Sonntag, 29. Juni 2014

የህይወት እሩጫ የሚያቃትተው ወጣት፡፡



የህይወት እሩጫ የሚያቃትተው ወጣት፡፡

ሰው ችግር ብቻ ሳይሆን ስራ ፍለጋ የሚሩዋሩዋጠው፤ እድገትም ፍልጋ መሆኑን እያየን ነው፡፤ በአንድ ሞሰብ መብላት ቀርቶ፤ ሁሉም የተቆረጠ እንጀራውን ይዞ መሮጥ ከሆነ ወዲሕ፤   ለአስር ሰው አንድ ሰው አስር ሰሀን መግዛቱ ከወሰነ ወዲህ ኑሮ አልቀለለችም፡፡ ስልጣኔ ምቾት ናት ግን ችግርን አብዢም ናት፡፡   ለአንድ ልጅ አንድ መኝታ ቤት ማሰብ፤ እና ግራውንድ ፕላስ ቤት መመኘት አልያም ቪላ ፤ እድገት በእደገት ከሆነ ወዲህ የሰው ልጅ እግርአውጭኝ፤ ብር ስጭኝ ሆኖአል፡፡ ዘንድሮ ብቻ ሳይሆን መቼም ፤ታችአምናም በአገራችን አንድ ሰው ከአንድ ቤት ጠንካራ አይጠፋም እና፤ ብዙ ሰው ይዞ ለመብላት ግድ የለዋል፡፡ የተባረከ ቢጣልም እንደዮሴፍ አንድ አልጠፋም በኢትዮጲያ፡፡ ስራ መፍጠር በየአገሩ ወጣቱ ተያይዞታል፡፡ የመጣበት የስራ ማጣት ሁኔታ እራሱን ስራ ፈጣሪ እንዲያደረገው መርጦአል፡፤ ለምሳሌ ከደቡብ አሜሪካ ወደታላቂቱ ሰሜን አሜሪካ በድብቅ ድራግን እየወሰዱ የሚሸጥ፤ መነገድእና ቁጥጥሩ ከባድ እና አስጊ እየሆነበት የመጣው ወጣት ነጋዴ፤ ዛሬ ብዙው ከፖሊስ ጋር ምን አታገለኝ እያለ የስራ ዘርፍ ለመቀየር ተገዶአል፡፡  ሕጻናቶችን በድብቅ ባልተፈቀደ መንገድ ወደሀብታሚቱ አሜሪካ ለማሻገር ደቡብ አማሪካዊ የሆነ ገንዘብ ከፋይ አልጠፋም፡፡ ይህም ወንጀል ቢሆንም እንደድራጉ ትልቅ ሪስክ ገና ስለሌለው፡፡ ስራ ፈጠራ ይሉሃል እንዲህ ሆኖአል፡፡ የሚያዋጣ ቢዝነስ፤ ከደሃ አገር ወደሃብታም አገር ሰው ማሻገር፡፡ የአንዳንድ አገር ፖሊሶች የሚሰሩት አላጡም፡፡ ከአንዱ የስራ ዘርፍ ወደሌላው የሚሩዋሩዋጠው ወጣት ስራ መፍጠር እንዲሕ ቀላል መሆኑን ያሳያናል፡፡ ለነገሩ ኢዮሮፕም የፈለገችውን ጥረት ብታደርግም እና ወሰኑዋን ማንም እንዳይገባባት ብታጠናክርም፤ ከወሬ ሊያልፍ ያልቻለው፤ ወጣት ስደተኛ እንደጎርፍ ይገባ ይዞአል፡፡ አስተዳደሩ እንዴትም  እንደሚገቡ ማወቅ የተቻለው አይመስልመ፡፡ ስራ ፈጣሪዎች አሉእና ስራን እንዲሕ ይፈጥሩታል፡፡ ሁሉም በድብቅ በብልጠት የሚሰራበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፤ የሰው ልጅ መከራ ሲበዛበት ማን ነው ያብዳል ብቻ የሚለው፡ አይምሮውም ይፈጥራል እንጂ፡፡ ሰው የሚባለው ፍጡር ከእንሰሳ የሚለየው ሕይወቱን ለማዳን የሚወስደው የእርምጃ ጥበብ ነው፡፡ አይዞን፤ አንዱ ቢጠፋም፣ እጽዋቶች በተበላሸው አየር ሊጠፋ ቢዳዳቸውም፣ ደግሞም መሬት ብትንሸራተትም ፣ በረሃው ቢሰፋ ፣ አውሎ ንፋስ የቀላቀለው ንፋስ ቢያስቸግርም፣  አለምን እንጠብቃት ልትጠፋ ነውእና እያለ ተቆርቁዋሪ ቢለፍፍም፤ አይዞን ሰው ጠፋል እንጂ አይጠፋም፡፡ ጥበበኛ ነኝ የሚለው የሰው ልጅ  ነፍሱን ላመትረፍ ይጥራል፤ ዘዴ ይዘይዳል፣ ይገላል ይሰርቃል፣ ይማራል ይመራመራል፡፡ በሬሳም ላይ ተረማምዶ ቢሆን፤ እኔ ግን እኖራለሁ እተርፋለሁ ብሎ አፍጥጦ እና ደፍጦ እያየነው ነው፡፡ እራስ ወዳድነቱን የሚያሳየው የሰው ልጅ፤ እንሰሳትን በልቶ፤ እጽዋትንም ጨፍጭፎ፤ ጌሾንም ተጎንጭቶ ቢሆን አዎን የተርፋል ይኖራል፡፡
በዚህም የተነሳ ከወደአገሬ ኢትዮጲያም ወሰንን በመሻገር ጥበብ ያካበተው አገሩን ትቶ ወደኢሮፕም መጉረፍ ይዞአል፡፡ ግን ከእንግዲህ የኢይሮፕም ኑሮ ቀለል ብሎ አለመታየቱን እንየው፡፡ ለምን መጣህ ብቻ አይደለም ጥያቄው እንዴት ገባህም ቀላል አይሆንም፡፡ በየቀኑ ዘዴውን የሚቀያይረው አገባብ፤ ፈተናው ብቻ ሳይሆን ግቡንም ሳይመታ እየቀረ አላማውን ግብ ማድረስ ያቃተው ወጣት ሆድ እያስባሰው ይገኛል፡፡ የቅዠት ህይወት መጡብኝ፣ አዩኝ እና አላዩኝም የሚለው የእብደት ዳር ዳሩ ጭንቀት እየወረሰው የመጣውንም ስደተኛ ቁጥሩን መናገር ይከብዳል፡፡ አገባቡ ላይ እንጂ አኑዋኑዋሩ ላይ እጅግም ኢንቬስት ያላደረገው ወጣት፤ ወይኔ ገንዘቤን አውጥቼ ብሎ የሚቆጭም አልጠፋም፡፡ እንግዲህ ከአገር ከወጡ መውጣት ቀላል አልሆነም፡፡ ማን ያንን ይፈልጋል? እንዴት ልመለስ የሚያሰኘው ብቻ ፍርሃት ሳይሆን፤ ያወጣሁትን እንኩዋን ሳልተካ፣ የተበደርኩትን ሳልመልስ የሚለው እራስ ምታት ሆኖአል፡፡ ቁዋቅ የሚያሰኘው ምን ይዠ ልግባ እና ገብቸስ ምን ልሰራ አሞራ ይብላኝ ያለ ይመስላል፡፤ በዚህም ጉዳይ ላይ ማንም የሚነጋጋር የሚጫወት የለም፡፡ መቆዘም ሆኖአል፡፡ ብር መሰብሰብ አልተቻለም ግን አገር ላለመመለስ ዘዴ መዘየድ ብቻ ሆኖአል፡፡ ይህ መፍተሄ ሳያገኝ፤ በየቀኑ አዲስ የሚገባ በሽ ሆኖአል፡፡ በጀርመን ብዙም ያልተለመደው ዲፖርቲሽንም ወይም ተገዶ ወደኢትዮጲያ መመለስ ምንአልባትም እውን ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ ሳይከሰት አይቀርም፡፡ ይህን የሚያደርገው የፖለቲካው ምክናያትህ ነው፡፡ በብዛት የሚሰጡት የፖለቲካ ምክናያት አጥጋቢ አይደለም፡፡ ብዙው የሚለው ማደግ እፈልጋለሁ፣ መማር እፈልጋለሁ፣ ሰርቼ መኖር እፈልጋለሁ ነው የሚለው፡፡ ወዳጄ እዚህም መማር የሚፈልገው የተጨናነቀበት አገር ሆኖአል፤፤ ደግሞም ስራ ያጣውም ብዝቶአል፡፡ ማደግም የሚፈልገውም ቢኖር ያደገውም እያሽቆለቆለ የሚሄድበት ክስተት እየደረሰ ነው፡፡ አንድ አገር ስለሌላው አገር ስራ ማጣት ምንአገባው? እራሱም ስራ አጥ አለው እና ይልሃል፡፡ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ነውእና፡፡ ሁሉም እራሱን ለማዳን በሚፍጨረጨርበት በዚህ ክፉ ዘመን፤ የመኖር እና የኪስ ዋስትናንም ለመጠበቅ ሲባል አንድ ሴት ባሉዋን በሌላዋ  እንደምትነጠቅ ነው፡፡ እነዚህ አጋጣሚዎችም እየተያዩ በመሆናቸው፤ ፈረንጅ ባል ያላት ሴት፤ ሴት ጉዋደኛ ይዛ ለማስጠጋት ለመተባበር እየከበዳት ሄዶአል፡፡ ብቻ የፈለገው ይሁን አገሬ አልመለስም የሚለው መንገድ ለኢይሮፕ ቀሎ የሚታይ ጊዜ አልሆነም፡፡ እዚህ ድረስ መጥተህ ለፍተሕ እና ከስረህ ወይ ከማበድ፣ ከመሞት አልያም ዲፖርት ከመደረግህ በፊት ማሰብ ደንብ ነው፡፡ እውን ዛሬ የትም ሮጦ ማደግ ይቻላል ወይ? የሚያሳድግህስ እውቀት ይዘሃል ወይ? ከአገር የሚያሰድድስ የፖለቲካህ ሁኔታ እውነትነት አለው ወይ?  አይምሮሕስ የሚችለው ግፍ ምን ያህል ነው? መከራን ለማለፍ ተዘጋጅተሃል ወይ? እንግዲህ አገርህን ከመልቀቅህ በፊት እራስህን መዘን፡፡  ኢይሮፕ ስደተኛ እየበዛባት በመሆኑ እያንጉዋለለው እንደታምራት የሚዘፈንበት ትንቢት መሰል የዛር ዘፈን እውን መንጉዋለል እንዳይሆን ልብ በል፡፡ ሰሞኑን አንድ ሁለት ኢትዮጲያዊ ሴቶች ዲፖርት ልንደረግ ነው በማለት በፍርሃት፣ በእንቅልፍ ማጣት እና በመረበሽ አገኘሁዋቸው፡፡ የሚበሉት አላጡም አራባቸውም እንጂ አይምሮአቸውን ግን ለማጣት ጫፍ ላይ ደርሰዋል እና፡፡ አጥጋቢእና የታወቀ  የፖለቲካ ኬዝ የለለው፤ መንገድ አይጀምር፡፡ ስደት በፖለቲካ እንጂ የኢኮኖሚ ስደት አሳሳቢ ቢሆንም እዚህ ለመኖር በቂ ምክናያት አይሆንልህም፡፡ „ማር ሲበዛም ይመራል“ እንዲሉ፤ አንድ አገር ምን ያህል ህዝብ ይችላል የሚለው ጥያቄም ኑዋሪውን እያሳሰበው እና እያስቀየመው እየሄደ ነው፡፡ ሰው እራሱ ካልደላው፤ ስለሌላው የሚያስብ መለአክ አይደለም እና፡፡ በቸር ባዩሽ

Donnerstag, 26. Juni 2014

ተቃዋሚ ለታፈነው ህዝብ እንደፖለቲካ መሲሂ ሆኖ በናፍቆት ይጠበቃል፡፡





ተቃዋሚ ለታፈነው ህዝብ እንደፖለቲካ መሲሂ ሆኖ በናፍቆት ይጠበቃል፡፡

እንኩዋን ትክክል ሳይሰራእና ትክክልም ተሰርቶ ህዝብ በአገዛዙ ቢደሰትም፤ አንድ ብቻውን በስልጣን ለመቆየት የሚጥር ፓርቲ ትልቅ የታሪክ ስህተት እየሰራ መሆኑን መረዳት መቻል አለበት፡፡ አንድ ፓርቲ ብሎ ነገር የለም፡፡ አንድ ንጉስ እንጂ፡፡ ያም ሁዋላ ቀር ሆኖ ቀርቶል፡፡ አንድ ንጉስ አጥብቆ ቢይዝ ትንሽ ይሻላል፤ ስርአቱ እና የአገዛዝ የመጀመሪያው ደረጃ እንደዛ ሆኖ ባልሰለጠነው ዘመን ስለቀረበ፡፡ ንጉስም ሰው መሆኑን እያደር ሲታወቅ ግን በሁሉም አለም እየቀረ ሄድዋል፡፡ እዚህ ላይ እንዳንሳሳት፣ ዛሬ በኢይሮፕ ያሉ ነገስታቶች፤ ምንም አይነት የፖለቲካ የማዘዝ ሚና የላቸውም፡፡ ግን የኢይሮፕያን ነገስታቶች ላገራቸው በዘመናቸው ብዙ ጥሩ አስተዋጽኦ ስላደረጉ እንደ ሲንቦል ደመወዝ እየታሰበላቸው ይኖራሉ፡፡ ደመወዙም ህዝብ ከሚከፍለው ታክስ ነው፡፡ ጥሩ አድርገው ለአገራቸው የጣሉት ውለታ ዛሬ እንዲከበሩ ህዝብ እራሱ አምኖበታል፡፡ በዘመናቸው ግን መጥፎ ነገር አለንበረም ማለት አይደለም፡፡ ደግሞም አልሰሩም የተባሉት የሩሲያው ነገስታቶች አይሆኑ ሆነው እስከ ዘር ማንዘራቸው እንዲጠፉ ብዙ እርምጃዎች በተነሳው የህዝብ አመጽ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ „የቤት ቁዝምዝም እቃ ይፈጃል እንዲሉ ለህጻናት ልጆቻቸውም ቅጣቱ አልቀረም፡፡ በወቅቱ ራሽያ በአሰቃቂ እርሃብ እና መከራ ህዝቡዋ ወድቆ እነሱ የሞላቸው የተረፋቸው ነበር እና፡፡  እሱንም ለማስቀረት ንጉሶች ባሉበት አገር ሁሉ ከፍተኛ ሪቮሊሽን ተካሄዶአል፡፡
ዘወትር የምናየው ከአምባገነን በሁዋላ ደግሞ በጉሬላ ተዋጊዎች አምባገነን ሆኖ ይተካል፡፡ በተለይ አፍሪካ አካባቢ እንዲህ የተለመደ ነው፡፡ አምባገነንን ለማስለቀቅ የነበረው አማራጭ ይህ ብቻ ነው፡፡ አልያም በራሳቸው በከበባቸው መከላከያ  መገልበጥ፡፡ ንጉሶች ሲያገለግላቸው በነበረው ወታደራዊ ሀይል እዛው አጠገባቸው ባለው ስልጣን እንዲለቁ ቢደረግም፤ ወታደርን ግን መልሶ ለመጣል የግድ ለመብት የሚታገለው ቁጡው ሀይል አምርሮ በየጫካው ገብቶ ከዛም በሁዋላ ለስልጣን ይበቃል፡፡ ጫካም ከገቡ በሁዋላ ስምአውጥተው ብቅ ይላሉ፡፡  ወደአገር ሲገቡ ግን ስማቸው ሁሉ ለሕዝቡ ባይታዋር ስራቸውም የማይታመን ይሆኖአል፡፡ እንግዲሕ ህዝብ ተቀበለውም አልተቀበለውም ማሰብ ያለብን፤ ምንም እንኩዋን ምክናያት ይዘው ለትግል በየጫካው ቢሄዱም ዘመኑ ግን የአንድ ፓርቲ ዘመን መሆኑን መዘንጋታቸው መልሰው አምባገነንን ጥለው እራሳቸውም አምባገነን ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ዛሬም የሙጥኝ ብሎ በብቸኝነት ስልጣንን መያዝ፤ በህዝብ እይታ ውለታ ሆኖ ተቆጥሮ፤ ይህን ያህል ዘመን ስለተዋጋ በስልጣን ይቆይ የሚል አይሆንም፡፡ ጭራሽ እንዲፈሩ የሚያደርጋቸው፤ ከአገር ሲወጡ ተንጠባጥበው እና ስም የለሽ ሆነው ከዛም እዛው ስም ስለሚሰይሙ „ገቡ“ ወይም „ገባች“ እየተባለ ይነገራል፡፡ ይህንን ዞሮ ማስታወስ ይገባል፡፡ እንደነገሩ  ደርግ ስልጣን ሲይዝ ወዲያውም ኢሕአፓ መሬት ላራሹ እያለ እና አትነሳም ወይ እያለ ከደርግ ጋር ተፋልሞ የሞተው ሞቶ የተረፈው ከአገር መውጣቱም ቢሰማ፤ ኢሕአፓ ግን ስልጣን ሊይዝ አልመጣም፡፡ ስንሰማ ግን ኢሕአፓ ተከፍሎ ግማሹም ከወያኔ ጋር ወግኖ ኢሕአዲግ ተብሎ ገባ ሲባል እኔ ለእራሴ በፖለቲካው ብዙም ችሎታ የለለኝ የተቀበልኩት ነገር ነበር ፡፡ ቢሆንም ግን ኢሕአዴግ የሚባለው ስም ወይም ወያኔ የሚባለው ስም ጫካ ከገቡ በሁዋላ የተመሰረተ በመሆኑ እራሱ ፓርቲውን እንደመጣብን እንጂ እንደመጣልን ሆኖ በሕዝብ እይታ ለመቀበል አስቸጋሪ ሁኔታ ሳይገጥመው አይቀርም ብዬ እገምታለሁ፡፡ደግሞ ስንት አመት ሊቆይ ነው  ብሎ አሳሳቢ ነገር በህዝብ አይምሮ ቀርጦ የቤት ስራ ከመስጠቱ ውጪ እነሱ ሰራን የሚሉትን ለማየት ህዝብ ተቸግሮአል፡፡ ምክናያቱም የሰው ልጅ ትልቁ ፈተናው አስተሳሰቡም መገደቡ ነው፡፡ ብዙ ግዜ አምባገነኖች ህዝብን የሚጫኑት ግንዛቤውን የሚያዳክም ነገር በማድረግ ነው፡፡ መካድ የለለበት ግን ተቃዋሚ ይከልከል ወይም ነጻ አይውጣ እንጂ ህብረተሰቡ ጋር ለመገናኘት አይችሉም ለማለት ሁኔታውን ሁሉ እያየነው ነው፡፡ ይህ በአለም ዙሪያ  ያለ ልምድ ነው፡፡ በዚሁ ሁኔታ ተቃዋሚ ለታፈነው ህዝብ እንደፖለቲካ መሲሂ ሆኖ በናፍቆት እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡ ስለዚህ ተቃዋሚ ያሸነፈበትም መንገድ እንዳለ በገሀድ እያየን ነው፡፡ እንዳውም የተከለከለን ነገር የበለጠ ተፈላጊ የሚያደርግበትእና፤ ተቃዋሚ የሚለውን ስም ገናና እንዲሆን ያደርገዋል፡፡  እንግዲህ የአንድ ፓርቲ ዘመን ማለፉን ደሞ ለመረዳት ለኢሕአዴግ 23 ዓመት የበቃውም አልመሰለኝም፡፡ እየተፈሩእና እየተሸነገሉ በስልጣን ዘመንን መጨመር ምን ያህል ለአየዕምሮአቸው እንደሚመቻቸው አይገባኝም፡፡
አሁን ጉዳዩ ማን ይበልጣል የሚለው ጥያቄ ያለውን ገዢ ፓርቲ አደጋ እንዲያኝዣብብበት ሊያደርገው የሚችለው፤ አንድም ተመቸኝ የሚል በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አለመኖሩ ነው፡፡ በሩ እንደተከረቸመባቸው ዘወትር እንሰማለን፡፡ ይህ ያልገባው ኢሕአዴግ ሕዝብን አምኖ መኖር ሳይሆን መከላከያውን አምኖ መኖር ለጊዜው የጠቀመው ይመስላል፡፡ ደግሞ ደጋግሜ የምናገረው ተቃዋሚ የማይፈቀድበት አገር፤ በገሃድ አምባገነንነትን ማወጅ እና እወቁኝ እኔ ጀግና ነኝ ብሎ ጣት የመቀሰር ያሕል ይሆኖአል፡፡ ምንአልባት ያለው ገዢ ፓርቲ፤ እውነትም ከመቆርቆር እኔ ነኝ የምሻለው ፤ ተቃዋሚ አይጠቅማችሁም ብሎ አስቦ ይሆናል፡፡ ያልተመቸው ህዝብ ግን ልምዱን እራሱ በእራሱ ማየት ይፈልጋል እንጂ፤  እይታው ታማኒነት ሊያሰጠው አይችልም፡፡  ፈሪ የማድረግ ነገርን ማድረግ ማወጅ የሚረዳው፤ ለጊዜው ማዘግየት አልያም ህዝብን በደፈናው በጭፍን እንዲጉዋዝ ሊያደርገው ይችላል እንጂ በእሱ ላይ ያለውን አመለካካት ሊለውጥ አይችልም፡፡ ለሕዝብ ምን ያህል የአስተሳሰብ ችሎታ እንዳለው እንዲረዳእና እራሱን እንዲገመግም እድል  ያልሰጠው ኢሕአዴግ፤ የእኔ አይምሮ ብቻ ነውእና የሚሰራው እኔ ላስብልህ ያለ ይመስላል፡፡ ይህ ፓርቲነት ሳይሆን ሕዝብ ስለማይችል እኔ ሞግዚት ልሁንለት የማለት ያህል ነው፡፡ የተቃዋሚን አለመርባትህዝብ እራሱ አይቶ ሊገመግም የሚችል ብቃት ይኖረዋል እና፡፡ ካልሆነም  አይ ኢሕአዴግ ይሻለኝ ነበር ሊልም ችል ይሆናል ብሎ ትንሽ እረገብ ማለት በተሸለ ነበር፡፡ የግሌ አስተሳሰብ፤  የተቃዋሚ ጋጋታ ለውጥ ያመጣል ብዬ ባላምንም ያለው ገዢ ፓርቲ ህዝብን ከእራሱ ጭምር አብሮ ገደል ለመክተት ጎዳና እንደጀመረ ሊረዳው አልቻለም፡፡ ወይም እያወቀ የፈለገ ይምጣ ያለ ይመስላል፡፡ እኔ ለእራሴ ይህ ጨዋታ አድካሚ ከመሆኑም በላይ ህብረተሰብን ሞኝ ያደረገ በመሆኑ እጅግ በጣም አዝናለሁ፡፡ ለኢሕአዴግ ቀላሉ መንገድ ተቃዋሚን ሁሉ መፍቀድ እና ህዝብ ጋር በግልጥ እንዲተዋወቁ ማድረግ ነበር፡፡ ይህ ግን አስፈርቶታል፡፡ ከገባም ጀምሮ ሁሉም ነገር የሚሽከረከረው በዚህ ተቃዋሚ በሚለው ቴማ ላይ በመሆኑ እኛም የተረጋጋ ህይወት መኖር አልቻልንም፡፡ ብዙዎች አስተሳሰባቸውን የሚገልጹት እንደእኔ፤ ፖለቲካው ላይ ተጽእኖ ለማድረግ ሀይል ወይም እውቀት ኖሮ ሳይሆን የአገሪቱ ሁኔታ አሳዣኝ ደረጃ ላይ በመገኘቱ እና እኛም ሰላምን በመመኘት ነው፡፡ እኔም ከእንግዲሕ ብዙም አስተያየቴን ከመሰንዘር እቆጠባለሁ፡፡ ምክናያቱም እዲንጋ ላይ ውሃ ማፍሰስ ስለሆነ ነው፡፡ ትክክልም ባይሆን አስተሳሰብን መስጠት ሊከበር ሲገባው ግን ኑሮአችን ምስቅልቅል እንዲል ይደረጋል፡፡ ከእንግዲህ እያንዳንዱ ስለእራሱ አስተሳሰብ ቢቆም መልካም ነው፡፡ እኔ አጼ ቴዎድሮስን ወይም በላይ ዘለቀን አልያም ደግሞ መለስ ዜናዊን ልሆን አልችልም፡፡ ይህን ስል ሁሉንም ማመሳሰሌ ሳይሆን ሁሉም ላመኑበት ነገር እስከሞት ተጉዘዋል እና፡፡ ይህ ሁኔታ ዛሬም ሰው ያንን የአንድ ሰው ጀብደኛነት እየጠበቀ መሄድ የማያዋጣ ነገር ነው፡፡ ሲበላሽ በአንድ ሰው መውቀስ፤ ደግሞ እንደገና ለለውጥ ድፍረትም አንድ ሰውን መጠበቅም ዘመኑ ለፈባቸው መሆኑን ተገንዝብን እያንዳንዱ ለሰላም እጁን አጣምሮ መቀመጥ የለበትም፡፡ እናውቃለን አድፍጦ መቀመጥ እና፤ ሁላም የለውጥ አፍ ሲከፈት አበባ እንዳየች ንብ ዙሪያውን መክበብ፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ አስተሳሰቡን ለውጦ ትግልን መካፈል አለበት፡፡ ለማንኛውም ሰው ተማረም አልተማረም፤ ደሃ ሆነም ሀብታም ሆነ፤ ሀይማኖት ይኑረው አይኑረው የኢትዮጲያ ፖለቲካ ወደፊት ልጆቹ የሚያድጉበትን አገር የሲስተሙን ጉዳይ በጋራ አይቶ ለተሸለ ዲሞክራሲ ቢንቀሳቀሱ ጥሩ ነው፡፡ በሌላው መልኩ የመጨረሻ አስተያየቴን የምሰጥበት ምክናያት ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት ከአዲስ አበባ ተነስቶ የወጣ መሆኑን ማንም ስለሚያውቀው ምንአልባት ታግሎ ስልጣን ቢይዝ ለህዝቡ ባይተዋር የሚሆን ባለመሆኑ ከኢሕአዴግ አገባብ የተለዬ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ስለዚህ ኢሕአዲግ ግንቦት 7 ስልጣን እንዳይዝ ከፈለገ፤ የሚቀጥለው ምርጫ ላይ ተቃዋሚዎች በግልጥ እንዲወዳደሩ ማባረሩን ማሳደዱን እና ማሰሩን ቢተው መልካም ነው እላለሁ፡፡ ህዝብን በራሱ የሚያስተዳድረውን መወሰን ግድ ሊለው ይገባል፡፡ እሱ በጠነከረ ቁጥር ህዝብም ጥላቻ እየገነባ ይሄዳል፡፡ የኢትዮጲያ ህዝብ ሞኝ አይደለምእና፡፡ ያም ሆነ ይህ በግልጽ የታዘብኩትን ለመናገር የኢትዮጲያ ህዝብ የበለጠው ክፍል፤ ምንአልባትም 80% ወይም ከዚያ በላይ አሁን ያለውን ገዢ ፓርቲ አይመርጠውም ብዬ ገምቻለሁ፡፡ ይህ የሚሆነው ግን አንዱ በከፍተኛ ግንዛቤ ሌላው ደግሞ በግል በደል እና ዘረኝነትን በምጥላት ይሆናል፡፡ እንግዲሕ ይህን ጽሁፌን ያቀረብኩት ለማበላለጥ ሳይሆን የእኔ የሴቱዋ እይታ ነው፡፡ ለዚህ ውድቀት 23 ዓመት ሙሉ ኢሕአዴግ ዝም ብሎ ቤተመንግስትን ከመጠበቅ እና ልማትን ብቻ ማውራት፤ በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ ያለውን በደል፣ ህግ መጣመም እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያደረሰውን መከራ ዞሮ ለማየት ግዜ አልነበረውም ነበርእና፡፡ ተቃዋሚ ግን ከሕዝብ ከአስተሳሰቡ ጋር ለመገናኘት በቂ ግዜ ወስዶአል፡፡ ሁሉም አቤቱታቸው ወደተቃዋሚ ነበር እና፡፡ ኢሕአዴግስ፤ የለለውን አለ ብለን እንድንቀበል አስገድዶናል አልያም ዘግቶናል፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ግን ኢሕአዴግ ላይ ያለው ከፍተኛ ጥላቻ፤ ህዝብን „የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው“ እንዲል ያደረገው ክፉ ስራ ተቃዋሚዎችን እና ህዝብን እንዳይገናኙ ፕሮግራማቸውን እንዳይለዋወጡ  የማፈን ስራ ጥቁር ነጥብ ጥሎ ያልፋል፡፡ ይህ ግንዛቤን የማያስጨብጥ ጭፍን አካሄድ ወጣቱ እና ችግሩ እንዳይገኛኝ በማድረጉ፤ ኢሕአዴግ   ወደፊት በሚመጣው ችግር እንደመሰረጥ ጣይ ሆኖ በወጣቱ አይምሮ ያልፋል፡፡ እኛም ትናንት ወጣት ነበርን እና፡፡ ላገናዘበው፡፡ በቸር ባዩሽ

Dienstag, 24. Juni 2014



ይህን ያውቁ ኖሮአል?

ሁሉም የተደበቁ ግፎች አንድ ቀን ይወጣሉ፡፡ አለማችን በግፍ የተሞላች ነች፡፡ አንዳንዱም መዘዙ ቤተእምነቶች የሚያስተምሩት ወግ ስርአት ባህል ነው፡፡ እኔ በበኩሌ ደሃም ሁን ሀብታም፤ ጎባጣም ሁን ቀጥ ያልክ በትዳርም ውስጥ ተወለድ ያለትዳር፤ እግዚአብሄር ለአላማው ሰውን የፈጠረ ይመስለኛል፡፡ ነፍስ  በሰው እጅ ትጠፋለች እንጂ በሰውስ አትፈጠርም እና፡፡ ስለዚህ ሁሉም የሰው ልጅ የእግዚአብሄር መልክተኛ ሆኖ የተፈጠረ ይመስለኛል፡፡ ግን እዝች አለም ላይ አስቀድሞ ሰይጣን ስለተላከ ይመስላል ሰውን እንዲስት አድርጎታል፡፤ ከሁሉ በጣም አስቀያሚው ነገር በእግዚአብሄር ሰም የሚደረጉ ስህተቶች ናቸው፡፡ ሰሞኑን አንድ ዶኩሜንታር ፊልም አየሁ፤ እሱም በአንድ ቦታ ከስምንት መቶ ህጻናት በላይ አጥም መገኘቱ ነው፡፡ ይህ ደግሞ እየታወቀ የተፈጸመ ታሪክ ነው፡፡ ታሪኩም በኢንግላንድ አካባቢ ተፈጽሞአል፡፡ቤተክርስቲያንም ብታውቅም ሚስጥሩን ደብቃ ይዛለች፡፡ እንዲሕ ነው የሆነው፤ በዛን ዘመን ካለጋብቻ የተወለደ፤ ወይም አባቱን የማያውቅ ህጻን ዲቃላ ይባላል፡፡ ይህ ኅጻን የተረገመ፣ የተጠላ፣  እድለቢስ እና ያልተባረከ ነው ተብሎ ተደምድሞአል፡፡  ስለዚህ የወለደች እናት እስከቤተሰቡዋ ስለሚያገሉዋት ነውርም ስለሆነ ቶሎ የተወለደውን ልጅ ወደዛ መጣል ነው፡፡ የሚገርመው ቤተክርስቲያንም በወቅቱ በተለምዶ ዲቃላ የሚባለውን ልጅ እንዲያድግ ወይም ህብረተሰቡ እንዲቀበለው የምታደርገው ጥረት አልነበረም፡፡ አንዲት ወጣት ወዳም ይሁን በአስገድዶ መደፈር የመጣባትን እርግዝና፤ ከመርዝ የበለጠ መራራ ይሆንባታል፡፡ ልጅ አይባለም መርገምት ነውእና፡፡ ለአንዳንዶች መደሰቻ፤ ለአንዳንዶች መርገም የሆነው እርግዝና አሰቃቂ ምእራፉን ጥሎ አልፎአል፡፡ ለአንዳንዶች ደግሞ  አለማችን ብዙ ግፍ እና ሰቆቃ እምባ የፈሰሰባት፤  የምድር ሲኦል መሆኑዋን አንዘነጋም፡፡ ለነገሩ በሁሉም ሞት ባይኖር አለም ምን ትመስል ነበር? ብዬ ስጠይቅ መልሱ ልቤን ያፈካዋል፡፡ በሁሉም ቤት አንድ ቀን ዋይታ አለእና፡፡  „ ለሁሉም ግዜ አለው“ የሚለው የሰለሞን ትንቢት መሰል ጥቅስ በወቅቱ አይታወቅ ይሆን? በዚህ የተነሳ ነበር ዲቃላ ተብዬው ያልታደለ ኅጻን ወይም ለእኛ ሀጢያት መጨመሪያ የተወለደ ሕጻን ነፍስ አውጭኝ ወደ ካቶሎክ ቤተክርስቲያን ሲወረወር የነበረው፡፡  እዛም የሞቀ እና የደመቀ ነገር አልተቀበለውም፡፡ በወቅቱ ኢይሮፕ እራሱዋ ሁሉንም ህዝብ እኩል ያልያዘች ስለነበረች እነዚህ ህጻናቶች የሚፈለገው እንክብካቤ ያደረገላቸው የለም፡፡ የታደለ ትረፍ ያለው ነፍስ ለአዳብሽን/ጉድፈቻ/ ይሰጥ ነበር፡፡ እዛ የቀረው ግን የበለጠው ቁጥር ይሞታል፡፡ ብርድ ነው እራሃብ ነው፡፡ አርና ሽንቱን የማይቆጣጠር ልጅ ማንስ ተከታትሎ ያስበዋል፡፡ እዛም ከተወረወሩ በሁዋላ  ዞሮ የሚያያቸው ቤተሰብ መንግስትም የለም፡፡ እናትም ልቡዋ ቢፈልግ እድሉ የላትም፡፡ ልጅም እንደወለደች አይወራም ነውር ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡ ባልሰለጠነ ዘመን መኖር፡፡ ግፉ ከዛሬው ይብስ ነበርእና፡፡ ለመሆኑ እግዚአብሄር አይደለምእን ነፍስ ለመፍጠር እና ወደዚች ምድር ለመላክ ያሰበው? እንግዲህ ያ ያልሰለጠነው ዘመን፤ ይህን ይመስላል፤ የሴት መከራ ለልጅ ሲተርፍ፡፡ ዛሬ የተረፉት ወይም ለአዳብሽን የተሰጡት አርጅተው ዘራቸውን እየፈለጉ እንባ በእንባ እየታጠቡ በደኩሜንታሪው ፊልም ተመለከትኩ፡፡ እንኩዋን እነሱ መለየትን ተለማምደው የተሰቃዩት እና እኛም የምናየው አለቀስን፡፡ አለም ምን ትመሰል ነበር በዛ ባልሰለጠነ ዘመን?
ደግሞም ሌላ ሽው ያለ ኮሜንት በሌላ ዜና ሰማሁ፡፡ በነገስታቶች በባላባቶች ቤት አካሉ ጎሎ ወይም ታሞ የተወለደ ሕጻን ይገደል ነበር የሚል ጥርጣሬ የያዘ ነገር፡፡እሱም እባላባቶች ቤት ቆንጆብቻ ነው የሚወለደው የሚለውን ማንነት የተለዬ ለማድርግ ነበር፡፡ ዌል ነጻ ፕሬስ እየጎለጎለ አሰቃቂውን ዘመን ጠቆም ሳያደርግ አልፎ አያውቅም፡፡  ዛሬ ግን አለም ለየት ያለ መልክ ይዛለች፡፡ ባልሰለጠነው ዘመን ፤ ኢትዮጲያም ውስጥ ዲቃላ ነውር እንደነበር እኔም ሰምቻለሁ፡፡ „ ዋ ዲቃላ ታመጪብኝ እና“ ተብላ ያላደገች ሴት አትገኝም፡፡ማን ወልዶ ለዛውም፡፡ ከተወለደም፤ ጎረቤት ሳያየው እንዳያለቅስ አፉ እየታፈነ፤ ወይም ጌቶቹ/አባወራው/ እንዳያዩት እንዳይሰሙት እየተባለ ያደገም እንዳለ ይነገራል፡፡ አልያም ወደገጠር በስውር ለከብት እረኝነት የተሰጠ፡፡ እናንተ ግን ዘመን ነጻ አውጥቶአችሁዋል፡፡ ልብ በሉ ሰውን ሰው ነጻ አያወጣውም ዘመን እንጂ፡፡ የትናንትናውን በደል ላስብ ያለ የዛሬውን ሳይመለከት ድርብ እንዳይሆንበት፡፡ ዛሬ ዘመን ለጣለብህ ግፍ እና መከራ ድምጽህን አሰማ፡፡ በትናንትናው ዘመን የተደረገው በእራሱ በእምነት መሪዎች የተደገፈ እና የተደበቀ ሆኖ አልፎአል፡፡ ስለዚህ እንዳው ወደትናንት ገብቶ ሲቃ ከሚይዘን፤ የዛሬ ያቀረበልን የነገው እንዳይወቅሰን መዘጋጀት ነው፡፡ ከሳሹም ተከሳሹም አልፈዋል እና፡፡ ጥቂት ባላባቶች እንደሚመቻቸው ወግን ስርአትን አድርገው አሰቃቂ ሁኔታ በአለም ዙሪያ አልፎአል፡፡ ዛሬ ኢይሮፕ መልኩዋ ከተቀየረ ዘመን አለፈ፡፡ አንተስ ወዳጄ፤ ከትናንትናው ለመውጣት ዝግጁ ነህእን? ወይስ ትናንት እንዲህ ሆኖብኛል እያልክ አጽም መቀስቀስ፡፡ ልብ እንበል ወዳጆቼ፤ የባላባት ዘመን ለዛሬ አይሆንም፡፡ አጠፉም አለሙም አለም በአንድ ወቅት አንድ አይነት የዘመን ባህል ኣሳልፋለች፡፡ አለም አንድ መሬት ላይ የሰፈረች እኛን የተሸከመች እንሰሳ ነች፡፡ አሕያ ትጫናለች እንጂ የተጫነችውን ማወቅ ትችላለች እን?በቻለችስ፤ ምግቡዋን ተሸክማ በባዶ ሆዱዋ ባልተራመደች ነበር፡፡ በቸር
ባዩሽ


Donnerstag, 19. Juni 2014

የስም ድግስ በኢትዮጲያ



የስም ድግስ በኢትዮጲያ

የኢትዮጲያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተመካክረው በአንድ እስከአልመጡ ድረስ፤ ግልጽ የሆነ የሕዝብ ድጋፍ የሚያገኙ አይመስለኝም፡፡ ሁሉም ፓርቲዎች ተቀራርበው ወደአንድ ውህደት ለመምጣት ያልቻሉበት ምክናያት የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን በጥላቻ የመተያየታቸው ጉዳይ ዛሬ ዛሬ እየመሰለኝ ሄደዋል፡፡ የፖለቲካ ጉዳይ ቢሆን መፍተሄ መቼም ባላጡ ነበር፡፡ እንደተማረ የፖለቲከ ሰው ከሆኑ ማለቴ ነው፡፡ እንግዲሕ እራሴን ግልጽ ላድርገውእና፤ ኢሕአዴግን ባለው ቀውስ ብቻውን ተጠያቄ ማድረግ ለእኔ እየከበደኝ መጥቶአል፡፡ ምክናያቱም ሕዝብ ተቃዋሚ ፓርቲ አለ የሚለውን ተስፋ እስከአላነሳ ድረስ መንከራተቱ እና መሰደዱ፤ መታሰሩእና መሞቱ ይቀሬ ነው፡፡ ህዝብ ተቃዋሚ የለም ካለ ግን አንገቱን ደፍቶ ለአንድ ኢህአዴግ ያድራል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አላችሁ ወይም የላችሁም ተቃዋሚዎች? እናንተ ችግራችሁን ፈትታችሁ ካልቀረባችሁ፤ እንዴትስ የኢትዮጲያን ህዝብ አንድ አድርጋችሁ ልታስተዳድሩት ትችላላችሁ? ስለዚህ እኔ በእናንተ በኩል ያለኝ ተስፋ እየመነመነብኝ ሄድዋል፡፡ ወይስ የእናንተ አንድ አለመሆን ምልክት የኢትዮጲያ መበታተን ይሆን? እኔ የፖለቲካ ሰው አይደለሁም ግን ይሁንና እያንዳንዱ የኢትዮጲያ ህዝብ በኢትዮጲያ ሰላም የሚያገባው ይመስለኛል፡፡ ኑሮው ከመክበዱ በላይ ብዙ ነገሮች በውስጣችን ብዙዎቻችንን እንዲደነጋገረን የማድረግ ተጽእኖ እየፈጠረ ያለው ሁሉም ነው፡፡ አንድነት እያሉ የሚለፈልፉ ፓርቲዎች አንድ ሆነው አናያቸውም፡፡ ለነገሩእማ የኢትዮጲያ ህዝብ በትእግስት አብሮ እየኖረ ይገኛል፡፡ ያልተስማማ ፓርቲ የሚያፈራው ያማይስማማ አባል ነው? ሁሉም የአባል ባለቤት ለመሆን ነውእን አባል የምትፈልጉት ወይስ አገሪቱን በትክክለኛው መንገድ ለመምራት? ስለዚህ ለውጥ ከእናንተ ካልመጣ እንወክለዋለን የምትሉት ህዝብ አምኖ ሊያዳምጣችሁ አይችልም፡፡ የእናንተ ጉዳይ እስረኛውን ካለማብዛት በስተቀር የተሸለ ነገር ያመጣል ብዬ መገመት አልችልም፡፡ ስለዚህ ባህላችሁን ቀይሩ፡፡
እግረ መንገዴን አንድ ልበላችሁ፡፡ ባለፈው የሆላንዱዋ ንግስት ለልጅዋ ንግስናዋን አወረሰች፡፡ ነገ ደግሞ የስፓንያው ንጉስ ካርሎስ ንግስናውን ለልጁ ያወርሳል፡፡ እኛ ለዚህ ያልታደልነው፤ ልቤ በቅናት ይቃጠላል፡፤ በቀሚስ ወይም በባል አልቀናም፡፡ የምቀናው በአገር መሪዎች ነው፡፡ ባልም ቀሚስም በአገር ሰላም ያምራል እና፡፡ ትናንት ሀይለስላሴ ያደረጉት ስህተት ዘላለም ሊይዙት የማይችሉትን እይዛለሁ ብለው፤ ለውጥን በሰላም ሳያሳዩን አለፉ፡፡ እኛም ተረግመን ነው መሰል ይህ እጣ ፋንታ ዛሬም ተከትሎን፤ ስልጣንን በሰላም መልቀቅ ልንላመደው አልቻልንም፡፡ እንደአሜሪካ አውሎ ንፋስ ስም ብቻ እያወጣን እና እየቀያየርን እዛው የፖለቲካ ባህሉን እያገላበጥነው እንገኛለን፡፡ እስኪ አንድ ተከፍሎ ስም የወጣለትን ስለ ዲያስፖራ ትንሽ ላነሳሳው፡፡

ዲያስፖራ

ዲያስፖራ፤ ኢሕአዴግ አገራችሁ ግቡ ካለ በሁዋላ ግን ዲያስፖራ ብሎ በከፈለ ስሜት ስም ሰጥቶ ተወልዶ ካደገበት አገር ከዘሩእና ከወገኑ ተለይቶ እንዲታይ ሆን ብሎ ያወጣለት ስም ባያተዋር እንዲሆን ሆን ብሎ ያደረገው ይመስላል፡፡ ስደት ሁሉም ተሰዶአል፡፡ ሁሉም ከአገር ወጥቶአል፡፡ ወያኔ ኢሕአዴግ እራሱ ኢትዮጲያ ወጣ ገባ እያለ የነበረ እና በጫካ የኖረ ነው፡፡ ተሰዳጁን ዲያስፖራ እንዳለው ሁሉ እራሱን ደግሞ የጫካው ብሎ ወይም ሌላ ስም መስጠጥ ነበረበት፡፡ እራሱን ባላባት አድርጎ እግሩን አስራርቶ፤ ዲያስፖራ የተባለውን ክፍል አየር ላይ አንሳፎ የቀረው ወያኔ ኢሕአዴግ፤ ግራ የሚያጋባ ፓርቲ እንደሆነ አንድእና ሁለት አይባልም፡፡ ይሁንና ግን ተቃዋሚም ቢሆን ለዲያስፖራ ለሚባለው ክፍል ቀሎ አልታዬም፡፡ ምክናያቱም ዲያስፖራው አገሩ ጉዋጉቶ ቢገባ እንደወያኔ ቀኝ እጅ ተደርጎ በብዙ መልኩ ኢታማኒ እንዲሆን መደረጉ ነው፡፡ ገረፍ አድርጌው ልለፍ እና፡፡ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ ሆኖ ዲያስፖራ ለተቃዋሚ ወያኔ ነው፤ ለኢሕአዲግ ደግሞ ተቃዋሚ ነው፡፡ የህ አለመታደል የሆነ ውንጀላ፤ ሁሉም አንድ የሆኑብኝ ምክናያት አለእና፡፡ ያልተለወጠ ነገር፡፡ ኢሕአዴግ አገሩን እንደልቡ በእጁ ይዞ ችግር እንኩዋን ቢደርስብህ ለመርዳት አቅም የለለው ስራ አስፈጻሚ ይዞ በህግ ይጫወታል፡፡ የሚጠብቀው ቤተመንግስቱን እንጂ ሕዝቡን ለመጠበቅ አቅምም የለውም፡፡ ለመሆኑ በፈለገውም ሁኔታ ቢሆን አገሩ የሚገባ በሁሉም መወንጀል አለበትእን?
አሳፋሪ ምግባሮች የሚታዩበት አገራችን፤ ሁሉም መተማመን የለለበት መንታ መንገድ ላይ ገብቶ ቆሞአል፡፡ ለመሆኑ ዛሬስ ከአገር የሚወጣው ሁሉም እውነት የፖለቲካ ችግር ኖሮበት ነውእን? እውነት ተርቦ ነውእን? አይደለም በነገው የማይተማመነውም ሀብታምም ልጁን ያሸሻል፡፡ ሁሉም ግን አንድ ቀን ዲያስፖራ ተብሎ ወያኔ በሰየመለት ስም ይገባል፤ ከዛም በባይተዋርነቱን ይኖራል፡፡ በተቃዋሚም ሆነ በገዢው ፓርቲ ዲያስፖራ እየተባለ የሚነገርለት ይህ ህዝብ ግን፤ ችግር የገጠመው የዲሞክራሲን አካሄዱን ስለሚያውቅ ብቻ ነው፡፡ ከዛም ወያኔ ኢሕአዴግ አያዳምጠውም ኢዲሞክራሲ የሆነ ምግባር አለውእና፤ ተቃዋሚም ያኮረፈው የማያምነው ሆኖአል፡፡ ሁሉንም ወያኔ፤ ሁሉንም ተቃዋሚ ብሎ በጥርጣሬ ማየት አገር መግባት ያመጣው ቀውስ ነው፡፡ አዎ ሁሉም አገሩን ይፈልጋል፡፡ ነውረነትም አይታየኝም፡፡ ይህን ክፍፍል ለምዶባችሁ እንዳይቀር እና የእቃ እቃ ጨዋታ እንዳይሆናባችሁ ወደመልካም ስራ ሁሉም ቢያስብ መልካም ነው፡፡ ካልሆነ ግን ህዝቡን እንዳው ድንግርግሩን ሁሉም ባያወጣው ምልካም ነው፡፡ ችግር አለ ግን ችግሩን የሚፈታውን መንገድ ሳትጨብጡ ሁሉም ህዝብን መወከል አይችልም፡፡ የኢትዮጲያ ህዝብ አማራ ነው፣ ትግሬ ነው፣ ኦሮሞ ነው፣ ጉራጌ ነው፣ ዲያስፖራ ነው………. ይህ ክፍፍል ለማስተዳደር ይቀል ይሆንን? ወይስ ዘላለም የማይቆየውን ስልጣን ለማራዘም? „ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልምሆነእና፤ እራሱን ያላመነ ሌላውን ማመን ይሳነዋል፡፡ የኢትዮጲያ ህዝብ ድምጹን የሚያሰማብት ገዢም ፓርቲም ሆነ ተቃዋሚም የለውም፡፡ ምክናያቱም የፖለቲካ አካሄዳችሁ በጥላቻ የተሞላ እና በድብቅ ሚስጥር የተሞላ በመሆኑ፡፡ እስከዛው የኢትዮጲያን ህዝብ እግዚአብሄር ይሁነው፡፡