የበይ እና የተበይ ተመልካች እንዳልሆን
ፖለቲካን ምፍተሄ አምጪ ለማድረግ ያልተቻለበት ምክናያት፤ ፖለቲከኞች ውስጥ 1. እራስን ወዳድ እና ፖለቲካን ድልድይ አድርጎ መጠቀም የሚፈልግ 2. ባለፈው ዘመን መበደልን አይምሮው ያልቻለለት እና መበቀል የሚፈልግ 3. እውነተኛ አገርን ህዝብን ሊለውጥ የሚፈልግ ህልመኛ ወይም ባለእራእይ ይሆናል፡፡ እነዚህ ገዢውንም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲ የሚባሉትን በሙሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡ ችግሩ ግን አንዱ ፓርቲ ሳይሆን፤ በሁሉም ውስጥ የሚሳተፈው ፖለቲከኛ አንዱ በአንዱ እጅ የወደቀ በመሆኑ ወይም አንዱ ፖለቲከኛ ሌላውን ፖለቲከኛ ስለሚፈራ ነገሮች ውስብስብ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ብቻ ያም ሆነ ይህ እሁሉም ውስጥ በደንብ አገሩን ህዝቡን የሚያፈቅር እንዳለ ጥርጥር የለውም፡፡ ግና፤ ችግሩ እኔ እንደሚመስለኝ፤ የኢትዮጲያ ለውጥ ሁልግዜ በመሪዎች ወይም በፓርቲዎች ላይ የተመሰረተ እንጂ፤ ችግሩ ላይ ባለመሆኑ፤ ረጅም ግዜ የሚያታግል ይሆናል፡፡ ሁሉም ትኩረቱ እንቢተኛው ላይ እንጂ እሱ እራሱ ደግሞ እምቢተኛ እንደሆነ የመረዳት አቅሙ በረጅም ግዜ በወሰደው ተስፋ አስቆራጭ ትግል አመለካከቱን የተወሰደበት ይመስላል፡፡ እኔ ነኝ የታገልኩበት ማለት የሚያመጣው ሁልግዜ እችግራችን ላይ ሳይሆን የምናተኩረው ስልጣን ላይ ይሆናል፡፡ አንድ ፓርቲ ካለህዝብ ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፡፡ እንድ ፓርቲ መጥፎ ይሁን ጥሩ የሚታወቀው ከስልጣን ሲወርድ እየሆነ የመጣበት ኢትዮጲያ በሁሉም ዘመን ተቃዋሚ የሚባለው የፖለቲካ ሰው በሙሉ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው አልፈዋል፡፡ ለፖለቲ ካ ሰዎች ሲነሱ አላማ እና መሰረት አለን ቢሉም ፤ ሁሉም ያለፈበት፤ ስንመለከተው አምባገነን ነው የሚለውን በስልጣን ያለውን ፓርቲ ለመጣል ስለሆነ ከፍተኛ የሆነ ጥላቻ አንግቦ ይነሳል እንጂ መሰረታዊ ለውጥ የሚሆንበትን ነገር አንድም ፓርቲ ሲያተኩርበት አይቼ አላውቅም፡፡ ይህ የፖለቲካ ፍጥጫ ብዙውን ግዜ በጥላቻ የተሞላ የሚያደርገው ወይም የሚጋብዘው ዘወትር በስልጣን ላይ የሚገኘው ገዢው አካል ነው፡፡ ስናስታውስ ሁሉም የተተካካው በጥላቻ መሆኑን ማስታወስ የሚገባን ሁሉም የኢትዮጲያ መሪዎች ወደው ከስልጣን ወርደው ወይም አካፍለው አያውቁም፡፡ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ርዮተአለም ቢኖረውም ግን የሚመስለኝ፤ የእራሳቸው እርዮተአለምን መተግበር እንዳቃታቸው እና ዞረውም እርስበእርሳቸው እንኩዋን ሲበላሉ እናስተውላለን፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክናያት በእኔ ግምት መነሻቸው ጥላቻ እንጂ አንድም ርዮተ አለም ስላልነበረ ነው፡፡ ከጥላቻ በሁዋላ የሚመጣ ርዮተአለም ለመተግበር ያስቸግራል፡፡ ስለዚህ 7 ሆነው የጀመሩት የወያኔ ትግል ሰፋ ያለ ተከታይ ማፍራቱ ይታወቃል፡፡ ይህ የሆነበት ምክናያት ደርግ ሕዝቡን አሰላችቶት ስለነበረ እየኮበለለ እንዲሄድ እና የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው የሚል አመለካከት፤ ወኔ እና ጥላቻ የወያኔን ትግል ተቀላቅሎ ዛሬ ኢሕአዴግ ተብሎ አዲስ አበባ ዘልቆአል፡፡ ስለዚህ እኔ በበኩሌ ሁልግዜ ፓርቲ የሚመሰረተው በርዮተአለም መነሻነት ሳይሆን በጥላቻ እና በገዢ ፓርቲ ግፍእና መከራ መሰላቸት ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህ ችግራችንን ብናቀውም በጋራ ግን የችግራችን መፍተሄ ለመፈለግ የሚያስተምረን የሚመራን እንድናጣ እንደህዝብ ተቸግረናል፡፡ ምንአልባት ወያኔ ኢሕአዴግን መፍተሄ እንዳያመጣ ወይም እንዲ ጠላ ሊያደርገው የሚችለው ሁኔታ ከርዮተአለም መመስረት በፊት ጥላቻን ይዞ በመውጣቱ ነው፡፡ ኮለኔር መንግስቱ ሀይለስላሴን እና አስተዳዳሪውን በጣም ይጠሉ እንደነበር የወሰዱት ብቀላ በ60 ባለስልጣኖች ግድያ አላቆሙትም፡፡
አንድ ነገር ደግሞ ምንአልባት ላይመቻችሁ ይችላል፤ እናስተውል ካልን፤ወያኔ ኢሕአዴግ ደርግን ለመጣል ተነስቶ ቢሳካለትም የጀመረው ርዮተአለም፤ በክልል የከፋፈለው እና በዘር ስም ሁሉም በራሱ ጎጥ እንዲመራ ያደረገው ነገር፤ እረጅም ግዜ ጎጥ የሚለውን ነገር እረስቶ በአንድነት ይኖር የነበረውን ሕዝብ አስደንጋጭ ነገር እና የስነልቦና መረበሽ እንዳመጣበት የማንክደው ሀቅ ነው፡፡ ይህ ተጋብቶእና ተዋልዶ የነበረው ሕዝብ ልክ ዱብ እዳ እንደመጣበት ቢሆንም፤ ደግሞም በውስጡ ጥቂት ብዙም ከጥቅም ጋር የተሳሰሩ ሰዎች በደስታ ሲጨፍሩበት እና እንዳውም ታሪክን እየመዘበሩ መንግስትእና ህዝብ እንዳይገናኝ ድልድይ ሲያፈርሱበት እንደነበር እናውቀዋለን፡፡ አዎ የሞተእና ያረጀ ከታሪክነት ሊያልፍ የማይገባውን መዝብሮ በማጣመም፤ ጎጥእና ጎጥን እንዲፋጠጥም ተደርጎ እንደነበር የማይካድ ሀቅ ነው፡፡ ስለልማትም ሲወራ ሁሉም ክልሉን ያልማ የተባለበትም ወቅት ነበር፡፡ በእምነትም ከሄድን አንዱ አንዱን የሚከስበትን የሚጠላበትን ነገር ሁሉ አይተን አልፈናል፡፡ እንግዲሕ ይህን እንዲከሰት የወያኔ ኢሕአዴግ ፍላጎትም ይሆን ወይም የሰዎች እራስን ወዳድነት አመለካከትን በመሳት ችግሮች ግን አልፈዋል ዛሬም እየቀጠሉ ነው፡፡ ይህ ተቻችሎ አብሮ የመኖርንም ሁኔታ ሊያናጋው የዳዳው እንደነበር አንክደውም፡፡ ብዙ ነገሮች ፌድራል ፖሊሱን ስራ እንዳያጣ አድርጎታል፡፡ በዚህ የተነሳም እና ደግሞ እነዚህ መሰል ነገሮች የመሬት ሁኔታ ስድነት ሁሉ ኢሕአዴግን ትልቅ ሀሜት ላይ እንደጣለው አይካድም፡፡ ሕዝቡም በዚህ የተነሳ ኢሕአዴግ ቢነሳለት ደስ የሚለው ሊበዛ ይችላል፡፡ እንዲነሳለት ይፈልግ እንጂ፤ ግን ማንን እንደሚተካ የማያውቀው፤ ካለመሰረት የመጣውን ለመቀበል መከፋቱ ወይም የተገደበው የፖለቲካ እውቀቱ ያስገድደዋል፡፡ እንደነገሩ የኢትዮጲያ ህዝብ በአንድነት የሚጉዋዝለት የፖለቲካ ፓርቲ ቢያገኝ ኖሮ ኢሕአዴግን ለመቀየር በወደደ ነበር፡፡ እንግዲሕ ልብ እንበል፤ አንደኛ እራሳቸው ገዢ ፓርቲዎች ባመጡት ቀውስ ሕዝቡ እንዲማረር ይሆናል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ሕዝቡእራሱ ከባህል ተጽእኖ ክፉን እራሱ እጉያው ደብቆ በማስቀመጡ ፤ ከረር ተቲ ከክ ነን ፤ ባለመድፈሩ የእራሱ ጠላት እራሱ ይሆናል፡፡ ብዙ ግዜ ገዢ ፓርቲዎች ያመጡትን ቀውስ ግን እንዴት ልፍታው ሳይሆን ቀውሱን እንዴት ልደብቀው በማለት ጊዜን በተሳሳተ አካሄያድ ይበለዋል፡፡ የተደበቀ ነገር የጠፋ ነገር አይደለም፡፡ ተቃዋሚ ደግሞ የማንኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ ባህሪው በመሆኑ ከገዢው ፓርቲ ስር ስር እየሄደ ስህተቶችን ይለቅማል፡፡ ቢቻልም አጋኖ ለህዝብ ያቀርባል፡፡ ይህ አካሄያድ ገዢውፓርቲም እራሱ ተጠቅሞበታል፡፡ አስታውሳለሁ፤ ወያኔ ጫካ እያለ፤ ሰዎች የወያኔን ሬዲዮን ያዳመጠ ሁሉም ወደጫካ ይገባል ይባል እንደነበር፡፡ ፕሮፖጋንዳው ሀይለኛ ነበር፡፡ „ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው“ ተብሎአልእና፡፡ ምሬት ሲበዛ ፤ በዚህ አይነት ሁኔታ ግዜ ነበር፤ ቅንጅት በኢትዮጲያ በለስ ሊቀናው አፋፍ ላይ የነበረው፡፡ ወቅቱ ኢሕአዴግ በእራሱ አባል እንኩዋን ፈተና ላይ የወደቀበት ጊዜ ነበር፡፡ ሁሉም ሁለት ጣቱን ቀስሮ ቅንጅት ቅንጅት ሲል ነበር፡፡ ግና ቅንጅት ምን ያህል ግዜ ነበር ከተደራጀ፤ የሚለውን ስንመለከት፤ በጥላቻ „የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው“ የሚለውን መነሻ እንዳይሆን ያስፈራ ያልጠነከረ ወይም በብሶት እና በመከራ ብቻ የሚሸሽበት ድርጀት ወይም የፖለቲካ ፓርቲ እንድንመሰርት የሚያስገድዱን ብዙ ሀይለኛ ችግር ሊኖረን ይችላል፡፡ ግን ምን ያህል መፍተሄ ያመጣል የሚለውን ለመመልከት አዳጋች አልሆነም፡፡ ኢሕአዴግ ቅንጅት አሸንፎአል ብሎ ለመልቀቅ ተዘጋጅቶ ነበር ወይ? እንዲዘጋጅስ የሚያደርገው አመኔታን ገንብቶአል ወይ?ደግሞስ ቅንጅት የተቀናጀው፤ እርስበእርሳቸው ፓርቲዎች ተዋውቀው ተማምነው ነው ወይ? የሚለውን ማየት ግድ ሊለን ይገባል፡፡ ህዝብ ለውጥ መፈለጉ ብቻ ሳይሆን ለለውጡ የተዘጋጀው ፖለቲካ ፓርቲ ማነው?ስንት ነው? ያለውን ገዢስ ፓርቲ አስወግደው ስልጣን ለማያዝ አንድነታቸው እርስበእርሳቸው አብሮ የመስራት መደራጀት ምን ያህል የበረታ ነው? ምን ያሕል ያመኑበት ነው? የሚለውን ሁሉ መመልከት ያሻል፡፡ አንድ ነገር መገመት ይኖርብናል ብዬ የምገምተው፤ ማንኛውም የሚካሄደው የገዢውም ፓርቲ ሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ ትግል ህዝብን አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርገው ክፍል ተሸናፊ ይሆናል፡፡ ኢሕአዴግ አሁንም በትግል ላይ አልጨረስኩም ይላል፡፡ የእሱ ትግል እንዲጠቃለልት ከፈለገ የህግ የበላይነትን ፈጽሞ አስፈጽሞ እንዲፈጽሙ ነጻ ለቆ፤ አድሎን ትቶ፤ በጎጥ ክልል የሚለውን ነገር እንደገና መርምሮ ማየት እና ማሳየት ነው፡፡ ተቃዋሚ በትግል ላይ ነኝ ይላል፡፡ ይህም ውጤት እንዲያመጣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተዋህደው ፖለቲካ አካሄዳቸውን መመርመር አለባቸው፡፡ ሕዝብን መቶ አቅጣጫ ብታሳየውም ከእለት ጉርስ የማያልፍ ህይወት ስለሆነ አኑዋኑዋሩ ተቃዋሚም ሆነ ገዢው ፓርቲን የት ነው ያለሕ ብሎ ለመፈለግ ይቸገራል፡፡ ሁለታችሁም ተቃዋሚም ገዢውም ፓርቲ ደግሞ የምትጉዋዙት ጉዞ የሕዝብ ዝምታ መቻሉ ሳይሆን ታዝቦ ነው እያልኩ ሰላም ሰላም ይብዛላችሁ እላለሁ፡፡ ባዩሽ