ገዢው ፓርቲም ተቃዋሚን ካሳደደ፤ እረዳቱን እንደተቃወመ ይቁጠረው
ተከፋንም ደላንም መቼም ኢትዮጲያ የምትባልን አገር ሁሉም ጎጥ በአንድነት ተረክበናታል፡፡ ዛሬም ሀሳባችን በክፋት፣ በብቀላ እና በመደናገር ቢገኝም ኢትዮጲያ የሚል ስም እንዳለ ነው፡፡ የተለወጠው በባንዲራችን አረንጉዋዴ ቢጫ ቀይ በሚለው ላይ የተቀመጠው አንበሳ በሌላ ተቀይሮአል፡፡ እኔ ለእራሴ አሮጊት ሆኘ ነው መሰል ከአንበሳው መላቀቅ አቅቶኛል፡፡ ሰው ሲበስል፤ ካለፈው ልጅነቱ ይመለሳል እና፡፡ አንበሳውን ሳስታውስ በዚህ መልኩ እስኪ ልየው፡፡ ይህ ማለት ግን ያለፈውን ዘመን አገዛዝ ሁሉ እደግፋለሁ ማለት አይደለም፡፡ አይዞአችሁ እኔ የባላባት ዘር ሳልሆን የገበሬ ዘር ነኝ፡፡ ስለዚህ አንበሳውን ስል ያለፈው ስርአቱ ደጋፊ አልያም የተለየች ተጠቃሚ እንዳታደርጉኝ፡፡ በቃ እንደ 90% ኢትዮጲያዊ ነበርኩ፡፡ መቸም የገበሬን ሕይወት ታቁታላችሁ፡፡ ያመረታትን ይዞ ወደከተማ የሚሮጥ እንጂ ለእኔ የሚል አልነበረም፡፡ ልጆቹንም የሚያስተምር የነበረው ስንቅ በመቁዋጠር ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ የገበሬው ልጅ የተማረ አልነበረም፡፡ ያለፈው አገዛዝ ሁሉ በኮሎኒ ወረራ ላይ በብዛት ያተኮረ ስለነበረ የውስጥ ችግሮቻችን ላይ ብዙም ለማተኮር ግዜ የነበረው ስርአት አልነበረም፡፡ በዚህም የተነሳ ሁሉም ክፍለሀገር የልማት እድገት አላሳየም፡፡ አገሪቱ በጥቂት ባላባቶች እጅ የወደቀች ያደረጋትም ችግር ነጮች በአፍሪካ ላይ ያደረጉት ትኩረት የህዝቡን ስሜት የሰረቀ ነበር፡፡ ሁኔታውም ሁሉ በጋራ ጥቅም ላይ ያተኮረ አንድነት ሳይሆን የነበረን አንድነታችን በኮሎኒ እጅ ላለመውደቅ ነበር፡፡ እዚህ ላይ እኔ እንደሚመስለኝ፤ ማንኛውም ጎጥ ኮሎኒን የተቀበለ አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጲያም ዝንዋ በአለም ላይ ያንሰራራው የዚህ አንድነት ውጤት ነበር፡፡ አንድነት ጠላትን ለማባረር ብቻ ሳይሆን አብሮ ተጋብቶ ተዋልዶ ለመኖርም ከማንኛውም ዘር የተዋለደው ዛሬ ሊመሰክር ይችላል፡፡ ተጋብተናል በሞትም ሀዘንን ተካፍለናል፡፡ ዛሬ ግን ብዙ ነገር መልኩን እየቀየረ መጥቶአል፡፡ ኮሎኒ ለጊዜው ባለመኖሩ፤ የጋራ ጠላት የለንም፡፡ ስለዚህ ዛሬ ሁሉም ትኩረት የሰጠው ከጥቅም ጋር በመሆኑ፤ በተለያየው መልኩ እኔ ወደሚለው ፈተና ተሸጋግረናል፡፡ የመጀመሪው እኔ የእኔ ዘር የቅደም እና ይብላ የሚለው እና ሌላውን የሚኮንን አባዜ ተከስቶብናል፡፡ ይህ አይምሮአችንን ፈተና ጥሎብናል፡፡ ግን የሚገርመው የእኔ ጎጥ ብቻ የሚለውም ደግሞ ሲሰራ እጅግም አይታይም፤ ምክናያቱም፤ እሱም የእኔ የመንደር ልጅ በማለት ጭራሽ እየተጣበበ ይተካከክ ይዞአል፡፡ እሱም አልሰራም እና የእኔ ቤተሰቤ ብቻ ወደሚለው ቅልጥ ያለ እራስን ወዳድነት ገብቶ በሙስና እና ሀብት በማካበት አባዜ ውስጥ ገብተናል፡፡ እንግዲሕ ለአንድነት የጋራ ጠላት ካስፈለገ፤ ጠላት ስጠን ብለን መጸለዩ ይሻላል ወይስ እንዳው የውስጥ ችግራችንን የሚፈታ ጥሩ ፖለቲከኞች ስጠን ማለት፡፡ ልብ እንበል፤ እስኪ ባለፈው ዘመን የተሸለ ተጠቅሙአል የሚል የአንድ ዘር ስም ጥሩ፡፡ ይህን መልስ ለመስጠት መጀመሪያ የጎጃምን፤ የወሎን አልያም ሰሜን ሸዋን እና ጎንደርን ሄዶ መጎብኘት ነው፡፡ እስኪ እንግዲህ አንድ ዘር ብቻውን መጠቀሙን ከትግራይ ህዝብ ከኦሮሞ ህዝብ ከደቡቡ ህዝብ ማወዳደር ነው፡፡ እኔ ዞሬ ኢትዮጲያን አይቻለሁ፡፡ ግን ባለፈው ስርአት፤ በንጉሱ ስርአት የተለዬ ጥቅም ያገኘ ዘር አላየሁም፡፡ ምንአልባት አንዳንድ ሰው ከሁሉም ክፍለሃገር ሊኖር ይችላል፡፡ ይህንን ለማየት ሁሉም ወጣት ሽንጡን ገትሮ ፈረንጅ እንደሚያደርገው፤ ሁሉንም ክልል እየሄዱ መጎብኘት ነው፡፡ በጥቂት ባላባቶች የተነሳ ህዝብ መኮነን የለበትም፡፡ በአንድነታችንም የተጠቀምንበትንም ትርፉን አብሮነትን ሰውነትን እምነትን ማየት መልካም ነው፡፡ ሰው ከሰው እንጂ የሚኖረው ከአውሬ አይደለም፡፡ ባለፈው ስርአት ሁሉ፤ ሁሉም ጎጥ ኢትዮጲያዊ ተብሎ አውሬነትን ሳይሆን ሰውነትን አሳይቶአል፡፡ ዛሬ ፈረንጆች የደረሱበትን አብሮነት እኛ ገና ጥንት አብረን በመኖር አሳይተነዋል፡፡ በዚህ ግን አንድ ዘር ብቻ ተጠቅሞአል የሚል እግዚአብሄር የለሽ እንዳይሆን ጎራ ብሎ ሄዶ ይጎብኝ፡፡ እንዳው ቂጥን ጠፍጥፎ ተቀምጦ የወሬኛ አዳማጭ ሆኖ ዘርን ከመኮነን ይውጣ፡፡
ያም ሆነ ይህ ዛሬ የውስጥ ችግራችን አይናችን ላይ ፈጦ እንደድሮው መኖር አልፈልግም ማለት ሁሉም የያዘ ይመስላል፡፡ እንዲርበኝ አልፈልግም፣ መማር እፈልጋለሁ፣ መታከምም ይገባኛል፣ እራሴን መኖር እፈልጋለሁ፣ አስተሳሰቤን በነጻ መስጠት እፈልጋለሁ፣ በረንዳ ላይ መተኛት አልፈልግም፣ የምፈልገውን ስርአት የሚተገብር የፖለቲካ ፓርቲ እፈልጋለሁ…… በማለት ሁሉም ክልል የሰው ልጅ ለሚገባው ጥቅም እና እኩልነት ተነስቶአል፡፡ ግን እዚህ ላይ ደግሞ እንደድሮው ላለመኖር ትክክል ቢሆንም፤ የድሮውን ግን መጥፎ መሆኑን ለማስረዳት አንድ ዘር ወይም አንድ ሀይማኖት ላይ አተኩሮ ጠላት አድርጎ ማቅረብ በጭራሽ የተሻሻለ የፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይሆን እንደገና ወደጋርዪሽ ህብረተሰብ ግዜ የሚመልስ ይሆናል፡፡ አያችሁ አሁንም አንድ ዘርን ብቻ አተኩረን አማራው ነው ትግሬው ነው እያልን የምንኮንነው፤ ያው የነበረን አንድ የሚያደርገን የጋራ ጥላት ፈላጊ ያደርገናል፡፡ እስኪ አንድ ሰው ይንገረኝ መላው የአማራ ህዝብ ኢትዮጲያን በድሎ ከሆነ፤ ደግሞም እስኪ መላው ትግሬ ኢትዮጲያን ሕዝብ በድሎ ከሆነ፡፡ ሰው በተፈጥሮው ሁሉም በዳይ ወይም ተበዳይ አይደለም፡፡ በትግሬ ሰው የተበደለ ይኖራል የተጠቀመ ይኖራል፡፡ በሌላውም ዘር ውስጥ ባለ ሰው፡፡ ችግሩ አሁን የሚመስለኝ የውስጥ ችግራችንን የሚፈታ ፖለቲከኛ አለማግኘታችን ይመስለኛል፡፡ ግን እንደሚመስለኝ ሁሉም ለመፍታት በጥረት ላይ ናቸው ብዬ እገምታለሁ፡፡ መጣር ግን መሳካት ማለት አይደለም፡፡ ሊሳካም ላይሳካም ይችላል፡፡ ችግሩን እንደመፍታት ዘርን ጠላት አድርጎ የሚያቀርብ ፖለቲካ ማካሄያድ እንዳውም ለፓርቲው ተጨማሪ ሸክም መፍጠር ከመሆኑ ባሻገር የሚያመጣላት ትርፍ የለም፡፡ አለም ከእንግዲህ የምትደርሰው በአለም ፖለቲከኞች እይታ እንጂ፤ በሰፈር ፖለቲካ እንዳልሆነ እያየነው ነው፡፡ ስለዚህ እኩል ከአለም ጋር መራመድ ያቃተው በተፈለገ ግዜ ከፍርድ አያመልጥም፡፡ የድሮው ስርአት ለዛሬው አይሆንም፡፡ ድሮ ተበድያለሁ እና ዛሬ ልበድል ማለትም ሁዋላቀርነት ነው፡፡ ጥሩው እንዳውም በዳይ እና ተበዳይን ይቅር የሚያባብል ፖለቲከኛ እንጂ፤ ወደብቀላ የሚጎትት ፖለቲከኛ ሳይሆን የሁዋላ ሁዋላ ወንጀለኛ ይሆናል፡፡ በቂ መቃለል የሚገባው ችግር እያለ፤ ጠላትህ ዘር ነው ብሎ ማቅረብ ምንም የሚጠቅመው ነገር የለም፡፡ ለተቃዋሚም ሆነ በስልጣን ያለው ገዢ ፓርቲ ሸክም ማብዛት እንዳይሆንባቸው ልብ የበሉ፡፡ ኢትዮጲያ ብዙ መንገድ ተጉዛለች፤ በእልክ እንደገና ወደጉዞዋ መጀመሪያ እንዳትመልሱዋት ፖለቲከኞች ሁሉ አይናችሁን ክፈቱ፡፡ ህዝብ የሚፈልገው ዳቦ የሚገዛለትን ስራ እንጂ መከፋፈልን አይደለም፡፡ ሕዝብ የሚፈልገው በእኩልነት፣ ካለአድሎ ካለማንአለብኝነት፤ ካለእራስ ወዳድነት የሚመራውን የፖለቲካ ፓርቲ በዲሞክራሲ መምረጥእንጂ ዝም በል እኔ አውቅልሃለሁ የሚለውን አይደለም፡፡ ንጉስ እንዲሰጠን እግዚአብሄርን ለምነናል፡፡ እሱም ዳዊትን ትተን እሳኦል እጅ ላይ ወድቀናል፡፡ ሳኦል ጨካኝ ትእቢተኛ እና ደግሞም እግዚአብሄር የላከለትን ዳዊትን ያሳደደ ነው፡፡ እንግዲህ በስልጣን ላይ የገባ መሪ ሁሉ፤ የሳኦልን ባህሪ እንደሚይዝ እመኑ፡፡ ያስራሃል፣ ያሰድድሃል፣ ደግሞም በትእቢት እና በእብሪት ይወጠራል፡፡ ይህን ብትጥለውም የሚመጣውም ያው ነው፡፡ ሰውእግዚአብሄርንም የሰው መሪ ስጠን ሲባል ፤ ይህን ሁሉ እንደሚፈጽምብን ተናግሮአል፡፡ መንፈሱ ዘሩ የሰው መሪ ይህ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲም ተቃዋሚን ካሳደደ፤ እረዳቱን እንደተቃወመ ይቁጠረው፡፡ ተቃዋሚም ምን ቢለፋ ካለዘመን አይሆንም፡፡ ዘመን ግን በሁሉም ላይ ደግሞም ለሁሉም ይመጣል፡፡ መልካም ለኢትዮጲያ፤ መልካም ለአለም፡፡ እውነት ማሸነፉዋን አንዘንጋ፤ ዘሩዋ የእግዚአብሄር ነውእና፡፡
ባዩሽ

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen