Freitag, 12. September 2014

„ከየትም አምጭው ዶቄቱን ፍጭው“



ከየትም አምጭው ዶቄቱን ፍጭው“

 @ Freedom Forethio ላንተ በግል ኮሜንት ላለመስጠት ወስኛለሁ፡፡ ምክናያቱም የግንዛቤን ጉድለት ስላየሁበት በሰፊው እሰው ማሀል ብንለዋወጥ ይሻላል በማለት ነው፡፡ መቼም በእኔ በኩል ያመንኩበት ይህን ነው፡፡ ምንአልባት ይህ ባህረዬ ለብዙዎች ያልተለመደ  ሊሆን ይችላል፡፡ ሀሜት እና የጉዋዳ ወሬን በጣም እጠላለሁ፡፡ የጉዋዳ ወሬ ብዙውን ግዜ የሚፈጠሩት ለጥፋት ይቅርታ መጠየቅ ባለመለመዱ ነው፡፡ አንተ ስሜቴን ለመጉዳት ጥረት አድርገሃል፡፡ ግን በስሜቴ እንዳልወድቅ ውስጤ በእግዚአብሄር ብርታት ውትድርና የሰለጠነ ይመስለኛል፡፡ ውጊያዎችን ደግሞ ለመመከት እግዚአብሄር እንደሚያበረታኝ አልጠራጠርም፡፡ ለዚህም ከልቤ ነገሮችን አውጥቼ ለመናገር እወዳለሁ፡፡ ከአፍ የሚወጣውን በልብ ፊልተር ማጽዳት ማጥለል እመክራለሁ፡፡ ለማንኛውም ደጋግሜ እንደምለው፤ የማቀርበው አስተያየት ሁሉ፤ አንተን የፈረድክብኝን  ወዳጄን @ Freedom Forethio ወይም ሌሎችን ወዳጅ አንባቢዎቼን በመብለጥ አይደለም፡፡ ግን የማቀርበው የእራሴን አስተሳሰብ ማውጣት ትክክል መሆኑን ስላመንኩበት ነው፡፡ ያሰብኩትን መደበቅ ለማንኛችንም አይጠቅምም እና፡፡ የማይመቸውም ቢኖር የአንዱ አስተሳሰብ ከሌላው የተለዬ መሆኑን እንድናውቅ እና በጋራ አስተሳሰብ ወደዲሞክራሲ ለመሄድ ልምምድ እንዲሆነን ነው፡፡
ለነገሩ  አንተ አቁዋምህ የወያኔ ይሁን የተቃዋሚ ሳላውቅ ስለግንዛቤ በአንተ አስተያየት ላይ ኮሜንት  መስጠት እቆጠባለሁ፡፡ ለነገሩ የተጨበጠ ነገርም አታቀርብም፡፡  እኔን ዝም በይ ከማለት፤ ራስህ ዝም ብትል ይሻላል፡፡ ሰው ላይ ትፈርዳለህ በጣም ሁዋላ ቀር እና ችኩል ባህሪ አለህ፡፡ ይመስለኛል እኔን ከታላላቅ የፖለቲካ ሰዎች እኩል ተርታ ማሰለፍ ፈልገሃል፡፡ ይህ ነው ትልቁ ስህተት፡፡ ሕዝብን በሙሉ ፖለቲከኛ ማድረግ የሚፈልግ ባህል ፖለቲከኞችን ቁም ነገር እንዳይሰሩ እና ህዝብም ወደእራሱ መብት ጥያቄ እንዳይመጣ ያደርጋል፡፡ መብትን ለመጠየቅ የእርዮተ አለም ደጋፊ መሆን የለብንም፡፡  ስለዚህ ከእኔ የእርዮተ አለም ፖለቲካ አትጠብቅ፡፡ እውቀቱም የለኝም፤ ደግሞም የማውቀውም የፖለቲካ ፓርቲ የለም፡፡ ለምን መሰለህ ሁሉም ልባቸው እንደአንተው የተቆዘመ ነው፡፡  በሁሉም ላይም የከረረ መጥፎ ነገር መጻፍም የማልፈልገው፤  የእርዮተአለማቸው እውቀት ስለለለኝ ነው፡፡ በወያኔ ዘመን አልተመቸኝም ማለት ሌላ የሚመቸኝ አገኛለሁ ማለት አይደለም፡፡ ግን ደግሞ እሚመጣውም ላይ ጥርጣሬ ቢኖረኝም፤ ገዢው ፓርቲ እንዳው እንደቤተክርስቲያን ዘላለም ቆሞ ይኑር ለማለትም አልደፍርም፡፡ ገዢወቅ ፓርቲ እግዚአብሄር አይደለም፡፡ ይህ የዲሞክራሲ ባህሪ በጭራሽ አይደለም፡፡ በኢትዮጲያ ገዢው ፓርቲ ከያዘ እንደማይለቅ እኮ እናውቀዋለን፤ ለምደነዋል፡፡ ደግሞ ተቃዋሚው ገዢውን ፓርቲ እንዳለ ድምጥማጡን ካላጠፋ ለመቀራረብ ጥረቱ ደካማ ነው፡፡ ታዲያ ወያኔ ኢሕአዴግ ከምጠፋ ይዠ ልጥፋ ቢል ትክክል አይደለም እንዴ?
ሌላው እኔ የማምንበት ነገር አለ፡፡ እራሴ የማምነው፤ ሁሉንም ማለት ኮሚኒስትም ይሁን ካፒታሊስት አልያም ኢምፐሪያሊስት ደግሞም ሶሻሊስት ሁሉም ፓርቲያቸውን ይዘው ኢትዮጲያ ውስጥ መኖር አለባቸው ነው የምለው፡፡ ሁሉም በጠቅላላው የሚመቸንም የማይመቸንም፡፡ ይህ ነው የዘመኑ አካሄያድ፡፡ እኛ እኮ እንደሕዝብ በውነት ፖለቲከኞችን ንቀናል፡፡ እስኪ በናታችሁ ከማንኛቸው ነው ትምህርት የምንቀስመው?  ምንድን ነው እሱ፤ ሁሉም ካልሆነለት መተው ነው ያለበት፡፡ በወያኔም ሆነ ተቃዋሚ ሰው አያምኑም፡፡ የእነሱ ሁሉ እርዮተአለም የሚሽከረከረው በአካባቢያቸው በሚቀርባቸው በሚያምኑት ሰው ስለሆነ ከፖለቲከኛነት ወደአምባገነንነት  የሚሸጋገር ባህሪ ይይዛሉ፡፡  በክብ ያለ፤ በሚያምኑት ብቻ የተወሰነ ፓርቲ አምባገነን ለምን አይሆንም፡፡ የሰው ባህሪ እኮ እራሰን ወዳድ ነው፡፡ ኢትዮጲያ እስከአሁን ድረስ ያለው የፖለቲካ ባህል፤ ተቃዋሚዎችን  እንዳለ ሁሉንም ደምስሶ  ብቸኛ ገዢ መሆን ነው፡፡ ይህ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ባህል እውነት የሚመጣውም ይለውጠዋል ለማለት አልደፍርም፡፡
ዘወትር የሚያነጋግረው ጎዳይ ደግሞ እንዳንተው አሁን እኔን እንደወነጀልከኝ ወያኔ ነሽ እንዳልከው የማፈን ስራ ነው፡፡ አንድ ሰው እኮ ወያኔም ቢሆን ወደአንተ ፓርቲ የሚያመጣውን ስራ መስራት ነው እንጂ ያለብህ ልታጠፋ የማትችለውን ነገር ለማጥፋት መሞከሩ ድካም ነው፡፡ አስተሳሰብን እንጂ ማጥፋት ሰውን አይደለም፡፡ አቶ መለስ እኮ ሞተዋል፡፡ ግን ያለው አስተሳሰባቸው  አላማቸው ነው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው እኮ ታስረዋል፤ የታሰረ ሰው አላማውን ለመተግበር አይችልም፡፡ ግን አቶ አንዳርጋቸውም አስተሳሰባቸውን  አላማቸውን እውጭ ትተው ነው ወደእስር የወረዱት ፡፡ እንደአቶ መለስ አስተሳሰባቸውን ትተው ወደመቃብር እንደወረዱት፡፡ እና ሰው ዝም ብሎ እሰው ጋር ይታገላል፡፡ ምን ትታገለዋለሕ የሁሉም ታዋቂ ሰዎች ወይም የፖለቲካ ሰዎች፤ አስተሳሰባቸውን  እህዝብ ውስጥ ዘርተውታል፡፡ ዘር አላቸው፡፡ የሚመቸውን ሰው ሁሉ ይዞ ደግሞ ያናፍሰዋል፡፡ ስለዚህ ትግል መሆን ያለበት አስተሳሰብን በአስተሳሰብ ማጥፋት ነው እንጂ እንዳው ለዘመናት ሰው በመክሰስ አይደለም፡፡ የሞተ ሰው አይነሳም፡፡ የዘሩ ባህሪው ግን ህያውነት ይኖረዋል፡፡ ይህ በሁሉም ያልተለወጠ የፖለቲካ ባህሪ ተይዞ አንተ ወያኔ ነህ አንተ ተቃዋሚ ነሕ እየተባባለ በሰው ክስ ብቻ የተወሰነ እድገት የለለው ነገር ይሆናል፡፡ እንክርዳድ እና ስንዴውን እኩል በኩል የሆነበት መሬት ላይ መሬቱን ብትወቅሰው ዋጋ የለውም፡፡ መጀመሪያ የምትዘራው ስንዴ እንክርዳድ የማያበቅልበትን ወይም የማይበዛበትን ሳይንስ መማር እና ማወቅ ነው፡፡ የፖለቲካ ሳይንስም ታላላቆቹ እንዳይሰሩ የምናደርጋቸው አገርን በማፍቀር፣ እምነትን በማፍቀር ፣ በእረስ ወዳድነት፣ በድህነታችን የተነሳ ለውጥን የምንመኝ  ሰዎች ነን፡፡ በጋራ እንዳናስብ ተጠቃሚው እና ተጨጋሪው ክፍል እሚቀራርበው አላገኘም፡፡ ታዲያ ወያኔን የሚጠላው ህዝብ  ብዙ ነው ከተባለ ለምንድን ነው ስልጣን ላይ ብዙ እንዲቆይ የሆነው፡፡ የሚፈልገውም አካል እኮ ስላለ ነው፡፡ በዘር፣ ብር በመውደድ፣ እራስን በመውደደም……በለውም ወይም በአላማ ፤  የሚወደው ተሰልፎ አቅፎ ደግፎ የያዘው አካል አለ፡፡ ስለዚህ  ተቃዋሚንም የሚፈልግ እውነተኛ አካል አለ፡፡ ደግሞ በወያኔ የተበደለ አለ፡፡ ግብር መክፈል የማይፈልግ አለ፡፡ ለአገር ተቆርቁሮ ተቃዋሚ በነፍስ ድረስ የሚል አለ፡፡ ስራ በማጣት ተቃዋሚ ስራ ይሰጠኛል የሚል ተስፋኛ አለ፡፡ እርግጥ ነው፤ ለገዢው ፓርቲ ግልጥ ለማድረግ፤ ገዢው ፓርቲን የሚወደው አካል ምንም አይነት የኢኮኖሚ ችግር የለለው እንደሚሆን ይታወቃል፡፡ በቃ የፖለቲካ ባህል በአለም ላይ እንዲህ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ የሚደገፈው ምንግዜም በምቾት ነው፡፤ ተቃዋሚን የሚደግፈው በገዢው ፓርቲ ዘመን ያልቀናው ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነበት ምክናያት የኢትዮጲያ ህዝብ የፖለቲካ ግንዛቤውን ለማሳደግ፤ ሌላውም ወገኔ ነው ይብላ አልያም ወገኔ ነው ለምን ይራባል የሚል የፖለቲካ ንቃተ ህሊና የሚሰጠው የፖለቲካ ሰዎች አግኝቶ አያውቅም፡፡ ስለዚህ በኢሕአዴግ ዘመን የጠገበው ላልጠገበው ያስባል ብዬ አልገምትም፡፡ እንዳውም የተቸገረው ህዝብ እና ገዢው ፓርቲ የሚገናኝበትን ድልድይ አፍራሽ የሚሆነው በገዢው ፓርቲ የተመቸው አካል ነው፡፡ ብቸኛ ተጠቃሚ መሆን በኢትዮጲያ ያለ ባህል ነው፡፡ ሁለት አይነት አገዛዝ አለ፤ አንዱ ህዝብን አደንቁሮ መግዛት፤ ሌላው ህዝብን አንቅቶ መግዛት፡፡ ኢኮኖሚው በላሸቀበት፤ ድህነት በተንሰራራበት አገር ህዝብን አደንቁሮ መግዛት አዋጪ ነው፡፡ ለዚህም ነው አንተ ተቃዋሚ ነሕ አንተ ደጋፊ ነሕ እየተባለ የሚነዛው፡፡ በውጭ አገር ያገኘሁት ልምድ፤ ገዢው ፓርቲ ዘወትር ትኩረቱ ባልተመቸው ህዝብ ላይ ነው፡፡ እኛ አገር ግን ገዢው ፓርቲ ለተመቸው ሰው መቆም ስድ መልቀቅ እንደልቡ ማድረግ ነው፡፡ ድሮም ለንጉሱ የቀረበ እንደልቡ ነው፡፡ ለኢሰፓ/ለደርግ የቀረበ እንደልቡ ነው፡፡ ዛሬም ለወያኔ ኢሕአዴግ የቀረበ እንደልቡ ነው፡፡ ነገስ ሌላ የሚሆንበት ምን የአስተሳሰብ ለውጥ ምን የባህሪ ለውጥ መጣ፡፡ „ከየትም አምጭው ዱቄቱን ፍጭው“፡፡ በቸር ባዩሽ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen