ማስተዋሻ፤ ለመሆኑ ኢህአዴግ
ምን ያህል ያለውን ብልሹ አስተዳደር እንዲቀይር እና ይህንንም ለመቀበል ዝግጁ ነን፡፡ ይህን የምልበት ምክናያት እስከዛሬ ስለተበላሸ
የሚያስተካክለውን ነገር አንፈልግም አንቀበልም ነው የምንለው? ይህንንስ ካልን፤ ኢህአዴግ የሚቀይረውን የሚያስተካክለውን የማንቀበል
ከሆነ፤ የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ሁሉጥቅሙ ምንድን ነው ? ሰላማዊ ሰልፍ የሚደረገው፤ መልስ ለማግኘት ነገሮችን ለመቀየር ይመስለኛል፡፡
መንግስትን ለማውረድ በሰላማዊ ሰልፍ አይቻለም፡፡አንድ በምርጫ ፣ በጦርነት አልያም በአመጽ ነው፡፡ በቃ ባህሪው በአለም ዙሪያ ይህ ነው፡፡ ሰው ፕሮቴስት የሚያደርገው ለመደመጥ እና መልስ ለማግኘት ነው፡፡ ገዳይ ለፍርድ ይቅረብ፤ ወይ የህል ዋጋ ይቀንስ
፤ አልያም ብልሹ አስተዳደር ይቀጡ፤ ሙሰኞች ይታሰሩ መሰል ነገር
ማለቴ ነው፡፡ በሰላማዊ መንገድ መልስ ለማግኘት ነው፡፡ ይህንን የሚያስረዳኝ
ባገኝ ደስ ይለኛል፡፡ የሚያስተካክለውን ለመቀበል እና አጋዠ ካልሆንን የሰላማዊ ሰልፉ ጉዳይ ውጤቱ ምን እንደሚያመጣ አልያም ወዴት
እየወሰደን እንደሆነ ማስተዋል ግድ ይለናል፡፡ ነጻ ሀሳብ በመስጠቴ የሚያኮርፍ ካለ፤ ካለመንቃት ጋር አያይዘዋለሁ፡፡ እኔ ከማንኛውም
ፖለቲካ ፓርቲ ነጻ ነኝ፡፡ አስተሳሰባችን ግን እንዲያድግ ተናገርኩ፡፡ እኔም የማላውቀውን ለማወቅ፡፡ ያልገባኝን ለመረዳት፡፡ ከተሳሳትኩ እኔ አለመንቃቴ ስለሆነ የሚያነቃኝ ያስፈልጋል እንጂ የሚቆጣኝ ወይ
ጥግ አሲይዞ ከጫዋታ ውጭ የሚደርገኝ ኩነና አልፈልግም፡፡ አይመቸኝም፡፡
ማንም ቢሆን ካለመነጋገር ማንንም ማስገደድ እንጂ ማሳመን አይችልም፡፡ ሰው በሚያየው ተጨባጭ ሁኔታ ማገናዘብ
የለመደበት ግዜ እንዲሆን የአለም ማህበራዊ ሚዲያዎች ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ ለዚህ ነው ፖለቲከኞች የእምነት መሪዎች እና
የተለያዩ ተቁዋማት ዲሞክራሲን ማሰብ እና በስራቸው ያለውን ሰው ያወቀውን
መቀበል ያላወቀውን እንዲያውቅ መጣር ያለባቸው፡፡ እስኪ ልብ እንበል፤
ከኤሽያ፣ ከአረብ አገሮች እና ከአፍሪካ የህዝቡ ፍላጎቱም ስላደገ
በትልቁ ዲሞክራሲን በመፈለግ ብዙ ህዝብ ወደኢይሮፕ እና አሜሪካ መፍለስ
ይፈልጋል፡፡ ሰው በተፈጥሮው ነጻነት የሚፈልግ ነው፡፡ እራስን የማዳን ጥበበኛ ነው፡፡ ሰው ማለቴ ነው፡፡ የአስተሳሰብ እና የባህሪው ነጻነት፡፡ ይህ ከሆነ ስንቶቻችን ነን እኛስ አሁጉር
ወይም አገር ይህንን ለመጋበዝ ጥረት የማናደርገው? እኛ እዛ ከምንሄድ አስተሳሰቡ እዚህ እንዲመጣልን እንጣር የማንለው? አንድ ነገር
በመፈለግ ያለህበትን አገር እየለቀክ የምትሄድ ከሆነ የምታጣውም እናዳለ ልብ ማለት ያሻል፡፡ ያም የምታጣው ነገር፤ መንፈስን የሚያስጨንቅ፤ ወይም ክፉ የማድረግ እና በጥላቻ
እንድትሞላ የሚያደርግህ ባህሪ ሊያስገነባህ ይችላል፡፡
በኢይሮፕ ያለው የመናገር ነጻነት ብቻ ነው፡፡ ማንም ይናገራል፡፡
ግን ጥላቻን ብቀላን የሚያመጣ ነገር አይፈልጉትም፡፡ ይህን የሚያደርጉት በአካባቢያቸው ያለው ሰላም እንዳይደፈርስ ነው፡፡ አንተ
ግን ጥላቻ በአገርህ አካባቢ ላይ ብትሰብክ ተሰነጣጥቀህ ተከፍለህ ብትቡዋቀስ ደም እስካልተፋሰስክ ድረስ ሊያቆሙህ አይችሉም፡፡ ፍላጎቱም የላቸውም፡፡ ምክናያቱም በዚህ ጉዳይ ላይ የነሱን ማለትም የስደት አገርህን ካልነካህ እነሱ
ተው ቢሉ እንደጣልቃ መግባት ሊያዩት ይችላሉ፡፡ አልያም በቃ እራሳቸው ካላሰቡ እኛ ምን እናድርግ ሊሉ ይችላሉ፡፡ እነሱም እንዲሁ
የዛሬ 100 አመት አሳልፈውታል እና፡፡ ዛሬ ግን የብሄር የሀይማኖት መቡዋቀስ 90% አጥፍተውታል፡፡ ስለኢይሮፕ ካወራን ነው፡፡
ጥቂት ወግ አጥባቂ ክፉ እና የማይረዳ አሁንም ይገኛል፡፡ ይሁን እና ግን
አገር ለማፍረስ አስጊ አይደለም፤ ምክናያቱም በበላጩ ህዝብ የድምጽ የበላይነት በህግ የበላይነት አስተሳሰቡ የታሰረ ነው፡፡
አዲሱን ናዚን አሁን ያለውን በማስታወስ ልብ እንድትሉ የማስታውሳችሁ፡፡
ይህም ይሁን ብለው አልተውቱም፡፡ ይህንን የተለየውን ወግ አጥባቂ
እና ጠባብ ለማጥፋት ሳይሆን ለማስተማር ለመለወጥ እጅግ ብዙ ገንዘብ ኢንቬስት ያደርጋሉ፡፡ ሰውን አለማወቅ አለመረዳት አለመገንዘብ ወደጥላቻ እና ዘር ማጥፋት ወንጀል
እንደሚያመጣው ስለሚያውቁ ነው፡፡ ለዚህ በስልጣን ያሉ ፖለቲከኞች ይጠነቀቃሉ፡፡ ይህንን አስተሳሰብ ለመለወጥ አይምሮው እንዲያስብ
ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ ጥፋቱ ከሰው ስጋው ሳይሆን ከአይምሮው መሆኑን ደርሰውበታል፡፡ ስለዚህ አስተሳሰቡ የሚመታበትን ነገር ለማድረግ
እና የሰው አስተሳሰብ ወደሰብአዊነት እንዲመጣ ለማድረግ ወጪ ያወጣሉ፡፡
አይምሮ የተሰራው ለማሰብ እና አካባቢህን እንደትመለከት
እንድትጠብቅ ነው፡፡ የኢህአዴግ ፖለቲካን አንዱ ያበላሸው የሰዎች መስገብገብ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህም ስንለው የቆየው እራሱ
ፓርቲውም ያመነበት ነገር ቢኖር ብልሹ አስተዳደር እና ኪራይ ሰብሳቢም አስቸጋሪነቱን የተናገሩት መሆኑ ነው፡፡ በስም እየጠቀሱ ተናግረውታል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢ ማለትን ነው፡፡ ሙስና መሰለኝ፡፡
መሞዳሞድ መሰለኝ አባባላቸው፡፡ እናጸዳለን ይላሉ፡፡ ግን ምን ያህል
እውነታ አለው የሚለውን የሚያውቀው እዛው የሚኖረው ህዝብ ነው፡፡ አስቸጋሪ መሆኑን ግን የምገነዘበው፤ የሰው ፍላጎቱ ጣራ እየዘለለ
ስለሆነ እና „ከየትም አምጭው ዶቄቱን
ፍጭው“ ስለሆነ አስቀድሞም
በቸልተኝነት ስለታዬ ቀላል አይሆንም፡፡ እስኪ ውነቱን እንናገር፤ እውን ኢህአዴግ ይህንን ስራ ለመስራት ቆርጦ መነሳቱን ለተሰላቸው ህዝብ ምን ያህል እውነት እንደሚሆን የሚያስረዳበት
መንገድ ሰፊ ነው ወይ? ይህንን እራሱ እንደ ህዝብ ሳየው፤ ችላ ብለን እጎን ያለው ቢያለቅስ ምን አገባኝ ካልን እና፤ ወንጀል ሲሰራ ዝም
ካልን ዋጋ ከፋዩ እራሱ ህዝቡ ይሆናል፤ ማንኛውም የፖለቲካ ሲስተምም ቁም ነገር ሳይሰራ ያልፋል፡፡ ፖለቲከኞችም ከወንጀል ያልጸዱ
ሆነው መታየታቸው አይቀርም፡፡ በአለም የምናየው የፖለቲካ ባህሪ እንዲሁ ነው፡፡ አንድ ነገር በህይወቴ የተረዳሁት ነገር ቢኖር፤ ያልነቃ ህዝብ ፖለቲካ ደጋፊም
ሊሆን አይችልም፤ ግን ተቃዋሚን ደጋፊ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክናያቱም ሆድ የሚያስብስ ባህሪ ብዙ ካለ ተናዳጅም ለመሆን በጭራሽ አያዳግትም፡፡
ስለዚህ ህዝብ ቢነቃ ለፖለቲካው ትልቅ አስተዋጽኦ ስላለው፤ መሆን የነበረበት፤ እንዲነጋገር፤ ችግሮችን በይፋ በአደባባይ ፊት ለፊት
እንዲነጋገር የኢትዮጲያ መንግስት ህዝቡን ወደአድባባይ መድረክ እንዲያመጣ
የሚያደርግ ሲስተም 25 አመት ሙሉ አድርጎ በነበር በተሻለው ነበር፡፡
ካልሆነ የተቃዋሚ መድረክ ይፈልጋል፡፡ እዛም የሚያወራው ለኢህአዴግ
የተመቼ አይሆንም፡፡ ግልጽ ነው፡፡ የተቃዋሚ ወሬ በአለም ላይ የሚሆነው፤ የህዝብን የልብ ትርታ ማዳመጥ እና መጠቀም ነው፡፡ ይህንን
በስልጣን ያለው ፓርቲ ቀድሞ ማዳመጥ እና ችግሩ እንዳይሰፋ ማድረግ ነበረበት ባይ ነኝ፡፡ እሱ ያላነሳውን የደበቀውን የሚያነሳው
ምንግዜም አለ፡፡ የተቃዋሚን ባህሪ ገዢ ፓርቲ ካወቀ ይጠነቀቃል እንጂ ቁጡ መሆን አይገባውም፡፡
እኔ እስካልተነካሁ ሌላው የእራሱ ጉዳይ የሚል አባልተኛ
ተይዞ ፤ እራሳችንም ህግን አጣመን ለማስፈረድ ነገሮችን ለማስፈጸም
በምንጥረው እና በምናደርገው ሙከራ እራስ ወዳድነት ባህሪ፤ አገራዊ ፍቅር ቀርቶ የብሄር ፍቅርም እንደተባለው መገንባት አይቻልም፡፡
ልብ እንበል፤ ኢህአዴግም ሆነ ተቃዋሚም አባል ቢያበዙ ሁለቱም ከአንድ
ህብረተሰብ እንደሚወስዱ ማመን ነው፡፡ ስለዚህ ባህሪው አንድ አይነት፣ የአስተሳሰብ ባህሉ አንድ አይነት ከሆነ ህዝብ ማለት ነው፡፡
ስለዚህ አባሌ ምን ያህል በእውነት እና በእምነት አገራዊ ፍቅር ገንብቶአል
ማለት እና መጠየቅ ይገባናል፡፡ በየእራሳችን ፍላጎት፣ ስለእራስ ማሰብ አገራዊ ፍቅር አያመጣም፡፡ አገራዊ የእድገት ስሜትም አይኖረውም፡፡
ሁሉ ነገር ከጥቅም ጋር የተያያዘ ይሆናል፡፡ ስለሆነ እኛም ሀላፊነትን
መወጣት እንደህዝብ መማር አለብን፡፡ ይህንን ብዙ ግዜ ተናግሬዋለሁ፤ በነገሩ ተጠቂ ስለሆንኩ፡፡ ይህም ማለት ባለስልጣንን ለማባለግ
የሚደረጉ ጥረቶች እና ስግብግብ ሰዎች የሚወስዱት ጨካኝ እርምጃ ነው፡፡ የፈለገ ይሁን በላየድትህ ላይ ይራመዳል፡፡ ለማንም ግድ
የለውም፡፡ ይህ ብሄርን ከብሄር አይለይም፡፤ ልብ እንበል መላው የኢትዮጲያ ኅዝብ በቁዋንቁዋ ሊለያይ ይችላል፡፤ ባህሪያችን ግን
በአንድ አምባገነን መንግስታቶች የተገዛን ሰው ያለው ነው፡፡ ፈሪ እና አድርባይ፤ የእራስ ጎጆን እራስን ማዳንን የምንመለከት፡፡
ዳር እስከዳር አንድ ነው፡፡ በሁሉም ጥሩ አለ መጥፎ አለ፡፡
ብልሹ አስተዳደር እና ኪራይ ሰብሳቢ አልያም ሙሰኛ እና
መሞዳሞድ የሚቀረው፤ በሁሉም ክልል የሚኖር ህዝብ እኩል ንቃተ ህሊና ሲያገኝ ብቻ ነው፡፡ ሌላው አሁን አሁን ጎልቶ የሚወራው በክልሎች
የድንበር አካባቢ ያሉ ሁኔታዎች ጉዳይ ነው፡፡ የወሰን ጉዳይ፡፡ እንደእኔ በደንበር አካባቢ ያሉ አገሮች ጉዳይም መቁዋጫ የሚያገኘው እና ዘላቂ መፍተሄ
የሚያገኘው፤ በማንኛውም ክልል የህግ የበላይነት ፣ እኩልነት እና
ዲሞክራሲ እውን ሆነው ሲገኙ ነው፡፡ ሌላው አይጫነኝም የሚል ስሜት እና እምነት ሲገነባ ነው፡፡ የአይምሮም ስራ በዲሞክራሲው ላይ
ሲኖር ይኖረዋል፡፡ ያነዬ አውራጃዎች ወዲያ ወዲህ መሆን አያስጨንቀንም፡፡ ምክናያቱም እዛም ብሄድ ያለው
ህግ እዚህ ስላለ፤ እዚያም ያለው እኩልነት እዚህም ስላለ የወሰደ ቢወስደኝ የሚል ብልህነት ሲመሰረት ነው፡፡አሁን ባለው ሁኔታ ግን
ከባድ ይሆናል፡፡ ሰው በብሄሩ እበደላለሁ ብሎ ካሰበ አስቸጋሪ ነው፡፡ እንግዲህ ኢይሮፕ የፈረንሳይም ሆነ የጀርመን ህግ በመሰረታዊ ችግሮች እና በስብእና
በህግ የበላይነት አንድ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ወሰን ላይ ያሉ አገሮች ወዲያ ወዲህ ቢሉ ትልቅ ቴማ አይሆንም፤ ህዝብም አይደነግጥም፡፡
ይህ የሆነው ዛሬ ከአደጉ በሁዋላ ነው፡፡ በፌት ተዋግተውበታል ተጋለውበታል፡፡
ስለዚህ ሁሉንም ነገር ለማቃለል መጀመሪያ መሆን ያለበት በሁሉም ክልል እኩል የሆነ መሰረታዊ ዋስትና አስቀድሞ መገንባት ነው፡፡
ከዛ የቀደመ ድርጊቶች ጦርነት ጋባዥ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እናም በመጨረሻ የምለው፤ ማንኛውም ፖለቲካ እና ፖለቲከኞቹ አብረው የመስራት
አቅም ካልገነቡ፤ ህዝቡን በመከፋፈል እንደሚጎዶት ልብ እንበል እና፤ ሁሉም ወደዲሞክራሲ ይምጡ እላለሁ፡፡ ሰላም የብዛላችሁ፡፡
ባዩሽ አበበ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen