Freitag, 6. Juni 2014



ጉድ እና ዘንድሮ


አለማችን በሙስና ነገር በጣም የደከማት ይመስላል፡፡ በየአገሩ በመጋነን እየተነገረለት  ያለው የታላላቅ ሰዎች በሙስና መዘፈቅ ጉዳይ ሕዝብን በማስቆጣቱ እና ካልተስተካካለም ህዝብን ወደስርአት አልበኝነት ሊመራ ይችላል ተብሎ የተፈራው አክቲቪስቶችንም ቁጥራቸውን በእጅጉ እንዲጨምር አድርጎአል፡፡ በአለም ላይ የሚቸገረው ህዝብ ቁጥሩ እየጨመረ የሚሄድበት እና፤ የዳቦ ጉዳይ እንኩዋን እያጨናነቀው በሚሄድ ህዝብ መካከል፤ እኔ ብቻ ልኑር የሚሉ እራስን ወዳዶች ሊጠፉ አልቻሉም፡፡ ዛሬ ቻይናን እንኩዋን የሙስና ጉዳይ የሚያሳስባት ሆኖአል፡፡ ምክናያቱም በስልጣን ያለው የትልቁ ፓርቲ ባለስልጣኖች ሙስና ሳይኖርባቸው የቀረ አይመስልም፡፡ በየአደባባዩ ለዚሁ ጉዳይ እየወጡ የሚታሰሩ ሊጠፉ አልቻሉም፡፡  ቁጥሩ እየጨመረ የሄደው ተቃውሞ በቻይና ሌላ የፖለቲካ አካሄያድ ሊያስመዘግብ እንደሚችል ነው፡፡ ካላስተዋሉ ማለት ነው፡፡ ኢኮኖሚዋ እጅግ ያደገው ቻይና ሰዎቹዋን ለበለጠ ጉጉት ሳይዳርገው አልቀረም፡፡ አንዱ ሙስና ሲሆን ሌላው ደግሞ እኔም ይገባኛል የሚለው የእኩልነት መብት ጥያቄ ይሆናል፡፡ ተማሪዎች በተለይ እየሞቱም ጥያቄ አቅራቢ ከሆኑ ሰንበትበት ብለዋል፡፡ ዝም ማለት የቀረ፤ ፍርሃትም ከልባቸው እየወጣ የሄደ ይመስላል፡፡ ኢኮኖሚ አደገ ማለት ሁሉ ተመቸው ማለት እንዳልሆነ እየታየ ነው፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ልተወው እና ስለዛሬው አየር ጠባይ ልንገራችሁ፡፡ አንደዬ ይቀዘቅዛል አንደየ ይበርዳል፡፡በጀርመን ማለቴ ነው፡፡ የምንለብሰውን አንዳንደዬ ማወቅ ተስኖናል፡፡ ቢሆንም ለእኛ አታስቡ፤ ለሁሉም የአየር ጠባይ የሚለበስ ስላለን፤ ፖርሳችንን ወጥረን መሄድ ነው፡፡ በጨርቅ ሞልተን ማለቴ ነው፡፡ እንዲያ ሲል ማውለቅ፤ እምቢ ሲል መልበስ፡፡ ምን አለብን፤ ዲሞክራሲው ትንሽ ምቾት ሳይሰጠን አልቀረም፡፡ የኢሮፕ ንጉሶች ብዙ ደክመው አልፈዋል፡፡ አንድ ቀን ከመስራት አርፎ የማያውቀው ጀርመን ዛሬ የደረሰበትን ደረጃ ሳየው ግርም ይለኛል፡፡ በፖለቲካ ያልተለማመዱት ልምድ የለም፡፡ ብዙ መስዋእትነት የከፈለው እርስበእርሱ እንደአውሬ እየተራረደ ሲዋጋ የነበረው ኢይሮፕ ዛሬ አንድ ለመሆን ፈር ቀዶለታል፡፡ የትናንትናውን አላዩም፡፡ ቢያዩስ እንዴት ጀርመን ከፈረንሳይ እንግሊዝ ከጀርመን እያለ አንድ ይሆኑ ነበር፡፡ በጭራሽ የሚታሰብ አልነበረም፡፡ ግን ወደሁዋላ እንደያይ ፈረንጅ የታደለ ይመስላል፤፤ ወደፊት ይረግጡ ይዘዋል፡፡ በኢሮፕ የሚራብ ወይም በረንዳ ተገዶ የሚያድር የለለበት እየሆነ ነው፡፡ የዳቦ ጥያቄያቸውን የመለሱ አገሮች፤ ሰብአዊነት የገባቸው አገሮች አንድ ለመሆን ወስነው ጀምረውታል፡፡ የቀሩትም እንዲስተካከሉ እየተመከሩ ነው፡፡ ይሻላል ባይ ነኝ፡፡ ሁሉ ባይከብርም መራብ የለበትም የሚል እምነቴ የጠና ሆኖአል እና፡፡ የሕን ልተወው እና፤
ጀርመን ሙስናን የማይወድ አገር ነው፤ ከጥንት ጀምሮ፤ ለየት የሚያደርገው፤ ከስር ሳያድግ መቁረጥ ይችሉበታል፡፡ ሰው እንዳለ ፖሊስ ይመስላል፡፡ እያንዳንዱ የሚያየውን ይጠብቃል የሰማውን ለማረጋገጥ ይጥራል፡፤ ጠቁዋሚው አያድርስ ነው፡፡ እንዳውም የማይጠቁም ይናቃል፡፡ ስህተትን አይቶ ዝም የሚል ሰነፍ ወይም ህመምተኛ ብቻ ነው፡፡ በእኛ ግን እብድ ይባላል፡፡ በማያገባው እየገባ ይባላል፡፡ የመንግስት የተባለች ነገር አንድ እስክርቢቶም በከንቱ አትወጣም፡፡ ማፈሪያ እያሉ ያዋርዱሃል እንጂ እንዲህ ሆ ቀጥል ወይም „ዝም አይነቅዝም“ ብሎ እንደአገሬ ሰው የሚያዳንቅ የሚተችህ አይምሰለህ፡፡ እንኩዋንም ፖሊሱ ልልህ ፈልጌ ነው፤ ህዝብ ንብረቱን ይጠብቃል፡፡ የመንግስት መኪኖች በእረፍት ጊዜ አይንቀሳቀሱም፡፡ ወ/ሮ አንጀላ መርክልም ቢሆኑ ለግል ጉዳይ ወይም ከስራቸው ውጭ የመንግስትን ገንዘብ መጠቀም አይችሉም፡፡ሁሉም ባጀት አለው፡፡ ጀርመን አገር  ሳንሱር የሚደረገው፤ ጋዜጣ ላይ በምትጽፈው ወይም በምትናገረው ሳይሆን ቁጥጥሩ እምታባክነው ንብረት ላይ ነው፡፡ አምስት ሳንቲም ማን አስነክቶህ፡፡ የመንግስት ማለት የእኔ ነው፣ የቤተሰቤ ነው፣የጎረቤቴ ነው ደግሞም የጀርመን ሕዝብ ነው፡፡ እንዲች በይለፍ በይቅርታ አይከድም፡፡ ማን ይፈቅድለታል ዳኛውን ይህን ለመወሰን፡፡ እሱም ባለቤት እኮ ነው፡፡ ለአገሩ እየቀጣ መቀጣጫ ያደርጋል እንጂ፡፡ ፖለቲካ ፓርቲ እዚህ ውስጥ ምን አገባው፡፡ ሌባውም ፓርቲን ተማምኖ አይሰርቅም፡፡ ይህማ ከሆነ ፓርቲውን ከጨዋታ ውጭ ያደርጋል፡፡ ወዳጄ፤ ካለ ዲሲፕሊን ሹመት የለም፡፡ የማንነትህ አጥንት ሳይመረመር ስልጣን ማን ሰጥቶሕ፡፡ እንዲሕ ናት ጀርመን፡፡ ደግሞ አንድ ልበላችሁ
ስዊዝ ባንክ ገንዘብ በድብቅ ያስቀመጡ ባለሀብቶች ጉድ ከፈላባቸው ሰንበት ብሎአል፡፡ አንዱ አገሩን ወዳጅ እንዳለ ዶኮሜንታቸውን ሳይሰጥባቸው አልቀረም መሰል፡፡ እራሳችሁን አጋልጡ ተብሎ ከተነገረ ከርሞአል፡፤ ቅጣቱ ቢቀል ተብሎ የሚያጋፍጥም አልጠፋም፡፡ ያጋፈጠም ጉዱ እየተመዘዘ መውጣት ይዞአል፡፡ እሱ በማንካ መንግስትን ሊሸነግል ያለ የጀርመን ሕግ  ግን አካፋውን ይዙ ቀርቦአል፡፡ ልብ በሉ፡፡ የሰረቁ አይደሉም፡፡ ግን ግብር ያላስገቡት ገንዘብ ስላለበት ነው፡፡ ያው ነው፤ በዚህ አገር ግብር ያላስገባ ለሕዝቡ ሌባ፣ ሞላጫ፣ ደግሞም ማፈሪያ ነው፡፡ እንኩዋን ሚሌኒየር ይቅር እና ተራ ሰራተኛም ቢሆን አይቀርለት፡፡ ልዩነቱ ሚሊኒዬር ሲታማ በሚዲያ ነው፡፡ ጋዜጠኛስ ሌላው ጎልጉል ነውና ያውጃል፡፡ ጉድ እኮ ነው፡፡ አቤት ህግ እንዴት ደስ ይላል፡፡ ወዳጄ፤ አባጋር እዚህ አገር አይፈራም ህጉ እንጂ፡፡  ሕግ አስከባሪው አይፈራም እዚህ አገር ዘመዴ ህጉ ነው፡፡ ህጉ አብሮሕ ይተኛል አብሮሕ ይነሳል፡፡ ሕግ ነው፡፡ ድንገት ብትሞት እንኩዋን፤ እሬሳሕ ሳይመረመር ወደመቃብር ማን ወስዶሕ፡፡ ወይ ፍንክች፡፡ ለምን ሞተ ?እንዴት ሞተ? ደሞ ወደሴቶች ልግባ፡፡
አጠር ላድርገው፡፡ ለሴት እኩልነት የምትሙዋገተው ተዋቂዋ ሴት /Alice Schwarzer/ አሊስ ሽቫርዘር  የስዊዘርላንድ ባንክ ገንዘብ ጉዳይ የሚመለከታት ሆኖ እራሱዋን አጋፍጣ 200.000 ሁለት መቶ ሺህ ዩሮ  አስገብታ ነበር፡፡ ግን የዛሬው ዜና እንደነገረን፡፡ የጀርመን አቃቤ ህግ ሌላ ክስ ይዞ ቀርቦአል፡፡ እሱም ብሩ ትክክል አይደለም አይበቃኝም ብሎአል፡፡ ያውጣኝ ነው፡፡ ችግሩ አሁን ለወይዘሩዋ ያ የምትደነቅበት የፖለቲካ አቁዋም፤ አንቱ ያስባለት እና መሰንበቻውን ገደል አፋፍ ላይ የነበረው ጨርሶ ገደል እንዳይገባ ፍሩልኝ፡፡ ጥያቄው ብር ብቻ ሳይሆን፤ የምትናገረው የሚታመነው ድርጊትን መሰረት ስለሚያደርግ ነው፡፡ ከፍ ከፍ ያሉ ዝቅ ዝቅ ይላሉ ነው ነገሩ፡፡
አገሬ ኢትዮጲያ እንዴት ከረምሽልኝ ልበልሽ እና፤ በይ አንቺም በጎረቤት ቅኚ እና ልጆችሽን ወደፊት እንጂ ወደሁዋላ አትዩ በይልኝ፡፡ ደግሞም አቃቤ ህግን ነቃ በልእና ነጻ ውጣ ለመንግስት/ ለህዝብ ስራ ቁም/ በይልኝ፡፡ እወዳችሁዋለህ የምላችሁ
ባዩሽ


Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen