በወሎ ሰማይ ክፍት መሆኑን አረጋገጥኩ
ክፍል 2
እኔም ደክሞኝ ነበር እና፤ ለማረፍ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩ፡፡ ከእኔ ጋር በወቅቱ የሚኖሩትም አንዲት ሴት እና አንድ
አዛውንት ሽማግሌ፤ ሁሉም ወደየማረፊያው ለመተኛት ገብቶአል፡፡ የደሴ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ በግፍ ያስገደለኝ ውሻዬም በዚሕ
ለሊት በሕይወት ስለነበረ በጣም ይጮሃል፡፡ እንቅልፍም ቢጫነኝ እንደምንም ተነስቼ ለምን እንደሚጮሕ ለማየት እንደእስር ቤት በበረት የታጠረውን የመስተዋት መስኮት ተጠጋሁት፡፡
የሚጮሐውም ወደሰማይ እያየ እና እየዘለለ ነበር፡፡ ገረመኝ፡፡ ወደላይ ግን ባቀና እኔ የማየው ነገር አልነበረኝም፡፡ ባሻ የሚተኙበትን
ክፍል አሽቆልቁዬ ብመለከት ግን ካለወትሮአቸው ጸጥ ብለዋል፡፡ ትንሽም ልቤ በድንጋጤ ተሞላ፡፡ ምንአልባት ሕይወቴን የሚፈልጋት ጣራ
ላይ ተንጠልጥሎ ይሆን ብዬ ፤ እጎኔ ወዳለው ክፍል ቀስ ብዬ ከፈትኩ እና ገባሁ፡፡ ከእኔ ጋር ያለችው ሴት ግን እንደሕጻን ለጥ
ያለ እንቅልፉዋን ተኝታለች፡፡ ከቤቱ ውስጥ ወጥቼ ለመሄድ እና ውሻዬ የሚጮሕበትን ጉዳይ ለማየት አልደፈርኩም፡፡ ደግሞም በፍርሀት
ብሞላም እንቅልፍ የሚነሳ አልሆነም እና ወደአልጋዬ መሄድ አማረኝ፡፡ ለወትሮው ስፈራ እንቅልፍ የለኝም፡፡ በዚህ ምሽት ግን ውስጤ
በሰላም ተሞላ፡፡ እኔም ወደአልጋዬ ሄጀ ተመቻችቼ ተኛሁ፡፡ ወዳውም የእንቅልፍ ሰመመን ውስጥ ገባሁ፡፡ በድንገትም አንድ ሰማያዊ
ሻል የለበሰች ሴት ቀስ ብሎ በተከፈተ መስኮት ሰማይ ብቅ ትላለች፡፡ አለባበሱዋም በሙሉ ጠጉሩዋ እስከአንገትዋ ድረስ በለበሰችው
ሻሽ የተሸፈነ ነው፡፡ ፊቱዋ ግን ውብየሆነእና በደግነት የተሞላ ነበር፡፡ እኔም ወደዚህ ቅርብ ሰማይ ተመለከትኩ፡፡ በእዚህ ግዜ
ግን ከአላግየ ላይ ተነስቼ ቆሜአለሁ፡፡ እሱዋም „ እኔ ማርያም ነኝ፡፡ ከእኔ ምን ትፈልጊያለሽ ብላ በመገረም ትጠይቀኛለች፡፡ እኔም
ከሚካአል እንጂ ከእሱዋ ምንም ፈልጌ ስለማላውቅ፤ እረ ምንም አልፈልግ እላታለሁ፡፡ እሱዋም“ ስሚ የልብሽ ናፍቆት ተሰምቶአል እና
በዛ በኩል አንኩዋኪ ክርስቶስም ይወጣልሻል“ ብላኝ የወጣችበት መስኮት ቀስ ብሎ እንደተከፈተ ቀስ ብሎ ይዘጋል፡፡ አንኩዋኪ ያለችኝ
ሰማዩ አመልካች ጣትዋ እሱዋ ከነበረችበት በጣም የራቀ እና በከፍታ ላይ የተቀመጠ ነበር፡፡ ስማዩም የደሴው ገብርኤል ቤተክርስቲያን መሰረት የተጣለበት ስፍራ ላይ ነበር፡፡ የዛን ግዜ አሁን የተሰራው ቤተክርስቲያን አልተሰራም ነበር፡፡
ታቦቱ የነበረው ትንሽ ቤት ውስጥ ነበር፡፡ እኔ ግን ለማንኩዋኩዋት
አልደፈርኩም፡፡ ሰማዩም ላይ እጀ አይደርስም ብዬ ለመሞከርም በጣም ልቤ ለመድፈር ፈራ፡፡ ግን አንኩዋኪ አንኩዋኪ የሚለው እንደውሃ
የሚፈሰው ድምጽ በዛብኝ፡፡ በዚህም የተነሳ በድፍረት አመለከተችኝ ቦታ ላይ አንኩዋኩዋህ፡፡የሰማዩም መስኮት እንደነጎድጉዋድ ሆኖ
ተከፈተ፡፡ መጽሀፍ ቅዱስን ግን አንድም የማላውቅ ሴት በዛ መስኮት ውስጥ በግንባታ ላይ ያሉ ታላለቅ ማሀንዲሶች እና ግንበኞች በስማቸው
እየጠራሁ እንደማውቃቸው እጠራቸው ነበር፡፡ የመጀመሪያው ስሙን የጠራሁት ኤልያስ በማለት ነበር፡፡ እኔ ልጥራቸው እንጂ እነሱ ወደእኔ
እና ወደ ምድር አይመለከቱም ነበር፡፡ ለዚህ በስራ በእጅጉ ተጠምደው ተመለከትሁ፡፡ ወዲያውም ከእነሱ በአለባበሱ የተለዬ በብሩሕ
ነጭ ልብስ እስከአንገቱ ደግሞም እጁ አንገት ድረስ የለበሰ፤ በመስኮቱ ሙሉ ሆኖ ብቅ አለ፡፡ እጅግም ግዙፍ ነበር፡፡ ፊቱም የደግ ሰው፤ የዋህ ፊት፤ የማትፈራው ግን
የምትቀርበው የምትላመደው ነበር፡፡ ከዚህ እጅግ ግዙፍ ከሆነ ውብ ሰው ይህንን የማያስፈራ ፊት ማየቴ ገረመኝ፡፡ እሱም በለሰለሰእና
እንደውሃ በሚፈስ ድምጽ „ እኔ እየሱስ ነኝ፡፡ ከእኔ ምን ትፈልጊያለሽ“
በማለት ጥያቄ ጠየቀኝ፡፡ እኔም እረ ምንም አልፈልግ በማለት መለስኩ፡፡ እሱም ከአሁን በሁዋላ ብቻሽን አትሆኝም እና
በፈለግሽኝ ሰአት አንኩዋኪ በሩም ደግሞ ይከፈትልሻል እና“ በማለት የቃል መግባት ንግግር ይናገረኛል፡፡ ለዚህም ግንኙነት ምልክት
ይሆንሽ ዘንድ በማለት አንዳንድ ነገሮች ካሳየኝ በሁዋለ መስኮቱ ይዘጋል፡፡ እኔም ወደአልጋዬ ተመልሼ ልተኛ ስል፤ ባነንኩ፡፡ ለካስ ከአልጋየም አልተነሳሁ
ነበር፡፡ ወደ ሴቲቱም ክፍል ስሄድ ነቅታ ነበር፡፡ አልተኛሽም እንዴ ስላት „ እረ አንድ ሰውዬ ሲገባ ያየሁ መስሎኝ ባንኘ ነው
አለችኝ፡፡ ግራ በተጋባ መልኩ ወደመስኮቱ ስሄድ ባሻ ተነስተው በግቢው ይንጎራደዳሉ፡፡ ሰአቱንም ሳየው ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ተኩል
ሆኖአል፡፡ ግን ውድቅት ለሊት ነበር፡፡ ለካስ ነገሩንም ያየሁት ወዳው
አልጋዬ ላይ እንደተጋደምኩ ሳይሆን ብዙ ከተኛሁ በሁዋላ ነበር ማለት ነው፡፡ ባሻም „ የዛሬው ለሊት ይገርማል አንቺን እዚህ ካባ
ለብሰሽ አጠገቤ ቆመሽ አየሁሽ መሰል፡፡ ካባ እኮ ባል ነው“፡፡ በማለት ወደሕልም መፍታት ሄዱ፡፡ አሁን ስለባልም ሆነ ስለ አጉል
ተስፋ እንዳላልም የሚያደርገኝ እየሱስ የሚል ቃል ህይወቴን ሊለውጠው እንደተነሳ ባሻ አላወቁም፡፡ ውሻው ሲጮሕ ሰምተው ነበር? ብየ
ጠየኩዋቸው፡፡ እሳቸውም፡፡ „አዎ ፡፡ ስባንን ውሻው ይጮሕ ነበር፡፡
ሌባ የገባ መስሎኝ ዘልዬ ብወጣ እሱ የሚጮሐው ወደሰማይ እየዘለለ ነበር፡፡ እስከአሁን ሲጮሕ ነው የቆየው ፤ አሁን ግን ደሞ ድንገት
መጮሁም አቆመ እና ተኛ፡፡ እንግዲሕ ሰማይ ላይ ደግሞ ቀና ብልም
የማየው ነገር የለም“፡፡ በማለት የምስክር ቃላቸውን ነገሩኝ፡፡ እኔም
ወደአልጋዬ በመገረም ተመለስኩ፡፡ ያየሁትን ነገር ሁሉ ግን የተረጎምኩት ከእነዛ ተደራራቢ በአል ነውና ዛሬ አንስራ ያሉኝ ሰዎች
ጋር ነበር፡፡ ነግቶልኝም ዛሬ ይህን ቀን ስራ እንዳይሰሩ ለማድረግ ቸኮልኩ፡፡ በዛ በኩል ቅጣት እንዳይመጣብኝ ፈራሁ፡፡ እየሱስን
ለማየት የበቃ እምነትም የለኝም እና ቅብዥር ነው ብዬ ብገምትም፤ ሰዎቹን ግን ይህንን ቀን ነጻ ለማድረግ በውስጤ የሆነ ግፊት እየተጨመረ
ሄደ፡፡ የሰማይ መከፈት እና እየሱስ ነኝ የሚለው እየተደጋጋመ እረፍት ነስቶኛል፡፡ እኔም ጡዋት ሄጀ ስራ ዛሬ የለም ስላቸው፤ ይመርቁኝ
ጀመር፡፡ አንደኛው ግን „እትዬ የሆነ ነገር ሳይተያያት አልቀረም እንጂ ዛሬ የግድ እንሰራ ነበር“ ሲል እሰማው ነበር፡፡ እኔ ግን
የህልሙን ወይም የራእዩን ነገር በተመሰጣጠረ እይታ ባየውም ውነትም እየሱስ ብዙ ሳንደክም የምናገኘው መሆኑን የሚመሰክርልኝ ምስክርነቶች
ያሳየኝ ነገሮች እውነትነትን እየደጋገሙት ሄዱ፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ እየሱስ፣ መድሀኒአለም አልያም አማንኤል የሚባለውን ከዚህ ቀን
ጀምሮ ማነው ማለት ያዝኩ፡፡ እንዲሕስ ባይሆን ኖሮ መጽሀፍ ቅዱስን ምንነቱን ምንአልባትም ማወቅ አልችልም ነበር፡፡ ምንም እንኩዋን
ያንን ያለፈ እሁድ እና ገብርኤል ስራ አትስሩ የሚል መልእክትም ባይነግረኝ፡፡ እየሱስ ግን እራሱ እንዳለ በእራሱ የመሰከረልኝ እና
ቀጥታም ወደእሱ እንድለምን መፍቀዱ ይገርመኛል፡፡ ውድ አንባብያን ይህን የጻፍኩት ይህን ያየሁበት ያ አካባቢ ስለሚናፍቀኝ እና ሁልግዜም
ልቤ ወደእዛ ስለሚመኝ፤ ያሳደደኝን ሁኔታ የፈጠሩት ሰዎች ትዝ ሲለሚሉኝ ነው፡፡ በሰው መጥፎ ሀሳብ የተሰደደ እኔ ብቻ አይደለሁም፡፡ ይህ ሁላችሁንም ሊያሳስባችሁ
ይገባል፡፡ እርግጠኛ ሆኘ የምነግራችሁ ነገር አለ፡፡ እኔ የምናገረው የጻድቅነት ጉዳይ እንዳይመስላችሁ፡፡ እና ወደፌዝ ለመሄድ አትቸኩሉ፡፡
ግን የእግዚአብሄር ጥበብ የምትሄደው ወደመረጠው እንጂ ስለእሱ ወደተማረው አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ለስራው የሚመርጠውን እራሱ ያውቃል፡፡
እራሱም አስተማሪ ነውእና ሰው ስለእግዚአብሄር ሲናገር የአለም እውቀቱን ግዝፈቱን መጠየቅ አላዋቂነት ነው፡፡ እኔን ማለቴ ሳይሆን
ከሚሰደደው ሰው የምድሪቱን በረከት ማን እንደሚያስቁዋጥረው በሰው ዘንድ የተገለጠ አይደለም እና፤ በከንቱ የፈሰሱ እንባዎች እና
በከንቱ የፈሰሱ ደሞችን ብሎም አይምሮ የሚያናጋውን የሀሰት ምስክርነት እና ፍርድ የሚታደግ ንስሀ ፍጠሩ፡፡ ይህ እስካልሆነ ድረስ
ምድሪቱ ለሀጢያት ምግባር ለክፉ መሪዎች እየታለፈች ከመሰጠት አታባራም፡፡ ወሎን ሰማዩ ክፍት ሆኖ አይቸዋለሁ፡፡ የኢትዮጲያም ፖለቲከኞች ወሎን የሚፈሩበት
ነገር የሆነ ነገር ውነትም አለ ለማለት እንድደፍር አድርጎኛል፡፡ ጉዋጉቶ ሊያየውም ሊጎበኘውም የሚፈራ ብዙ ነው፡፡ እንደሚቀሰፉ
አድርገው ያዩታል፡፡ ምንአልባትም የልብን ክፋት የሚያየው አምላክ በዛ ምድር ቅርብ ሆን ብዬ የጠየኩበት ለሊት በእኔ ላይ ተፍጥሮአል፡፡
ከሰው ጽድቅ ጋር ሳይሆን የእግዚአብሄር መገኘትም በመረጠው ይገኛል እና፡፡ እንደእውነቱ „ከወሎ ምርቃኑ እርግማኑ ሲባልም ሰምቻለሁ“፡፡
ወሎንም የተረገጠ መሪ ይጠፋል የሚሉ አባባሎችም ሲናፈሱ እሰማ ነበር፡፡ ግን ከዚህ ለሊት ወዲሕ ግን የመሰከረልኝ ነገር አለ፡፡
በዋህነት ያመንከውን በክፋቱ አሳልፎ መስጠት ወሎ ላይ ሰማዩ ክፍት ነውእና፤ አባባሎችን ንቆ ማየት ሳይሆን ነቅቶ መመልከት መልካም
ነው፡፡ እንግዲህ አመናችሁም አላመናችሁም በወሎ ሰማዩ እጅግ ክፍት መሆኑን እነግራችሁዋለሁ፡፡ እስላምም አይደለም ክርስቲያን ሁሉም
በሰውልጅ ላይ የሚያደርገውን ግፍ ያቁም፡፡ እግዚአብሄር በሰማዩ አለ፡፡ አንኩዋኩም ለባዩሽ የተፈቀደ ለእናንተ የተፈቀደ ጉዳይ ነው፡፡
እግዚአብሄር ጸሎትን ብቻ ሳይሆን በመገፋትህም ለማነም ይገለጣል እና፡፡ ሀጢያተኛም ሆንክ ጻድቅ አንተ የእሱ ፍጡር መሆንህን አትዘንጋ፡፡
ወሎ ወሎ ስል እንግዲህ የዘረኝነት ጉዳይ ሳይሆን የመንፈሳዊ ሕይወቴ ጉዳይ ነው፡፡ እግዚአብሄር በዛ ምድር እጅግ ቅርብ መሆኑን
እወቁ፡፡ እጅግ ቅርብ፡፡ ለምን እንደመረጠው ግን ምክናያቱን እኔ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ስለዚህ በከንቱ ሰውን የሚንገላታ ከሌላም
ክልል ወደዛ ምድር አይግባ፡፡ እዛውም ተቀምጦ ይህን የሚሰራ በቶሎ ንስሃ ይግባ፡፡ የወሎ ሰማይ የተመረጠ ነውእና፤ በዚህ ምድር
የታሰረውን ሰው የሚፈታው አይደለም እና ሁላችሁም ጸልዩ፡፡ በቸር ልበላችሁ፡፡ ማንም ወደአልጋው ስሄድ ሰማይን ተከፍቶ ለማየት አይሄድም
እና፤ ማንኛውም ሀይማኖተኛ በዚች በምድር ላይ ተከባብሮ ጎን በጎን ይኑር፡፡ ለተገፋ ሰው መስኮቱ በቀላሉ የተከፈተ ነውእና መራገምም
ከባድ ቢሆንም ግን ሰው እንዳያዝንባችሁ ተጠንቀቁ፡፡ እግዚአብሄር የሰው ልብ አምላክ ነውእና፡፡ ይህን ክልል እንድኖርበት በሰላም
እንድኖርበት ብትፈቅዱልኝ መልካም ነበር፡፡ ካልሆነም እግዚአብሄር ይብቃኝ ብዬ ካለመኖር የምለውጥበትም ጉልበት የለኝም፡፡ ደግሞም
ክርስቲኖች ልታስታውሱት የሚገባ ነገር አለ፡፡ እሱም እየሱስ እርቦት ወደአንዲት ተክል እንደሄደ ታውቃላችሁ፡፡ ግን ሲደርስ ፍሬ
የላትም ነበር እና“ድርቅ ብለሽ ቅሪ አላት ደረቀችም“ ተብሎ ተጽፎአል እና፤ እርግማን በፕላን የምትረግመው ሳይሆን ድንገት የሚወረወር
መሆኑን አትዘንጉ፡፡ ሁልግዜ ያፈራችሁ ሁኑ እንጂ እርግማን ክልክል ነው ብላችሁ አታስቡ፡፡ ክልክልስ በሆነ ድርቅ በይ ባላለ ነበር፡፡
የልብ መከፋት፤ ቅጽበታዊ ነገር መፍጠሩንም እመኑ እና ከሰው ሀዘን ተጠበቁ፡፡ በወቅቱ ያየሁትን ሕልም በአካባቢዬ ለነበሩ ተናግሬአለሁ፡፡
ለታላላቅ ሰዎችም ነግሬ ነበር፡፡ ግን ምንም ስላልነበርኩ መንፈሳዊ ተደማጭነት አልነበረውም፡፡ ግን እርአዩ እስከአሁን ጠፍቶ አያውቅም፡፡
ስለዚህ እኔ የምናገረው ፖለቲካ አይደለም የኖርኩትን ነውእና መከፋቴንም ደስታዬንም አካፍችሁዋለሁ፡፡ ማንኛችሁንም ደግሞ የሀይማኖት
ተጽእኖ ለመፍጠር አልናገርም፡፡ የወሎ ሰማይ ግን ለአንኩዋኩዋው የተገፋ ሰው ሁሉ ክፍት ነው፡፡ በዣን ወቅት እኔም እያነባሁ እሰራ
ነበር እና፡፡ ስራየ ሳይሆን እንባዬ የማይቻለውን እንድመለከት አድርጎኛል እና፡፡ እስላም ነኝ ክርስቲያን ነኝ ሳትሉ በበላያችሁ
ያለውን ሰማይ አንኩዋኩ፡፡ „ወሎ ወሎ ቀረ ተንቀዋሎ“ የሚባለው እራሱ መቅሰፍትን የሚያመጣባችሁ ፌዝ እንደሆነስ ማን ያውቃል? ይህን
የዋሆችን አገር ልብ ብላችሁ ጠብቁት፡፡ ማን ያውቃል ከወሎስ የሚወጣውን፡፡ ወሎ ስደተኞችን የምትቀበል ደግሞም በዋህነት የምትገስጽ
አገር፡፡
በቸር የምላችሁ ባዩሽ
ነኝ፡፡
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen