ፌድራል ፖሊስ እና ውለታው
አንድ ነገር ልናገር ፍቀዱልኝ፡፡ ቢከፋችሁ እንኩዋን እኔ እናንተን ለማስከፋት
በማለም ወይም ፕሮግራም በማድረግ አይደለም ያቀረብኩት፡፡ ስለዚህ ባይመቻችሁም አስቀድሜ ይቅርታ ጠይቄበታለሁ፡፤ ይሁንእና ግን ይህንን
መናገሬን ግን አምኘበት ነው የምናገረው፡፡አመለካከቴን ሳይሆን ትዝብቴን ነው፡፡ ችግሮች አሉ የምለው ችግርን ከመልካም ለይቼ ስላወኩ
ነው፡፡ ብዙ ሰው እኔ ችግር የምለው ችግር መስሎ አይታየውም፡፡ ምክናያቱም ችግር ሲበዛ በቃ ባህል እየሆነ እየተዋሃደ እንደሚሄድ
ነው፡፡ ቸድግርን እንደባህል እና እንደጤነኛ የቀን ሕይወት አድርገው የተዋሃዱ አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ምንአልባት መልካም ነገር ቢሆን
ሊደነግጡ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ቢሮ ስትሄድ ወዲያው ፈጽመው ቢሰዱሕ እርግጠኛ ነሕ ያ መጉላላትን የለመደው ሰው ሊያብድ ይችላል ብዬ
እገምታለሁ፡፡
እኔ ፌድራል ፖሊስ ከከተማው ፖሊስ ይሻለኛል፡፡ እነሱ ሴት ስትበደል ሲያዩ
በፍጥነት ካለምንም ማዘዣ ጣልቃ ሲገቡ ብዙ ግዜ አያለሁ፡፡ እራሴም የተለማመድኩት ነው፡፡ ገጠመኘሸን ላጫውታችሁ፡፡ አንድ ወቅት
ላይ ለአንድ ቤተሰብ ካለኪራይ የሚገለገሉበትን እቃ አዋስኩዋቸው፡፡ ይህንን ሳደርግ እጅግ በጣም ደስተኛ ነበሩ፡፡ እንዳውም እኔን
እንደመልአክ ለማድረግ የዳዱበትን ሁኔታም አልረሳውም፡፡ አንዱ ለአንዱ ማድረግ በጀርምን ከነጮች ጉዋደኞቼ ጋር የለመድኩት በመሆኑ
ለእኔ ምንም መስሎ አልታየኝም፡፡ በቃ መረዳዳት ያለ ነገር ነው፡፡ በአካባቢው ያልተለመደን ነገር እኔ ማድረጌ አስደንግጦዋቸዋል፡፡ እንዳው በትንሹ በወር አንድ ሺህ የኢትዮጲያ
ብር ባከራይ የማላጣበትን ይቅርብኝ ብዬ ካለክፍያ አዋስኩዋቸው፡፡ ይሁን እና ግን ይህንን ሳደርግ ምንም አይነት ከእግዚአብሄር ጋር
ወይም ከጽድቅ ጋር እራሴን በማስቀመጥ አይደለም፡፡ እኔም እራሴ የሰውን ፍቅር ስለፈለኩ፤ ሰዎችም ጋር የመተዋወቂያም አንደኛውን
መንገድ ይህን አይነት ማህበራዊ አካሂያድ ለመሄድ ወስኘ ነበር፡፡
ነገሩን የሰጠሁዋቸው ለአንድ አመት እንዲገለገሉበት ነበር፡፡ ልብ ብትሉ በብሄር ክፍፍልም ስለማላምን እነዚህ ሰዎች ጋር
የኢትዮጲያዊነት እንጂ የብሄር ግንኙነትም አለንበረንም፡፡ አማረኛ ይናገሩ እንጂ ግን ዋናው የሚጠቀሙበት ቁዋንቁዋ አማረኛ አይደለም፡፡
ይህን
አንድ ቤተሰብ የአራት ሰው የቤተሰብ ስብስብ፤ በልቤ ውስጥ በፍቅር ወድጃቸዋለሁ፡፡ የሰጠሁዋቸውም የትውስት እቃ እንደሚያስፈልጋቸው
አምኘበታለሁ፡፡ ደስታቸው ደስታዬ ለማድረግ የወሰንኩ ስለሆነ ምንም ቅሬታም አልነበረኝም፡፡ እኔ ግን ውጭ አገር ኑዋሪ በመሆኔ ያ
አንድ አመት አልፎ ሁለት አመት ያለፈ እቃውን እንዲጠቀሙበት ወሰንኩ፡፡ በሶስተኛውም አመት እንደዛው ነበር፡፡ በአራተኛው አመት
ግን እኔ አገሬ ተመለስኩ፤ እና እቃውን እንዲመልሱልኝ በአክብሮት ጠየኩ፡፡ የቀረበልኝ ግን መስፈራራት እና ዛቻ ነበር፡፡ እኔም
እንዲህ በቀላሉ የምመለስ አልነበርኩም፡፡ በትእግስት ግን ጠየኩ፡፡ ነገሩም ዝም ብሎ የሚተው አይነት እቃ አልነበረም፡፡ ብዙ ግዜ
የሰዎች ክህደት እያጋጠመኝ ብዙ ልምድ በማካበቴ፤ በሰዎቹ ክህደት እጅግም አልጠደነቁ፤ አልደነገጥኩምም፡፡ ኢትዮጲያ መመላለሴ እና
ሁኔታዎችን ማየቴ ብዙ የህይወት ልምድ አካብቻለሁ፡፤ ምንአልባትም የተጎዳው ልቤ ስለደነዘዘ ይሆናል የማይሰማው፡፡ በነገሩ ከመናደድ
የተለያየውን ዘዴ ተጠቅሜ የሚተርፈውን ማትረፍ መቻል እንጂ እሩጫዬ እንዲሕ አደረጉኝ እያልኩ ማልቀስ፤ እና መቆጨት ፍላጎቱ የለኝም፡፡
ይህን ባደርግ የምጎዳው እራሴ ነኝ፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ሰውን መጎዳት አንደዬ አብሮዋቸው የተዋሃደ ባህል ሆኖአል፡፡ ስለዚህ ያለቀስኩትን
ባለቅስ፤ የወቀስኩትን ብወቀውስ እንዚህን ሰዎች ወደንስሃ ላመጣቸው አልችልም፡፡ በቃ ለእኑ የሚያደርጉት ድርጊት በጉልበት እና በቀማኛነት
መኖር ጤነኛ አመለካከት ሆኖአል፡፡ እንደእውነቱ ብዙም ሰው አልደነገጠም፡፡ እየተጎዳዱ መኖር የየቀኑ የእራሳን ማዳን ዘዴ የሆነ
ይመስላል፡፡ በቃ አንዱ ብልጥ ሌላው ሞኛ ሞኝ ሆኖ ከመታየት ውጭ፤ የስሜትን መጎዳት የመረዳት አቅም የሚታወቅም አልመስልሽ አለኝ፡፡
ፈረንጅ አገር ቢሆን ትወቃቀሳለህ፤ እዚህ ግን መውቀስም፤ ማልቀስም ማዘንም መደሰትም የለም፡፡ በቃ የቻለ ይኑር እራሱን ብቻ ያትርፍ
ይመስላል፡፡
ፖሊስ ጣቢያም ሄድኩ፡፡ አንድ ፖሊስ አዛዥ ግን አንድ ትምህርት ሰጠኝ፡፡
ይህም፤ እኔ አዝኘ ያደረኩት ነገር ትክክል እንዳልሆነ እና እኛ ከውጭ
የምንመጣ ኢትዮጲውያኖች ሞኛ ሞኝ እንደሆን አይነት ነገር ነበር የተናገረኝ፡፡ „ሰዎቹን በገዛ እጅሽ ነው እራስ ላይ ያወጣሻቸው“
በማለት ጮሀብኝ፡፡ ምንአልባት ለአካባቢው እንደሆነ እንጂ፤ እኔ ጤነኛ የሰውልጅ ሊያደርግ የሚችለውን በአቅሜ ካለኝ ነገር ለማካፈል
ሞክሬአለሁ፡፡ „እንዳውም በነጻ የምታደርጉት ነገር፤ ምንም አይነት ትምህርትነት የለውም“ በማለት ፖሊስ አዛዡ፤ አንድ ለአስተሳሰቤ ቀለብ የሚሆን እውነታን አስጨበጠኝ፡፡“አዎ
እናንተ ኢሕአዴግን ያስጠላችሁ እየመሰላችሁ፤ ብራችሁን ታዝረከርካላችሁ፤ ሰዎችን ሕገወጥ እንዲሆኑ ታደርጋላችሁ“፤ እንዴት ማበድ
ነው ታዲያ ይህንን እቃ ከሶስት አመት በላይ በነጻ የሰጠሸው? ይህን ማንም የሚያደርገው የለም እኮ በማለት ተቆጣ፡፡ ሰውየውንም „ግባ“ በማለት ጮሀበት፡፡“ ለመሆኑ ይህቺ ሴትዮ ያደረገችውን መልካም
ነገር እኛ እንኩዋን እናውቃለን፡፡ እና እንደሰጠችህ አመሰግናለሁ ብለሕ ዘመድ አድርገሕ ትለያለሕ እንጂ፤ እንዴት እንዲህ ታንገላታታለሕ?
„ በማለት እራሱን በመነቅነቅ ተናገረው፡፡ „ንብረቱ የአንተ ነው
የእሱዋ? በማለት ጠየቀው፡፡ ንብረቱ የእኔ መሆኑን ከሰውየው ካዳመጠ በሁዋላ፤ ታዲያ መልስላታ በማለት ከሰውየው ምላሽ ጠበቀ፡፡
እቃውም በዚህ መልኩ ተመለሰልኝ፡፡
ከፖሊስ ጣቢያውም እንደወጣን፡፡ ፊኒፊኔ የእኛ ናት እኮ እናንተ አማሮች
አትኖሩዋት በማለት ትንሽ ጉራከረዩ አለብኝ፡፡ ሰምቸው ያማላቅ የዘር የቦታ ክፍፍል፤ ከእነዚህ ከምወዳቸው ሰዎች ስሰማ፤ ልቤ አለቀሰብኝ፡፡
የስድስት አመቱ የሰዎቹ ልጅ፤ እየሮጠ መጣ እና ጥምጥም አለብኝ፡፡ ይወደኛል፡፡ ክፉኛ ጥሎበት ይወደኛል፡፡ በዚህን ግዜ ደግሜ ይህንን
ልጅ ስለማላየው ልቤ እንደበረዶ ሲቀልጥ ተሰማኝ፡፡ ሆዴ ሁሉ ተንቦጨቦጨብኝ፡፡ እልቤ ውስጥ ያስገባሁት የምወደው ሕጻን ነበርእና፡፡
እንደስጋ ዘመዱ አድርጎኝ ባየኝ ቁጥር የሚፈነድቀው ልጅ፤ „ማሚ ባዩሽ አለቀሰች እኮ ብሎ ወዲያ ወዲህ መልስ ለማግኘት ፈለገ፡፡
ደነገጠ፡፡ እንባዬንም በጣቶቹ ጠረጋቸው፡፡ አባቱም ግባ ብሎ ተቆጣው፡፡ ይህንንም መምጣቱን ስለማውቅ ነበር አስቀድሜ እንባ የተናነቀኝ፡፡
ሁሉም ነገር ፖሊሱ እንዳለኝ ሆነ፡፡ ኪራይስ ትንሽ አነስ አድርጌ ብቀበል
እንዴት በተሸለ ነበር፡፡ ፈረንጅ ለሌላ ሲያደርግ አይቻለሁ፡፡ ለእኔም
ያደረጉልኝ መልካሞች ነበሩ፡፡ ስለዚህ የእኔም ትምህርት ከዛው የመጣ እንጂ ከሰማይ ዱብእዳ አልነበረም፡፡ ማን ያውቃል፤ ያነዬ የተደረገልኝ
እኔም በተራዬ እንዳደርግ እንደሆነ? አምነህ ያደረከው ነገር አይቆጭሕም፡፡
እንዲህ ሆነ፡፡ እቃዬን የተረካከብኩት ያለፈው ምርጫ ቀን ነበር፡፡ ከተማው
ጸጥ ብሎአል፡፡ ፖሊስ ጣቢያው በፌደራል ፖሊስ ሙሉ ነው፡፡ እንደምንም ብዬ ያደረኩት ጥረት እቃዬን ተረክቤ፤ ከሰዎች ጋር ተረካክቤ
ተለያየሁ፡፡ የምርጫው ቀን አልቆ ማታ ላይ ግን ያላሰብኩት ነገር ተከሰተ፡፡ ያ ያገለገልኩት ሰው ከእሱ ጋር 17 ጎረምሶች ሆኖ
ለሊት የምኖርበትን ግቢውን በመክፈት ደፍሮ ገባ፡፡ ይዠውም የነበረው
ዘበኛ ትቶኝ እነሱ ግቡ ሲገባ እሱ ሸሽቶ ጥለኝ ወትቶ ሄደ፡፡ የሚጠበቅም እቃ ንብረት የለኝ፡፡ በቃ ብቻዬን ስለምፈራ ብቻ ነው
ይህንን ዘበኛ በዛው ቀን የያዝኩት፡፡ ያመጣልኝ የሰፈር ደላላ ነው፡፡ እኔ በዘመኔ በዘበኛ የማስጠብቀው ንብረት አልያም በካዝና
የምቆልፈው ብርና ወርቅ የለኝም፡፡ በቃ አልወድም፡፤ ወርቅም አንድ ግራምም የሚባል ኖሮኝ አያውቅም፡፡ አልፈልገውም፡፡ ስለዚህ ሰውዬው
ለእኔ የነፍስ ፎርሙላ አይነት የኢትዮጲያ ባህል ፕሮቶኮል ብቻ ነበር፡፡ አቶ ዘበኛ ግን አሳልፎ ሰጦኝ ከፊቴ ድምጥማጡ ጠፍቶአል፡፡
ሰዎቹ የተሳሳቱት
አንድ ነገር ገጠመኝ፡፡ ይህቺ የፈረንጅ አገር ተመላሽ ኡኡታ አትችልም ብለው ገምተው ነበር ይመስለኛል፡፡ ምክናያቱም አፌን ለመጠበቅ
አልተዘጋጁም ነበር እና፡፡ እኔም ኡኡታዬን አቀለጥኩት፡፡ እሪታም እንደወሎ አነጋገር፡፡ በዘመኔ ከዛ በፊትም በሁዋላም እንደዛ ጮሄ
አላውቅም፡፡ ድምጼ ከመውጣቱ ግን ፌድራል ፖሊስ እንዳለ ግቢውን እየጣሱ ገብተው አጥለቀለቁት፡፡ ገብተውም እጮሕ ነበር፡፡ እንዲሕ
አይነት ደግሞ የባሰ ጉድ ገጥሞኝ አያውቁም፡፡ ለአንዲት ሴት 17 ጎረምሶች አስደነገጠኝ፡፡ ጀግና እምስል እንደሁ አላውቅም፡፡ እንጂ
አንዱም እኔን ለማንበርከክ በቂ ነበር፡፡ ደግሞም ገጠሬዎች ናቸው ብዙዎቹ፡፡ ተነድተው እንደመጡ ያስታውቃል፡፡ በዝምድና ወይም በዘር
ስም፡፡ የእኔ ጩሀት እና የፊድራሉ ጋጋታ ግራ አጋብቶዋቸው ደንግጠዋል፡፡ ሊያስፈራሩኝ ይሁን አልያም በውነት አደጋ ሊያደርሱብኝ
አላውቅም፡፤ ይህ ሁሉ ነገር የደረሰብኝ ግን በመስተጤ እንጂ በመንፈጌ አልነበረም፡፡
ፌድራል ፖሊሶቹ ወጣቶች ናቸው፡፡ ደስ የሚሉ ቀልጣፎች ናቸው፡፡ ከሁሉም ዘር
የተካተቱበት ግሩፕ መሆኑን ተመለከትኩ፡፡ አንድ ግን በልዩነት የማያዩት ነገር ተፈጽሞአል፡፡ እሱም የአንዲት ሴት ጩሀት ነበር፡፡
እንደእውነቱ ይህንን ከመካከላቸው በችልተኝነት ያየው የለም፡፡ ብቻ ሁሉም እነዛ ሰዎች ላይ አፍጠዋል፡፡ ሕገወጥነታቸውን እና ወንጀላቸውን
ሴት በማስደንገጥ ያዋክቡዋቸው ይዘዋል፡፡ ትግረኛም አማረኛም ኦሮሞኛም
ያወራሉ፡፡ ማንም አድሎ ሊያደርግላቸው የፈለገ አልነበረም፡፡ ግቢውን
ሞሉት፡፡ እነሱ ብቻ አልነበሩም፤ ጩሀቴ የአካባቢውንም ተመልካች ሰብስቦአል፡፡ ወዲያውም 17ቱንም ለቃቅመው እጅ ከፍንጅ እያዋከቡ
የዘው ፖሊስ ጣቢያ አጎሩዋቸው፡፡ ለሊቱን ግን ታስሮ ያደረው፤ ያ
የረዳሁት ሰው ነበር፡፡ ደሴ ፖሊስ ደርሶልኝ ስለማያውቅ፤ የአዲስ
አበባው አጋጣሚ የደመነፍሴን ጮሁክ እንጂ ፖሊስ ይደርስልኛል ብዬ አስቤም አልነበረም፡፡ እዛ ማንም አይደርስልኝም፡፡ በውነት ክፉ
ልምድ ነው እዛ ያካበትኩት፡፡ በዚህ ምሽት ግን እጅግ ደስተኛ ነበርኩ፡፡ በቃ በአገሬ ኩራት እንዲሰማኝ እራሴን ማበረታታት ጀመርኩ፡፡
ይሁን እና ግን እነዚያ የምኖርበትን ግቢ ሰአት ካለፈ ገብተው አደጋ ሊያደርሱብኝ ይችሉ የነበሩት ሰዎች መደበኛ ፖሊስ ምርመራም
ሳያካሂድ እና ጉዳዩንም ወደፍርድ ቤት ሳይመራልኝ እምቢ ብሎ ለቀቃቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ፊድራሎቹ ተናደው እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡
የሚገርመኝ ነገር ቢኖር መርማሪው ፖሊስ ከሰዎቹ ጋር እርቅ እንድፈጥር
በተደጋጋሚ ግፊት ያደርግብኝ ነበር፤ እንኩዋን ወደህግ እንዳቀርባቸው ሊያበረታታኝ ቀርቶ፡፡ ፖሊስ ሕግ አስፈራሽ ወይስ ሕግ አስፈጻሚ
በማለት እኔም እደነቅ ነበር፡፡ ወዲያውም ግን ፊድራሎቹ የመጡበትን ጉዳይ ለካስ ጨርሰው ፖሊስ ጣቢያውን ለቀው ሄደዋል፡፡ እኔም
መደበኛ ፖሊስ በተደጋጋሚ መጥተሸ ያንን ፋይል አትዘጊም እየተባልኩ እቸገር ነበር፡፡ ለነገሩ እኔ ፍርድቤት መሄድ እንጂ መዝጋት
አልፈለኩም ነበር፡፡ ግን ለፖሊስ ማህበራዊ ሕይወት ወሳኝ መሰለኝ ከህግ የበላይነት በላይ፡፡ ተተረፈች ተነገደች እያሉክ ልሰናበት፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen