አኔነቴን ለምን መኖር እንደፈለኩ፡፡
አቤል እና ቃኤልን የሰሩትን ስራ ሲደገም ባላይ፤ ስጋ ዘመዴን ብቻ ወድጄ፤ ባዳን ሁሉ በጠላሁ ነበር፡፡ ሰው የእራሱን ጎጥ ሲበድል እና ሲያሳድድ ባላይ፤ ጎጤን ብቻ በወደድኩ እና ኢትዮጲያ ኢትዮጲያ ባላልኩ ነበር፡፡ ሀብታም ደሃ ሲሆን፤ ደሃ ሃብታም ሲሆን ባላይ ኖሮ፤ በዛሬው ኑሮዬ እኮፈስ ወይም አዝን ነበር፡፡ ክርስቲያን ነኝ የሚል ሁሉ አጥፊ ቢሆን ሙስሊም እሆን ነበር፡፡ እስላምም ሁሉ በዳይ ቢሆን ኖሮ ሙስሊሞች ይጥፉ ብዬ እሰለፍ ነበር፡፡ ሰይጣን ሲሸነፍ ባላይ ኑሮ፤ በእግዚአብሄር ሀይል ባልታመንኩ ነበር፡፡ እማያምንም ሰው በተግባሩ ከአማኝ በልጦ ባልመለከት ኖሮ አማኝ ነኝ የሚል ሁሉ ጻድቅ ነው ብዬ በቀናሁ ነበር፡፡ ኢትዮጲያ ውስጥ አምባገነን እየተደጋገመ ባላይ ኖሮ የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ አባል እሆን ነበር፡፡ አይኔ የሚያየውን ነገር ሁሉ ብቻ ማመን በቂ ነው ብል ኖሮ በማይታየው እግዚአብሄር አላምንም ነበር፡፡ የስጋ ጆሮዬ የሰማውን ሁሉ እውነት ነው ብዬ ብመሰክር ሰይጣን ይጨፍርብኝ ነበር፡፡ ብዙ ጦር የነበራቸው አምባገነን መሪዎች ሲወድቁ ተመልክቻለሁእና፤ ጦሩን የሚያምን መሪ በእጅጉ ያሳዝነኛል፡፡
ባዩሽ

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen