ይህን ያውቁ ኖሮአል?
ሁሉም የተደበቁ ግፎች አንድ ቀን ይወጣሉ፡፡ አለማችን በግፍ የተሞላች ነች፡፡ አንዳንዱም መዘዙ ቤተእምነቶች
የሚያስተምሩት ወግ ስርአት ባህል ነው፡፡ እኔ በበኩሌ ደሃም ሁን ሀብታም፤ ጎባጣም ሁን ቀጥ ያልክ በትዳርም ውስጥ ተወለድ ያለትዳር፤
እግዚአብሄር ለአላማው ሰውን የፈጠረ ይመስለኛል፡፡ ነፍስ በሰው እጅ
ትጠፋለች እንጂ በሰውስ አትፈጠርም እና፡፡ ስለዚህ ሁሉም የሰው ልጅ የእግዚአብሄር መልክተኛ ሆኖ የተፈጠረ ይመስለኛል፡፡ ግን እዝች
አለም ላይ አስቀድሞ ሰይጣን ስለተላከ ይመስላል ሰውን እንዲስት አድርጎታል፡፤ ከሁሉ በጣም አስቀያሚው ነገር በእግዚአብሄር ሰም
የሚደረጉ ስህተቶች ናቸው፡፡ ሰሞኑን አንድ ዶኩሜንታር ፊልም አየሁ፤ እሱም በአንድ ቦታ ከስምንት መቶ ህጻናት በላይ አጥም መገኘቱ
ነው፡፡ ይህ ደግሞ እየታወቀ የተፈጸመ ታሪክ ነው፡፡ ታሪኩም በኢንግላንድ አካባቢ ተፈጽሞአል፡፡ቤተክርስቲያንም ብታውቅም ሚስጥሩን
ደብቃ ይዛለች፡፡ እንዲሕ ነው የሆነው፤ በዛን ዘመን ካለጋብቻ የተወለደ፤ ወይም አባቱን የማያውቅ ህጻን ዲቃላ ይባላል፡፡ ይህ ኅጻን
የተረገመ፣ የተጠላ፣ እድለቢስ እና ያልተባረከ ነው ተብሎ ተደምድሞአል፡፡
ስለዚህ የወለደች እናት እስከቤተሰቡዋ ስለሚያገሉዋት ነውርም ስለሆነ
ቶሎ የተወለደውን ልጅ ወደዛ መጣል ነው፡፡ የሚገርመው ቤተክርስቲያንም በወቅቱ በተለምዶ ዲቃላ የሚባለውን ልጅ እንዲያድግ ወይም
ህብረተሰቡ እንዲቀበለው የምታደርገው ጥረት አልነበረም፡፡ አንዲት ወጣት ወዳም ይሁን በአስገድዶ መደፈር የመጣባትን እርግዝና፤ ከመርዝ
የበለጠ መራራ ይሆንባታል፡፡ ልጅ አይባለም መርገምት ነውእና፡፡ ለአንዳንዶች መደሰቻ፤ ለአንዳንዶች መርገም የሆነው እርግዝና አሰቃቂ
ምእራፉን ጥሎ አልፎአል፡፡ ለአንዳንዶች ደግሞ አለማችን ብዙ ግፍ
እና ሰቆቃ እምባ የፈሰሰባት፤ የምድር ሲኦል መሆኑዋን አንዘነጋም፡፡
ለነገሩ በሁሉም ሞት ባይኖር አለም ምን ትመስል ነበር? ብዬ ስጠይቅ መልሱ ልቤን ያፈካዋል፡፡ በሁሉም ቤት አንድ ቀን ዋይታ አለእና፡፡
„ ለሁሉም ግዜ አለው“ የሚለው የሰለሞን ትንቢት መሰል ጥቅስ በወቅቱ
አይታወቅ ይሆን? በዚህ የተነሳ ነበር ዲቃላ ተብዬው ያልታደለ ኅጻን ወይም ለእኛ ሀጢያት መጨመሪያ የተወለደ ሕጻን ነፍስ አውጭኝ
ወደ ካቶሎክ ቤተክርስቲያን ሲወረወር የነበረው፡፡ እዛም የሞቀ እና
የደመቀ ነገር አልተቀበለውም፡፡ በወቅቱ ኢይሮፕ እራሱዋ ሁሉንም ህዝብ እኩል ያልያዘች ስለነበረች እነዚህ ህጻናቶች የሚፈለገው እንክብካቤ
ያደረገላቸው የለም፡፡ የታደለ ትረፍ ያለው ነፍስ ለአዳብሽን/ጉድፈቻ/ ይሰጥ ነበር፡፡ እዛ የቀረው ግን የበለጠው ቁጥር ይሞታል፡፡
ብርድ ነው እራሃብ ነው፡፡ አርና ሽንቱን የማይቆጣጠር ልጅ ማንስ ተከታትሎ ያስበዋል፡፡ እዛም ከተወረወሩ በሁዋላ ዞሮ የሚያያቸው ቤተሰብ መንግስትም የለም፡፡ እናትም ልቡዋ ቢፈልግ እድሉ የላትም፡፡
ልጅም እንደወለደች አይወራም ነውር ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡ ባልሰለጠነ ዘመን መኖር፡፡ ግፉ ከዛሬው ይብስ ነበርእና፡፡ ለመሆኑ እግዚአብሄር
አይደለምእን ነፍስ ለመፍጠር እና ወደዚች ምድር ለመላክ ያሰበው? እንግዲህ ያ ያልሰለጠነው ዘመን፤ ይህን ይመስላል፤ የሴት መከራ
ለልጅ ሲተርፍ፡፡ ዛሬ የተረፉት ወይም ለአዳብሽን የተሰጡት አርጅተው ዘራቸውን እየፈለጉ እንባ በእንባ እየታጠቡ በደኩሜንታሪው ፊልም
ተመለከትኩ፡፡ እንኩዋን እነሱ መለየትን ተለማምደው የተሰቃዩት እና እኛም የምናየው አለቀስን፡፡ አለም ምን ትመሰል ነበር በዛ ባልሰለጠነ
ዘመን?
ደግሞም ሌላ ሽው ያለ ኮሜንት በሌላ ዜና ሰማሁ፡፡ በነገስታቶች በባላባቶች ቤት አካሉ ጎሎ ወይም
ታሞ የተወለደ ሕጻን ይገደል ነበር የሚል ጥርጣሬ የያዘ ነገር፡፡እሱም እባላባቶች ቤት ቆንጆብቻ ነው የሚወለደው የሚለውን ማንነት
የተለዬ ለማድርግ ነበር፡፡ ዌል ነጻ ፕሬስ እየጎለጎለ አሰቃቂውን ዘመን ጠቆም ሳያደርግ አልፎ አያውቅም፡፡ ዛሬ ግን አለም ለየት ያለ መልክ ይዛለች፡፡ ባልሰለጠነው ዘመን ፤ ኢትዮጲያም
ውስጥ ዲቃላ ነውር እንደነበር እኔም ሰምቻለሁ፡፡ „ ዋ ዲቃላ ታመጪብኝ እና“ ተብላ ያላደገች ሴት አትገኝም፡፡ማን ወልዶ ለዛውም፡፡
ከተወለደም፤ ጎረቤት ሳያየው እንዳያለቅስ አፉ እየታፈነ፤ ወይም ጌቶቹ/አባወራው/ እንዳያዩት እንዳይሰሙት እየተባለ ያደገም እንዳለ
ይነገራል፡፡ አልያም ወደገጠር በስውር ለከብት እረኝነት የተሰጠ፡፡ እናንተ ግን ዘመን ነጻ አውጥቶአችሁዋል፡፡ ልብ በሉ ሰውን ሰው
ነጻ አያወጣውም ዘመን እንጂ፡፡ የትናንትናውን በደል ላስብ ያለ የዛሬውን ሳይመለከት ድርብ እንዳይሆንበት፡፡ ዛሬ ዘመን ለጣለብህ
ግፍ እና መከራ ድምጽህን አሰማ፡፡ በትናንትናው ዘመን የተደረገው በእራሱ በእምነት መሪዎች የተደገፈ እና የተደበቀ ሆኖ አልፎአል፡፡
ስለዚህ እንዳው ወደትናንት ገብቶ ሲቃ ከሚይዘን፤ የዛሬ ያቀረበልን የነገው እንዳይወቅሰን መዘጋጀት ነው፡፡ ከሳሹም ተከሳሹም አልፈዋል
እና፡፡ ጥቂት ባላባቶች እንደሚመቻቸው ወግን ስርአትን አድርገው አሰቃቂ ሁኔታ በአለም ዙሪያ አልፎአል፡፡ ዛሬ ኢይሮፕ መልኩዋ ከተቀየረ
ዘመን አለፈ፡፡ አንተስ ወዳጄ፤ ከትናንትናው ለመውጣት ዝግጁ ነህእን? ወይስ ትናንት እንዲህ ሆኖብኛል እያልክ አጽም መቀስቀስ፡፡
ልብ እንበል ወዳጆቼ፤ የባላባት ዘመን ለዛሬ አይሆንም፡፡ አጠፉም አለሙም አለም በአንድ ወቅት አንድ አይነት የዘመን ባህል ኣሳልፋለች፡፡
አለም አንድ መሬት ላይ የሰፈረች እኛን የተሸከመች እንሰሳ ነች፡፡ አሕያ ትጫናለች እንጂ የተጫነችውን ማወቅ ትችላለች እን?በቻለችስ፤
ምግቡዋን ተሸክማ በባዶ ሆዱዋ ባልተራመደች ነበር፡፡ በቸር
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen