አድርባይነት
የሚመጣው 1. ከፍርሃት 2. ከእራስ ወዳድነት ነው
አይምሮ ከባህር
ይሰፋል፡፡ የሰውልጅ የታወቁት እንኩዋን በጣም ብሩህ እውቀታም የተባሉት
እስከአሁን 1%ብቻ ነው ማይንዳቸውን የተጠቀሙበት ተብሎ በተመራማሪዎች
ይታመናል፡፡ አይምሮውን 2% እንኩዋን የተጠቀመበት እንደለለ ዘወትር
ይነገራል፡፡ ስለዚህ በሰው አይምሮ ውስጥ ብዙ ነገር የተቁዋጠረ እንዳለ እና የእራሱ ፋንታሲ ወይም ይበጃል የሚለው እንዳለው ልብ
እንበል፡፡ ይህን ስል ግን እኔ ትልቅ ነኝ ወይም የተሻለ ነገር አለኝ ማለቴ እንዳልሆነእና በጭራሽ ትእቢትን እና እብሪትን እንደምቃወም
ተረዱልኝ፡፡ ከሁላቸሁግን አለማወቄን የማውቀው የሌላውን አስተሳሰብ
ሳልኮፈስ ስሰማ ሳዳምጥ ነው፡፡ የእኔ ብቻ ትክክል ነው ከማለት ስወጣ ነው፡፡ አላዋቂ መሆን ደግሞ መታፈንን መገለልን ማምጣት የለበትም፡፡ አላዋቂነት የሚለወጥ ነገር እንጂ ሙጫ ሆኖ አይምሮ ውስጥ የሚቀመጥ አይደለም፡፡
አለማወቅ አይምሮን እንደጭጋግ ሆኖ የሚሸፍን እንጂ ተፈጥሮአዊ እውቀትን የሚያጠፋ ቫይረስ አይደለም፡፡ ሰው ማወቅ መረዳት ከፈለገ
ማወቅ የሚችል አይምሮ ተሰጥቶታል፡፡ ይህ የሚሆነው ግን ጭጋግ የሆነውን ጥበብን የሚሸፍነውን እብሪት እና ማንአለብኝነት አምባገነንነት
ከልብ ሲወገድ ብቻ ነው፡፡ አምባገነን ሲባል እንዳው ፖለቲካ መሪዎች ላይ ብቻ ተኮፍሶ የቀረ ወይም ለእነሱ ብቻ የተሰጠ መስሎ የሚታየው
ካለ ሞኝነት ነው፡፡ አምባገነን ከሁላችን ውስጥ በሰው ደረጃ ሊገኝ የሚችል በመሆኑ ሰው ሁሉ፤ እራሱን መመርመር አለበት፡፡ የበላይነት
ስሜት እራሱ በዘርም ሆነ በሀብት በእውቀትም ተመርኩዞ የሚገነባው በውስጥ የሚሰርጸው የአምባገነንነት ስሜት ነው፡፡ የሚያስከብር
ባህሪ ይኑርህ፡፡ እንዳው በማግኘት የተነሳ፣ በስልጣን እና በጨበጥከው ዲግሪ ከላይ ከላይ የምትራመድ ከሆነ እንቅፋት ይበዛብሃል፡፡ ምክናያቱም የቆምክባትን
መሬት ያዘጋጀችልህን መሰናክል ለማስተዋል ምድርን አላየህም እና፡፡ ሰው ከእራሱ የተለዬ አስተሳሰብ ሌላው እንዳለው መረዳት
አለበት፡፡ ሀብታም ሁን ባለስልጣን አልያም የተማርክ ግን ከአንተ የተለዬ አስተሳሰብ እና ሁኔታ ደግሞም ተቃራኒ እንዳለ ምንግዜም መረዳት አለብህ፡፡
ተቃራኒህ ሊያጠፋህ የሚነሳው፤ ያለህን ነገር ሁሉ ማካፈል ወይም ሌላውን መረዳት ሲያቅትህ ነው፡፡ ነገሩ ሁሉም አንድ ሰው በሚሰጠው አስተያየት ላይ ለምን እንዴት ብሎ ቢመራመር
እና ቢያስብ ለምን እንዲሕ ወይም እንዲያ እንዳለ ወደመረዳት አቅም ልንፈጥር እንችል ነበር፡፡ ግና አለመታደል ሆኖ ሁሉም መስማት
የሚፈልገው፤ ያንኑ የለመደውን፣ የሚያውቀውን አልያም እራሱ ጥሩ ነው
ብሎ የሚያምንበትን ነው፡፡ የአማባገነንነትም ባህሪ የሚፈጠረው እንዲሕ ሲሆን ነው፡፡ ስለዚህ መረዳት ቃተህ አስተያየት የሚገጥምህ
አይምሮህን ለአዲስ ነገር ወይም ለማታውቀው ነገር ዘግተህ ወይም ብሎክ ስታደርግ ብቻ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው የተለያዬ አስተያዬት
አስተሳሰብ አለው፡፡ አንድአይነት የሚያደርገው አንዱ እራስን ደብቆ አድርባይ ሲኮን ብቻ ነው፡፡ እሱም ቁዋሚ የሆነ የጠነከረ መሰረትም
የለውም፡፡ በዚህም የተነሳ የኢትዮጲያ ፖለቲካ መሰረት የለለው ፈራሽ ሕንጻ እየሆነ እንቸገራለን፡፡ አድርባይነት የሚመጣው 1. ከፍርሃት
2. ከእራስ ወዳድነት ነው ፡፡ ግን እኔ እግዚአብሄርን ወይም አላህን መሰረት አድርጌ የምነ ገረው፤ የኢትዮጲያን ህገመንግስት መሰረት
ያለው አድርጎ ለመገንባት የሚመቸው ነገር አስተሳሰብን በጋራ ማዋሀድ ብቻ ነው፡፡ ይህ እስከአልሆነ ድረስ፤ ዲሞክራሲን በፖለቲካው
አለም መመስረት አይቻለም፡፡ ግን በዛው መቻቻል የሚለውን ነገር በመስበክ ብቻ ይሆናል፡፡ መቻቻልም የህግ የበላይነትን ምንግዜም
አይተገብርም፡፡ በቸር ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen