅግም አላየሁም፡፡
በልጅነቴ ኢትዮጲያን የለቀቁት ሴት፤ ከወጣሁበት ግዜ እና ከሌላው አለም ህብረተሰብ ጋር የተቀላቀልኩበት ግዜ ጀምሬ ፤ይቅርታ እና ምስጋና በቀን ስንት ግዜ እየተናገርናቸው እንደምንውል የማይለዩን ዘመናዊ እና የሰለጠኑ ቃላቶች መሆናቸውን ተምሬአለሁ፡፡ በሚሊዮን ግዜ በላይ እነዚህን ቃላቶች እንደሌላው የሰለጠነ ህዝብ እስከአሁን እጠቀምባቸዋለሁ፡፡ እንዳውም በዘመኔ በፍቅር የማወጣው ቃል ቢኖር፤ ይቅርታ መጠየቅ እና ማመስገን ናቸው፡፡ ብርጭቆም ልጆቼ አንስተው ቢሰጡኝ፤ ውሃ ቢያጠጡኝ አመሰግናለሁ ካላልኩ ይታዘቡኛል፡፡ ከትዝብቱ በፊት ግን ማውጣት እንዴት አይነት መከበርን እንደሚያስገኝ አውቀዋለሁ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ቃላቶች ማንም ጤነኛ አይምሮ ያለው ሰው ሊላመደው ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ እናት ነኝ እና ሁልግዜ ለልጆቼ ምግብ ሰርቼ ስሰጥ“ አመሰግናለሁ ማዘር“ የሚሉኝ ምላሽ በውነቱ መማርስ ይህንን ያሰኛል፡፡ በቃ ስሜትን ማስደሰት እና ማሳዘን የሚቻል ነገር መሆኑን ገና ከሕጻንነት መማር እንዴት ደስ ይላል፡፡ እናትነትም ግዳጅ አይደለም እኮ፡፡ እናትነትም ስሜት አለው፡፡ የስሜት መግለጫውም ማንም ሰው ይቅርታ መጠየቅ እና መመስገን የሚፈልግበት ስሜት አለው፡፡ ካልሆነ እየበደለህ እንደባህል ነውሩን እየሸፈንክለት፤ አድም ሲልህ አብረህ እያደምክ፡፡ የወዳጅህን ነውር እያወደስክ እነዴት ይለመዳል፡፡ በውነቱ ይህ አስፈርቶኛል በኢትዮጲያ፡፡
 ይቅርታ እና ምስጋና  በኢትዮጲያ ውስጥ የተለመዱ አይደሉም፡፡ እንዳውም የሚገርመኝ ልኩዋን ነገረቻት ብለው በመጥፎ ደፋር ቃላት ተናገሪ ሲያወኩ ሲስቁ አይ ነበር፡፡ ከአፉ የደፈረ የሰፈር ጀግን ብዙ አፍርተናል፡፡  ስለዚህ የምንጎዳዳውን እያደገ እያደገ የገዛ ንብረትህንም ተዘርፈህ አጥተህ የምትሸሽበት እላይ ጣራ ዘለል ጉዳቶች በሽ ነው፡፡ እኛው እራሳችን በማዳነቅ መጥፎ ባህልን ይለፍ ሰጥተናል እና፡፡  በዚህ የተነሳ ከብዙው በጥቂቱ ጎድተውኛል የምላቸውን ነገሮች አልፎ አልፎ እራሴን ግልጽ በማድረግ ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡ ዛሬ የማጫውታችሁ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተከወነውን ነው፡፡ ቀጣዩን በክፍል 2 ተከታተሉ

Dienstag, 10. März 2015

ለዲሞክራሲ የህዝብ የአስተሳሰብ ብቃት ወሳኝነት አለው

ዛሬ ያየሁት እና የገረመኝ ማንነት አለ፡፡ ለመሆኑ የኢትዮጲያ ገዢ ፓርቲው ከእኛ ምን ይፈልጋል? በስልጣን ላይ እንዲቆይ እንድንረዳው ንውን ?ወይስ በስልጣን ዘመኑ እያለ የዲሞክራሲ ስራ እንዲሰራ ስራውን እንድንካፈለው? ይህንን ፖለቲከኞቻችን ሁሉ እራሳቸው ፍላጎታቸውን ለየትው ባለማወቃቸው፤ ሕዝብ የአድርባይነት እና የእራስ ወዳድነት ባህሪ እንዲላመድ እንዲገነባ አድርገውታል፡፡ ሁልግዜ ገዢ ፓርቲንም የሚደግፈው የንዋይ ተጠቃሚ ብቻ እየሆነ ይሄዳል፡፡ አንድ ገዢ ፓርቲም በድሃ አገር ሁሉንም ተጠቃሚ የማድረግ አቅም ፍጹም ሊኖረው አይችልም፡፡ ስለዚህ የማይጠቀመው በላጩ ክፍል ደግሞ የማያውቀውን ተቃዋሚ ደጋፊ ይሆናል፡፡ ይህ በአንድ አገር ውስጥ ሁለት ዜጋ የሚመሰርት ከባድ የሆነ የስነልቦና ተጽእኖ በሁለቱም ክፍል ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ ገዢ ፓርቲዎች የህብረተሰቡን የአስተሳሰብ እድገት ባለመረዳት፤ አልያም በመዝጋት አገርን ፈተና ላይ ይጥላሉ፡፡ ሌላው ሁሉም ፖለቲከኞች ያልነቃን ሕሊና እና ግንዛቤ የለለውን አይምሮ እንዳሻቸው እንደተመቻቸው ለመንዳት አቅምም ያገኛሉ፡፡ ይህ ለገዢውም ፓርቲ ሆነ ለተቃዋሚ የሚጠቅም ነገር የለም፡፡ የሁሉንም ጉዞ እረጅም፤ ውስብስብ እና ግራ የተጋባ ያደርገዋል፡፡ እኔ በበኩሌ፤ ድህነታችንን እና፤ የስራ ፈጠራ ችግራችን አስተሳሰባችንን ሊያሳድገው ባለመቻሉ፤ ሁላችንም እራሳችንን ወዳድ የሆነ ባህሪ የገነባን እና ለፖለቲካውለውጥ አስቸጋሪ ሆነናል፡፡
ሌላው ለመክበር መስራት እና ለመኖር መስራት የሚባለውን ልዩነት በኢትዮጲያ ልናውቀው አልቻልንም፡፡ በሌላው መልኩም የምንማረው እንዲያልፍልን ወይስ እንድናውቅ የሚለውን፡፡ የምናጠናውስ ጉዋደኛ እንዳይበልጠን ወይስ እንድንረዳ እና አዲስ ነገር እንድናውቅ፡፡ በሁሉም መልኩ ከነጮች የአስተሳሰብ እድገት ወደሁዋላ የተጎተትንበት ነገር ካለ፤ ለምን ብለን እራሳችንን መጠየቅ መልካም ይሆናል፡፡ ሰው ውድቀጡን እና የታለውን ካላወቀ መነሳት አይችልም፡፡ ካልሆነም ደጋግሞ ይወድቃል፡፡ አንድ ሰው መስራት ያለበት እንዲከብር ሳይሆን እንዲኖር መሆን በተገባው፤ ከመጀመሪያውም ማለቴ ነው፡፡ ምክናያቱም አገራችን ደሃ ስለሆነች፤ ምን አይነት ሰው በዚህ አገር ላይ ንዋይ አካብቶ ሚሌኒየር ለመሆን ጉጉት እንደሚያድርበት አላውቅም፡፡በእርግጥም በድሃ አገሮች ለመክበር፤ ከባድ የሆነ ፣አስቃቂ የሆነ ፣ጨካኝ የሆነ እና የማይራራ የሙስና አዘቅጥ ውስጥ መግባት እንዳለብን ልብ ማለት ይገባናል፡፡ ይህ ማለት ግን ሁሉንም ቢሌኒየር አያጠቃልልም፡፡ ንዋይም ቀድመው በትክክለኛ መንገድ አፍረተው ለኢንቬስትሜንት የሚዘጋጁ አሉ፡፡ እነሱንም አብረን መጨፍጨፍ አይገባንም፡፡
በአስተሳሰቤ መክበር ነውር ነው ማለቴ እንዳይሆን ልብ በሉ፡፡ ግን ለመክበር የምንጉዋዝበት መንገድ ሁሉ ይህን ያህል አስፈላጊ ነው ወይ ? ነው የእኔ ጥያቄ፡፡ ብዙውን ግዜ የሰውን ልጅ የሚያከብረው አንደኛው እና አስቀያሚው መንገድ ስንጥቅ ትርፍ አትርፎ ከዛም ግብር ያለመክፈል ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የምናየው፤ ብዙ አገር ላይ ሀብት በትንሽ ሰዎች እጅ ላይ ብቻ ተጠራቅሞ የሚገኘው ከዚህ አኩዋያ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ የመንግስትን ካዝና መመዝበር፤ እንደለብ ማዋል በእራሱ አገርን ደሃ እራቁት የሚያደርግ ህግ የለሽ ስርአት መገንባት ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ምግብ ለሰው ልጅ ውድ ሸጦ በምግብ ሽያጭ ትርፋማ ሆኖ ሚሌንየር መሆን እራብ ባለበት አገር እጅግ የሚያሳዝን እና የሚያስለቅስ ነው፡፡ ሰው ወዶ አይደለም ውድ ገዝቶ የሚበላው፡፡ አማራጭ ስለሌለ እና በልቶ ማደር ስለሚገባው ነው፡፡ ወደውስጥ እንግባ ካልን ባህሪያችን እራሱ ፈሪሃ እግዚአብሄር የለውም፡፡ ለነገሩ ፈሪሃ እግዚአብሄር እንዳለው ሁላችንም ስለት እናስገባለን፡፡ ግን እንዴት ገንዘብ እንዳገኘን ካወቅነው፤ ጌታ የነውርን ገንዘብ ይጠየፋል፡፡ መሰዊያውንም ቅረቡ አይልም፡፡ ደግሞም እንዘምራለን አልያም ሰደቃ እናወጣለን፡፡ ይህ ሁሉ ንጽሕ ማንነትን ይጠይቃል፡፡ በጣም የሚገርም ነው፡፡ እምነት የላቸውም ብለን እንደሀጢያተኛ የምንቆጥራቸው ሰዎች ግን ከዚህ የወጡ ናቸው፡፡ ለነገሩ አይምሮ ላለው እግዚአብሄር አብሮን የተወለደ እንጂ ሁዋላ የምናገኘው አይደለም፡፡ ምክናያቱም በውስጣችን ክፉና በጎውን ለይተን የምናውቅ ሆነን በራሱ መፈጠራችን ማስረጃ ነው፡፡
እነዚህ ውስብስብ የሆኑ ነገሮችን ለመፍታት ተቃዋሚ እና ገዢ ፓርቲዎች በጋራ አስተሳሰባቸውን አቀራርበው መነጋገር እና ሁለቱም የህዝቡን የአስተሳሰብ ደረጃ መቃኘት በተገባቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ ነገር ሊፈጠር ቀርቶ ጭራሽ አፈርድሜ ገብቶ እርስ በእርሳቸው ተስፋ በመቁረጥ ይጉዋዙ ይዘዋል፡፡ ህዝቡም እራሱን ማገዝ ያልቻለ ፖለቲከኞችን ደጋፊም ሆኖ ተቃዋሚም ሆነ መጥቀም ችሎታ እንደሌላው እያየነው ነው፡፡ ገዢው ፓርቲን የሚደግፈው፤ በእራሱ እራሱ የባህሪ ችግር፤ እንደእራስወዳድነት እና ስግብግብነት ደግሞም ትእቢት እና እብሪት የማካበት ባህሪ እና ሌላውን እንዳያድግ ዘግቶ የማያዝ ባህሪ በእጅጉ ያካበተ ሆኖአል፡፡ ደግሞ ገዢው ፓርቲን የማይደግፈው፤ ከነአካቴው በገዢው ፓርቲ ተስፋ የቆረጠ እና እድገት የሚባል ነገር የማይታሰብ እንደሆነበት እየታየ ነው፡፡ ይህ ሁለቱም ጉዳይ ግን ሰዎች ከፖለቲከኞች የሚጠብቁት እያንዳንዱ ከእራሱ ማንነት ኪስ እና ጥቅማ ጥቅም እየሆነ በመምጣቱ ነው፡፡ ይህን ግን ፖለቲከኞች ለመለወጥ የሚያደርጉት ነገር የለም፡፡ እንዳውም ይህ ባህሪ በፖለቲከኞችም ውስጥ ያለ የአካባቢው ተለምዶ ያካበተው በመሆኑ ሊለውጡትም የሚገባ መስሎ ሊታያቸው አይችልም፡፡ የመጥፎ አስተሳሰብ ውህደት እና፤ ካልተሰረቀ ካልተስገበገበ፤ ሕገወጥ ካልተሆነ አይከበርም የሚለው አይምሮን የዘጋ አስተሳሰብ ሁላችንም ገሎናል፡፡ አንድም የዳነ አለ ብዬ መገመት ያዳግተኛል፡፡ በአስተሳሰብ ደረጃ ነው የምለው፡፡
ስለዚህ በስልጣን የቆዩትን ያህል ቢቆዩ፤ ስራቸውን ማንም ሰው ሚዛን ላይ ለማስቀመጥ የአስተሳሰብ መመዘኛ አቅም የለውም፡፡ በዚህም የተነሳ በሁሉም ዘመን ተሰሩ የሚባሉትን ስራዎች በማበላሽት ጭራሽ እያንዳንዱን ክልል ታሪክ አልባ የማድረግ ተጽእኖ እየገነባን ሄደናል፡፡ ለምሳሌ ባለፈው አማራው የሰራው ነው ተብሎ ስለሚታመን፤ እስከነገስታቱ ታሪክ ድረስ አፈርድሜ እንዲበላ እና በዘመኑ የነበረውም ሀይማኖት እንዳልሰለጠነ ታይቶ ሲጨፈጨፍ እን ቅርስነት የለለው ትችት እየተተቸ እያየን ነው፡፤ በሌላ መልኩ የድሮውን አፍርሶ አዲስ መገንባት ደግሞ ጥላቻ ጥላችና ስለሚወልድ፤ ዛሬ ደግሞ ወያኔ ሰራ የሚባለውም ነገር ምንም እግንዛቤ ውስጥ እንዳይገባ እየተደረገ ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ፖለቲከኞች አካሄዳቸው በትላቻ የተሞላ፤ ኢትዮፒያንም የምንም ስልጣኔ አገር እንዳትሆን እና ታሪክ አልባ ስትሆን ማየት ግድ ብሎናል፡፡
ሚኒሊክ የሰሩት ከለለ መለስ የሰራው ይኖራል ማለት እንቆቅልሽ ኤየሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ብሄር የፈለገውን ያህል ብሄሩን ቢወድ ባህል እና ታሪክ አልባ በፖለቲከኞቻቸሰው እየሆነ መሄዱን መገንዘብ ግድ ይለዋል፡፡ ፈረንጆች ይህን ልዩነት በአገራቸው ከባድ የሆነ ደም መፋሰስ ያፈሰሱ የተገዳደሉ ቢሆንም፤ ግን በአንዱ ንጉስ ግዜ የተሰራውን ስራ ሌላው ሲመጣ ሊያጠፋው ጥረት አላደረገም፡፡ እንዳውም ሁሉም በቅርስነት ጠብቀውታል፡፤ ተጋለውም ተጣልተውም የሚያዩት መጨረሻ ላይ ውጤቱን ነው እንጂ መበቃቀል አየይደለም፡፡ ስለዚህ የኢትዮጲያን ለየት የሚያደርገው፤ አንዱ የሚመጣው አንዱ የሰራውን አጥፍቶ እራሱን ማሞገስ ስለሆነ ቅርሳችን የመሪዎች ስም ብቻ እንጂ፤ ስራቸው ሆኖ አያውቅም፡፡ ምክናያቱም ሁሉም ዘማችነቱ ቅርስን ማጣፋት፤ ስምን ጀግና ብሎ ማወደስ ላይ ስለሆነ፡፡ ስለዚህ ሚኒሊክ በአንዳንዶች፤ መለስ በሌሎች ገናናነትን ይዞ የአገር ቅርስ ሳይሆን የሰው አማኝ አድርጎን አንድ የሆነች ኢትዮጲያን ሳይሆን የተከፋፈለች ኢትዮጲያን እያስረከቡን ይገኛሉ፡፡ በቸር ባዩሽ
ባዩሽ
የዲሞክራሲው ጥላት የሆነው እራሱ በሕዝብ ውስጥ የሰረጸው ፍርሃት እና በእራስ ያለመተማመን ባህሪያችን ያመታው ጦስ ነው፡፡ ፖለቲከኞችን ለመሦምም ለመሻርም አቅም ኖሮን አያውቅም፡፡ ይህን ያደረገው ድሕነታችንን በስራ የመላቀቅ ሳይሆን በአድርባይነት ብቻ መተዳደር እንደምንችል አድርገን ስለምንገምት ነው፡፡ እራሴ ባህሪዬን ሳልመረምር ማን ላይ ጣትን እቀስራለሁ፡፡ መጀመሪያ እራሴ ብቃቴን መመርመር አለብኝ፡፡
ባዩሽ

አንድ ለአምስት በውስጣችን የሚኖር እንጂ ኢሕአዴግ የመሰረተው አይደለም

አንድ ለአምስት በውስጣችን የሚኖር እንጂ ኢሕአዴግ የመሰረተው አይደለም

ከግሩፕ መሽከርከር ያልወጣ አይምሮ በማህበራዊ ሚዲያ የሚደረገው ልውውጥ የአስተሳሰብ ለውጥ ያመጣል ብሎ መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ እንዳውም ተስፋ አስቆራጭ የሆነ ተጽእና እንዳያመጣ ልብ ማድረግ እራሴ  አለብኝ፡፡ ከፌስ ቡክ ሚዲያ ያተረፍኩትን እና የተጎዳሁትን ለማመዛዘን፡፡ እራሴን መመርመር አለብኝ፡፡ ሁሉም የቴክኖሎጂ ጥቅም ይዞ የሚሄደው የአካባቢውን የአስተሳሰብ እድገት መሰረት በማድረግ እንጂ፤ የሚዲያውን አገልግሎት ከመረዳት አይደለም፡፡ ፌስቡኩን የምጠቀምበት፤ ከእራሴ አስተሳሰብ ጋር ብቻ የሚሄደውን ሰው ለመገናኘት ከሆነ ፌስ ቡክ ለአገራችን ከሚያመጣው እድገት ይልቅ እንቅፋትነቱ ሊጎላ ይችላል፡፡ ማመዛዘን እና ለምን እና እንዴት የሚሉ ጥያቄዎችን ጠይቆ እራስን ለለውጥ ለማዘጋጀት፤ በእኛነታችን ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ለውጥ የዘጋነው ወይም ያላስተዋልነው ይመስላል፡፡  የፌስቡክ ሚዲያ የተናጠል አስተሳሰብን መጀመሪያ ብንስተናገድበት ጀኔራል የሆነውን ችግራችንን ሊገልጽልን አልያም ሊያስታውሰን ይችል ነበር፡፤ አሁን ግን እንደማየው እኔ ማንነትን ሳይሆን እኛነታችንን ያንኑ ጀኔራል ማድረግ እና የማጆሪቲ የምንለውን ነገር ይዘን መጉዋዝ ብቻ ነው፡፡ ለምን እና እንዴት የሚለውን ነገር እራሰችንን ለመጠየቅ እንኩዋን የአፍታ ያህል ምንም አይነት መሪት ሊሆነን አልቻለም፡፡ ይህም ጉዳይ አንተ እኔ ነኝ አንተ እኔ ነሕ እንጂ፤ ማንንም ሰው ወደልዩነት ንግግር ሊያመጣ ሊያወያይ አይችልም፡፡ አስተሳሰቤን የሆነ ነገር ትንሽ ሊያነቃንቀው ሊያፋጨው የሚችል ነገር የኢትዮጲያ ማህበራዊ ሚዲያ ሊፈጥር አይችልም፡፡ ልክ ፖለቲካውም እንደእምነት የሚሄድበት ሁኔታ፤ ነሕ ወይም አይደለህም አይነት ነገር ነው፡፡ መቀበል አለመቀበል ብቻ ነው ያለው ጉዳይ፡፡ ዚህም ሁኔታ ፌስቡክን እንደኢትዮጲያ ማህበራዊ ሚዲያ ለመጠቀም ምን ጠቀመኝ የሚለውን ነገር ሳየው፤ እንዳውም የለለኝን ሹመት የሚያከናንብ በፍርድ የሚያስጠምድ ወይ ውርደት  የሚያመጣ የፍርድ መሳሪያ እንጂ የሰውን እውነተኛ አስተሳሰብ ሊያሳይ የሚችል አይደለም፡፡ ሰው አንድ ነገር ተብሎ ከተፈረጀ፤ ያንኑ ሳየወድ በግድ የማንጸባረቅ ባህሪ በውስጡ ሊገነባ ይችላል፡፡ በፌስ ቡክ፤ ወይ ተቃዋሚ ነሕ አልያም የገዢው ፓርቲ ነሕ፡፡ እንግዲሕ ይህን የሚያስወስን ንግግር ወይም ውይይት የሚጋብዝ ሳይሆን የሚዘጋ እና ነኝ አይደለሁም ብሎ ሰው አንድ ጥግ ይዞ የሚቀመጥበት ብቻ ነው፡፡

       ይህን ሳይገሉ ጎፈሬ የሚያሰኝ ነገር፤ ሁላችንም አስተሳሰባችንን የምንመረምርበት እና ከጊዜው እድገት ጋር ልናስኬደው ቀርቶ የደረስንበትን እንኩዋን እድገት እንድንንደው ያደረገን እውነታ መሰረቱ ይህ ከጥቃቅን ግሩፕ እና ማህበር መደራጀት ጉዳይ አለመውታታችን ነው፡፡ ሁሉም የሚያከብረው የእኔ የሚለውን ብቻ ነው፡፡ በእምነትም ብንሄድ በፖለቲካም ብንሄድ በዘርም ብንሄድ ሰው የእኔ ብሎ የሚያምንበትን ብቻ እንዳይነካበት መከላከል አልያም የተለዬ አዋቂ አድርጎ በማቅረብ ሁሉም በእየራሱ ግሩፕ ብሎ በፈጠረው ነገር ምሽግ ሲሰራ እና ሲደበቅ እናያለን፡፡ እውን ግን ሁላችንም ዲሞክራሲን እንፈልገዋለን ወይ ብሎ እራስን ለመጠየቅ ተቸግረናል፡፡ ስለዚህ እውን እኔ አስተሳሰቤን ወደምፈልገው ደረጃ ወይም ለዘመኑ ይገባዋል ወደሚለው ግሎባል እንዲመች እያደረኩት ነውእን ወይስ በፖለቲካ ፓርቲ በዘር እና በእምነት በስውር አጀንዳ በተተበተበ ምሽግ ውስጥ እየከተትኩት እራሴን እየገደልኩት ነው ብዬ ማሰብ አለብኝ፡፡ አንድ ነገር ግን የተረዳሁት ሰው ሌላው የሆነውን በመሆን ሌላውን ሊያስደስት ይችል ይሆናል እንጂ ለእራሱ ግን ሀዘን ነው፡፡

በዚህም በዛም የተረዳሁት ነገር ቢኖር ኢትዮጲያ ላይ ችግራችን ይሆናል ብዬ የገመትኩት፤ በማህበር የተቃቀፈ ማህበራዊ ህይወት የአስተሳሰብ እድገታችንን የገደለው ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡ በማህበር መተቃቀፍ ሳይሰሩ የሰሩ፣ ሳያውቁ አዋቂ፣ ሳይፋቀሩ ተፈቃሪ እና እርስ በእርስ ነውርን መደባበቅ ብቻ ይሆናል፡፡ እከክልኝ ልከክልህ የሆነ በትንንሽ ሰዎች የታመገ ቡድን ከጥንት ጀምሮ በመመስረት የምንኖር መሆናችን እራሳችን መመርመር አለብን፡፡ ሁሉም የምናደርገው የማህበራዊ ሕይወት ተብዬ ማህበር የማንነታችን መደበቂያ ነው፡፤ ሌላው ደግሞ ከሌላው ጋር ካልተቀላቀለ ምንግዜም ተከላካይ እንጂ አጥቂ ሊሆን አይችልም፡፡ ለምሳሌ ብዙ ሰዎች፤ ኢሕአዴግን አንድ ለአምስት መስርቶ ብለው ይተቻሉ፡፡ ለነገሩ ድሮም እኛም አንድ ለአምስት ነን፡፡ ከዛ በላይ እንደእውነቱ ተግባብተን መጉዋዝ አንችልም፡፡ ትርፉ መጩዋጩዋህ ብቻ ነው፡፡ ግን እኔ የምለው ኢህአዴግ ይህንን አንድ ለአምስት የሆነ ባህል ሊጠቀምበት የሚጥር ነው፡፡  አሁንም ሳይ አንድ ለአምስት በፌስቡክም ውስጥ መሰዳደቢያ መወራረጃ፤ መመሰጋገኛ ሆኖ የሰውን የአስተሳሰብ እድገት እያጨደው እየገደለው ነው፡፡ ይህንን ሁሉም አሜን ብሎ የተቀበለው ከጥንት ጀምሮ የለመድነው፤ በግሩፕ አለቃ መነዳትን ነው፡፡ እኔ ለአስተሳሰቤ አለቃ እንዲኖረኝ አልፈልግም፡፡ ግን የምፈልገው ነገር ቢኖር እንዴት የሌላውንም አስተሳሰብ ልጋራ የሚለው ላይ መሆን አለበት፡፡ ኢትዮጲያ ልትለወጥ ትችላላች ብዬ የምገምተው ይህ የግሩፕ አይነት ማህበር ከነአካቴው ጠፍቶ ነገሮችን በስፋት ለማየት ስንዘጋጅ ብቻ ነው፡፡ ካልሆነ በግሩፕ የሚታቀፉ ማህበራት እንኩዋን ለውጥ ሊያመጡልን ቀርቶ ለውጥ እንኩዋን እንደሚያስፈልጉን ሊያሳየን የማይችል እውር አድርጎ ያኖረን፤ ዛሬም እያኖረን ነገም የምንኖርበት አስተሳሰብን የሚያደቅ ቫይረስ ተሸክመን እንደምንኖር ነው፡፡

በኢትዮጲያ ማንኛውም ፖለቲከኛ የሚያደርገው የሚፈጽመው ህዝብ የሚፈልገውን እና አዳብት ያደረገውን ነው፡፡ የግሩፕ መሪ የለለው ማንም በኢትዮጲያ ውስጥ ሊኖር አይችልም፡፤ ይህንንም የግሩፕ ማህበር ዘወትር በማንኛውም ማህበራዊ መሰህበር መስርተን የምንጠቀምበት ነው፡፡ ለምሳሌ ከቤተሰብ ማህበር፣ የአካባቢ ማህበር ለምሳላ የአምባሰል የቦረና የአገው የጎንደር የአክሱም የአዳዋ…….እያለ ከድሮ ጀምሮ በመረዳጃ ስም ያለ እና የተለመደ ያደረጉ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ኢህአዴግ ሳይፈጠር ጀምሮ ያለ ነበር፡፡ በቤተክርስቲያንም ጥቃቅን ማህበር አለ፡፡ እያለ ብዙ ነገር መሰረታችን በጥቃቅን ማህበር ሲጉዋዝ ሲቀራረብ ሲረዳዳ የነበረ ነው፡፡ ማህበር የለለው ሰው መኖር የሚቸገርበት ሁኔታ ብዙ አለ፡፡ ስለዚህ ፖለቲከኞች የተጉዋዙት የህዝቡን የልብ ትርታ እና ፍላጎት በማስተዋል እንጂ ዝም ብለው አይደለም፡፡ የጥቅም ነገር ሲመጣ ነው አንዱ ተስማሚ ሌላው የማይስማማ የሚሆነው፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ ልንነጋገራቸው የሚገባ ነገሮች እያሉ እኛ ግን አሁንም የምንነጋገረው የጣለንን ነገር ልክ እንዳነሳን ሆነን ነው፡፡ ይህ አይመችም፡፡ ሰው መቼም ሌላን አካባቢም ሲያይ ከዛም የሚማረው ነገር ይኖራል እና፡፡ ለመማር ግን መጀመሪያ ሰው እማያውቀው እንዳለ መረዳት አለበት፡፡ እምንማረው ፈተና ለማለፍ ሳይሆን፤ እንዴት መኖር እንዳለብን ለማወቅ መሆን አለበት፡፡
ባዩሽ