Donnerstag, 3. April 2014

መስራት ያቆመ ገበሬ ፍሬን አያይም

መስራት ያቆመ ገበሬ ፍሬን አያይም

ነፍስህ የምትፈልገውን የምታውቀው እራሱዋ ናት፡፡ ልብ ወደጽድቅ ስለሚጠማ ነው ሁልግዜ ስለእግዚአብሄር የምንናገረው እንጂ ምንአልባትም ጻድቅ ሆነን ላይሆን ይችላል፡፡ ሀሰትም እየሰራን እና እየተናገርን ስለእግዚአብሄር መናገር በጣም የሚከብድ ነገር ነው፡፡ ሁሉም ደግሞ እግዚአብሄርን ይፈልጋል፡፡ ሁሉም፡፡ ባይፈልግ ሁልም እየተደበቀ ሀጢያትን ባልሰራ ነበር፡፡ የሚደበቀው ከሰው ብቻ ሳይሆን ከእራሱም ነው፡፡ ሁለት ነገር በውስጡ አለ፤ አንዱ ውሸት አንዱ ሀሰት ነው፡፡ በአገራችን ያለውን ሁኔታ ወይም የሰውን ልጅ ክፉ አስተሳሰብ ለመቀየር እንኩዋን የፔንጤ ምእመናን ብቻ 18 ሚሊዮን በላይ ቁጥሩ መድረሱን እንሰማለን፡፡ ግን ይህ ቁጥር ምናአልባት መልካም አረአያ ቢሆን ኖሮ፤ ደግሞም መልካም አስተማሪ ቢሆን ኖሮ የአገራችን እስተሳሰብ እና እይታ በበጎ በተለወጠ ነበር፡፡ ከዛም አልፎ የጸዳን ቢሆን ኖሮ እግዚአብሄርም የተለዬ ታአምሩን ተጠቅሞ ለምድሪቱ የተትረፈረፈ በረከት መረጋጋትን ባመጣ ነበር፡፡ ግን ዛሬ በኢትዮጲያ የሰፈነው ፍርሀት፣ ሙስና፣ ማታለል፣ እራስን ወዳድነት ሆኖአል፡፡ ያሳዝናል፡፡ ቀድሞውኑ ኢትዮጲያ ስንት ሰው በሀሰት ደሙ የፈሰሰበት እምባ እሪ ኡኡ የምትልበት አገር ላይ እና ደግሞም አሁንም በተለያየው መልኩ ሕዝብ በነቂስ እየወጣ የሚሰደድበት አገር ላይ ቀዳሚው ስራ ምን እንደነበር ቤተክርስቲያን ማወቅ ነበረባት፡፡ቀድሞ የሚያስደስት ነገር አይምሮአችንን ለንስሀ ዘመን የዘጋ ስለሚሆን፤ ለተጨማሪ ቀውስ እንደምንዳረግ ማወቅ ነበረብን፡፡ ግን ይህን ደፍሮ የሚያስተምር ባለመኖሩ አረማመዳችን እየሳተ እምነታችን የይምሰል እየሆነ ሄድዋል፡፡ እግዚአብሄርንም የምንሰጠውን አደራ ላይፈጽም ይችላል ብለን በጥርጣሬ ውስጥ እንድንገባ ተገደናል፡፡ ይህ ጥርጣሬም ሰው የእራሱ ደመወዝ ከፋይ በመሆን፤ በፈለገበት መንገድ ይሁን ለመክበር እሩጫ ተያይዞታል፡፡ እኔን ልቤን የማረከኝ ወንጌል በሰው ባሕሪ ግን ከባድ ፈተና ላይ እንደወደኩ አውቀዋለሁ፡፡ እግዚአብሄር የለም የሚለው ደረጃ ላይ ባልደርስም ግን ቤተክርስቲያን ያጣሁበት እና መንፈሳዊ መጨናነቅ የደረሰብኝን ሁኔታ እንዳለ አውቀዋለሁ፡፡ቤተክርስቲያን የሚገባትንም ምእመናን አዘጋጅታ ካላቀረበች ሰውን መንፈሳዊነትን የሚያረጋጋ ነገርም አይኖረም ማለት ነው፡፡ ስጋዬን ለማወፈር ቤተክርስቲያን መሄድ የለብኝም፡፡  ከአንዱ ወደአንዱ በናፍቆት እና በፍቅር ልሂድ እንጂ የፈለኩትን የመንፈሳዊ እርካታ ያገኘሁበት አይደለም፡፡ ምድሪቱዋን ወንጌል ይለውጣታል ማለት አስተሳሰባችንን ወደሰብአዊነት ያመጣእና፤ የሰው ልጅ በእርህራሄ ተነስቶ ስግብግብነትን፣ እራስን ወዳድነትን እና ሀሰተኝነትን እንዲተው እና ወደጽድቅ እንዲመጣ ነበር፡፡ ግን ቤተክርስቲያን ደፍራ ይህንን ከማስተማር ቀድማ የገባችው ወደ ደስታ ታላቅ ድል እንደተቀዳጀች እና ምንም አይነት ስራ እንደለላት ሆኖ አይቸዋለሁ፡፡ በዚህም ውስጤ ይሰቃይ ነበር፡፡ የክርስቲያን ድሉ ምድሪቱን ወደመረጋጋት ማምጣት እና የሰው ልጅ ወደሰማያዊ አለም የሚመጣበትን መንገድ እንድናይ እንድናሳይ አርአያ መሆን ነበር፡፡ ዛሬ ግን ይህ በመካከላችን ሊኖር ቀርቶ እርስበእርሳችን የምንወዳደርበት የምንፎካከርበት የምድር ቀውስ ውስጥ ገብተን መዳከር ይዘናል፡፡ ክርስቲያን ማታለል፣ መሸንገል እና ማዳላት ውስጥ ዘው ብሎ የተዘፈቀበት ሁኔታ የስጋ ሕይወት ሆኖ እየታዬ ነው፡፡ ዛሬ መንፈሳችን በእጅጉ ተጨናንቆ ሊፈነዳ የደረሰበት ሁኔታ ላይ የደረስን ሰዎች አለን፡፡ ሌላውን ሀይማኖት ሳልነካ ነው እንግዲሕ ስለጴንጤው ይህንን ልናገር የደፈርኩት፡፡ ድል ድል ይሸተኛል ብሎ ተዘመረ እንጂ ድል መጥቶአል ማለት አይደለም፡፡ ክርስቲያንነት የሌላው ጠላት መሆንም አይደለም፡፡ ክርስቲያንነት ሌላውን መረዳትም ነው፡፡ ሰው ሲከፋው ሲጨናነቅ እና ግራ ሲገባው ወደቤተክርስቲያን መሮጡ ይህ የሚሳቅበት የሚፌዝበት አይደለም፡፡ እንግዲሕ በክርስቶስ ያመነ፤ ክርስቶስ እራሱ መዳኒት የሚሻ ነው ወደእኔ የሚመጣ ብሎ የተናገረው መንፈሳዊው ተንቢቱ ነው፡፡ ሰው በሚሰቃይበት ነገር ላይ ወደ ቤተክርስቲያን ቢሮጥ መንፈሱ አድራሻ ስላሳየው እንጂ ሌላ ጉዳይ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር እየቀሰቀሰ መንፈሳዊ ምግብ ወዳለበት ይልካል፤ ያመጣል፡፡ ይህ የመንፈስ ጉዳይ ነው፡፡ እዛ ግን መጥቶ ተጽናንቶ የሚወጣው ያሸበረቀ ልብስ ስላዬ ወይም የቃላት ጎርፍ ብቻ ስለወረደ አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ክንድ የሚታይበት አንተ ክርስቲያኑ ቀድመህ እሩጠህ አቅፈሕ የምታጽናናበት፤ እምባ የምትጠርግበት ማሃረብ ከኪስህ ሲኖርህ ነው፡፡ ብር አይደለም የምልህ፡፡ ብርማ እራስህም ልትጠግበው የማትችለው ወይም የለለሕ ትሆናለሕ፡፡ ግን አንዱ ክርስቲያን ግሩፑን እንጂ ሌላውን ሊያይ የሚችልበት ሁኔታ እንደለለ እኔ አይቸዋለሁ፡፡ አለማዊነት የሚታይበት እንጂ መንፈሳዊነትን ለማየት ችግር ነው፡፡ የሚያሰቃይ እንዳውም እሁድን የመጠላበት ሁኔታ እንደነበረብኝ አውቀዋለሁ፡፡ በስደቱም አለም ቢሆን አንድ ሰው ላይ አለም ያወጀችበትን ወሬ ቤተክርስቲያንም ስትቀበለው እና ሰውን የምታገልበት ሁኔታን ተጋፍጫለሁ፡፡ እንኩዋንም ሌላውን የሚለውጥ ምሳሌ ሊኮን ቀርቶ ፌዝ ቡዋልት እና ቀልድን ተለማምጃለሁ፡፡
ብዙው በቁዋንቁዋ ሲናገር እኔ አልናገርም ነበር፡፡ ያም ክርስቲያንነቴን ዝቅ የሚደርጉትን ሌሎች አማኞች አይቻለሁ፡፡ እኔ ግን እስከዛሬ ድረስ በሌላ ቁዋንቁዋ ልናገር የቻልኩ አይደለሁም፡፡ ሰውን ለመመሳሰል ብዬ ያልሆንኩትን ነው ብል ተገቢነት የለውም፡፡ ይህ የተሰጣቸው ሰዎች ካሉ ደግሞ እኔ ልቃወም አልችልም፡፡ እውነቱ ያለው እነሱ እና እግዚአብሄር ውስጥ ነው፡፡ ከመፍረድ መቆጠብን እመርጣለሁ፡፡ ግን እየሱስን ብዬ ክርስቶስን ብዬ ወደቤተክርስቲያን ተጉዣለሁ፡፡ ይሁንና ልቤን የሚያረካኝ ቤተክርስቲያን ግን አልገጠመኝም፡፡ ብቻዬን እንደገባሁ እስከዛሬ ብቻዬን ከቤተክርስቲያን ውስጥ እወጣለሁ፡፡ ይህ በኢትዮጲያዊያኖች አካባቢ የሁት ልምዴ ነው፡፡ ምንአልባትም ዘመኔን ሁሉ በእንደዚሕ አይነት ሁኔታ አልፌ አልፍ ይሆናል፡፡ ግን ተምህርቱን የሚሰጡትን በደንብ አዳምጬ አላምጨ እውጣለሁ፤ መንፈሴም ሊመገብ የሚችለውን በመመገብ እገኛለሁ፡፡ ይህም ስለሆነ አይኔ ሁልግዜ ክርስቲያን ፍለጋ ይባዝናል፡፡  ክርስቲያን ነን የሚሉ መካከል ተገኘሁ ማለት ክርስቲያን አገኘሁ ማለት አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያንም እሄዳለሁ ግን እኔ ለእነሱ ሁልግዜ አዲስ ነኝ እንጂ በመካከላቸው ወይም በእየሱስ ውስጥ ምን ያህል ዘመን እንደቆየሁ አያውቁትም፡፡ መንፈሳዊ ሕይወትንም አንዱ አንዱን ይመሰክርለታል እኔ ግን ማንም አጠገቤ ስለለለ የሰው ምስክርነትን አግኝቸም አላውቅምእና ወደ እነሱ የሚደበልቀኝም አላገኘሁም፡፡ ለነገሩ እግዚአብሄር ለመንፈሳዊ ማንነቴ ምስክር አይጠራም እንጂ ቢጠራ እኔ በዜሮ እወጣ ነበር፡፡ ዛሬ እንደነበረው ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰፍ አልልም፡፡ አንድ ነገር ተረዳሁ እየሱስ የግል አዳኝ እንጂ የጅማላ ባለመሆኑ ግሩፕ ውስጥ ባልገባም ለመንፈሳዊ ህይወቴ ትርጉም የለውም፡፡  ሁሉ አገለለሽ ብሎ እግዚአብሄር የእኔን ማንነት ገደል አይከተውም፡፡ ውድ ወገኖቼ የሁሉም ሚዲያ ሰው እራሱ ለመረጠው ሰው የተሰጠ ነው፡፡ እሱንም ሊሰሩበት አልቻሉም፡፡ የእግዚአብሄር ሚዲያው ግን ድፍረት ብቻ ነው፡፡ የበረሀው ድምጽ ምሳሌ ይሁናችሁ፡፡ ምግቡ አንበጣ ባይሆን ዩሐንስ መጥመቁን የድፍረት ድምጽ ይዞ ማን ያበላው ነበር፡፡ ደግሞስ በበረሀ ባይኖር ማንስ በከተማ ያስጠጋው ነበር፡፡ እውነት ነው እሱ ምሳሌ ሆነልኝ፡፡ በድፍረት የሚወጡ ቃላቶች ጉዋደኛ፣ ዘመድ፣ መንግስትም ያሳጣሀል፡፡ ብቻሕን ነሕ፡፡ ብቻህን፡፡ እሱ የድፍረትን ማጉሊያ የሰጠህ ካልጠበቀሕ ማን ይጠብቅሃል፡፡ አንተ ቤተክርስቲያንንም ብትይዘው፤ መሰረቱ ግን ክርስቶስ መሆኑን አትዘንጋ፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ አንዳንዶቻችን በሰዎች መካከል ደምቀን አብበን አምረን ስንኖር፤ አንዳንዶቻችን ደግሞ ተደብቀን፣ ተሸማቀን፣ ተሰድበን፣ ተንቀን፣ ተዘርፈንእና ተገለን እንኖራለን፡፡ እንባችንም እንደቦይ ውሃ እየፈሰሰ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ እንላለን፡፡ አዎ የዚች አለም ነገር የፍርሀት ድባብ ትለቅብናለች፡፡ ህይወት እንግዲሕ አንዱ ከእግዚአብሄር ተደብቆ ይደሰታል፤ ሌላው ለእግዚአብሄር እራሱን ግልጽ አድርጎ ያለቅሳል፡፡ አዎ እጅግ መራራ ጥፋቶች በኢትዮጲያ አሉ፡፡ አሰልቺ የሆኑእና ምን ልግባ የሚያሰኙ ችግሮች ከእለት ወደእለት እየጨመረ ነው፡፡ ግን ቤተክርስቲያንስ አብራ አስለቃሽ ትሆን ወይስ አርአያ???????
ባዩሽ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen