Sonntag, 2. März 2014

ባንዲራ የአገር ወይስ የፖለቲከኞች ምልከት



 ባንዲራ የአገር ወይስ የፖለቲከኞች ምልከት
ፌስቡክ መጠቀም የፈለኩት አገሬን ወደአለሁበት አገር ለማቅረብ ብዬ ነው፡፡ ያቀረብከውን ነገር ደግሞ በደንብ እንድታውቀው ይጠቅመሀል፡፡ እናንተ ጋር ሸር በማደርገው የአገር ጉዳይ ሁሉ የማላውቀውን እንዳውቅ ያደረጉኝ ነገሮች ጥቂት ናቸው ሊባል አይችልም፡፡ ብዙ ለማወቅ ደግሞ አስቸጋሪ የሆኑ እውነታዎችን እየተረዳሁ መጠቻለሁ፡፡ አንዳንደዬ አንዳንድ የሚዲያ መስኮቶች ጥላቻቸው ጣራ የዘለለ በመሆኑ ያንን ለመመልከት የሚከብድም ሁኔታ እንደነበረብኝ አልክደውም፡፡ ሚዲያን ከመሸሽ የሚጠቅመኝን ማንሳት የማይጠቅመኝን መተው መለማመድም እንደአለብኝም ተረድቻለሁ፡፡ የገዢው ፓርቲም ሆነ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሚዲያ ከአቅምህ በላይ ሆኖ የሚያስጠላ ነገር ይዘው ቢቀርቡም እኔ ግን በዛ ውስጥ ማለፍ ግድ የሚሆንበት ምክናያት ምንአልባት ዲሞክራሲን በሰፊው ሊያለማምደን ይችላል ብዬ ሁሉንም የፖለቲካ መሪቶች ለመከታተል ሞክሬአለሁ፡፡ የገጠመኝ ችግር ግን እውነቱን እና ሀሰቱን የመለየቱ ጉዳይ ነው፡፡ ብቻ በየትኛውም አለም ፖለቲካ የሚላወሰው የተቃዋሚውን ጉድ የሚለውን አውጥቶ ለህዝብ ማቅረብ እና ነውር ሰሪ መሆኑን ማጋፈጥ ነው፡፡ ግን የህዝብ ድምጽ ብዙውን ግዚ ተጠይቆ የማያውቅበት አገር ላይ የተቃራኒውን ጉድ ማውራት ምን ይጠቅማል፡፡ እንግዲህ አገራችን ይህን ትመስላላች፡፡ በትልቁ የተማርኩት ነገር ቢኖር ካለፈው ታሪክ መውጣት አለመቻላችን ነው፡፡ ያለፈ ታሪክ ሁልግዜ ተናዳጅ የሚያደርገው ክፍል እንዳለ መዘንጋት የለብንም፡፡ ለምሳሌ የደርግን መሻል ሰው በሚናገርበት ሰአት ቀንደኛ የደርግ ጠላት የሆነው ገዢው ፓርቲ ሊሰማ የማይፈልገው በመሆኑ ስልጣንን ለመልቀቅ ትዝ አይለውም፡፡ እንዳውም መጣሁብህ የተባለ ይመስለዋል፡፡ የኢሕአዴግ ስልጣን መያዝ የረዳው የጀግንነት ጉዳይ ሳይሆን የደርግ በሕዝብ የመጠላት ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ ደርግ ይሻል ነበር ብለን የምናወራው ወሬ ህዝብን በደርግ ላይ የነበረው ጥላቻን ሳያስተውል በዘፈቀደ ያደረገው የሚያስመስል ስድብ አይነት ውሳኔ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ጥሩ አለመሆኑን ለመግለጽ የግድ ያለፉት ጋር ማወዳደር አላስፈላጊ ነው፡፡ ብዙው የፖለቲካ አስተሳሰብን ዘግቶእና አግዶ የያዘው ካለፈው ታሪክ አለመውጣት ነው፡፡ ያለፈው ታሪክ ያለፈውን ሰርቶ አልፎአል፡፡ ታሪክን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ቢሆንም፤ ግን አስተሳሰብን ዘግቶ የሚይዝ ትብታብ ነው፡፡ የሁሉም መሪዎች የፖለቲካ ሁኔታ በዘመኑ በነበረው የአለም የፖለቲካ ባሕል የተጉዋዘ ነው፡፡ የዛሬውም የኢሕአዴግ የፖለቲካ ባሕል ከዛሬው የአለም ፖለቲካ አብሮ የሚሄድ መሆኑን እያየን ነው፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክናያት ህዝብም ወደደም ጠላም ለውጩ አለም የሚስማማ ፖለቲካ ያራመደ ስልጣን ላይ ይቆያል፤ ያልተስማማ ይወርዳል፡፡ በአካባቢው ህዝብ የተወሰነ  መሆኑ ለጊዜው የቀረ ይመስላል፡፡ ይህም በኢንቬስትሜንት ላይ የተመሰረተ የአለም የኢኮኖሚ ሁኔታ ነው፡፡ መሬትን በሰፊው ግሎባል በሆነ መንገድ ለመጠቀም ያለው ሁኔታ በአለም ላይ ሁሉ የመሬት ተፈናቃዩን እያበዛው ሄድዋል፡፡ ግሎባልን እውን ለማድረግ ጥረት ቢደረግም እውን የሚሆንበት ግዜ ግን በዳዴ ይገኛል፡፡ እስከዛው በደሀእና በሀብታም መካከል ያለው ልዩነት በጣም የተራራቀ እንዳይሆን የሚያሰጋ ሁኔታ ነው፡፡ አንዱ የፖለቲካ አካሄያድ ጥሩ ያለውን መንገድ ብቻ ሲከተል፤ የማይመለከተው ነገር ግን ኢሰባአዊነትን ስሩን እየገዘገዘው ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ሕጻናትን እራቁታቸውን ፎቶ ወይም ቪዲዮ በማንሳት የስሜት መቀስቀሻ መሳሪያ የሚያደርገው በአለም እየተስፋፋ የመጣው የወንጀል ሁኔታእና፤ ገንዘብ አግባብ በለለው መንገድ የሚያካብቱ ሰዎችን ቁጥጥር ያለማድረግ ጉዳይ ለአለም ሕዝብ ግሎባል የሆነ እራስምታት እየሆነ ሄድዋል፡፡  ስለዚህ የኢሕአዴግ ዘመን በጭራሽ ያለፈው ዘመን ፖለቲካ ጋር ሊወዳደር የማይችል የራሱን ችግር ይዞ ብቅ ያለ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ትናንት የነበረው ፖለቲካ የመሬት ባለቤትነት ከዛሬው ጋር ከእንግዲህ ሊሄድ የማይችልበት ሁኔታ የአለም የፖለቲካ ባሕል የፈጠረው መሆኑን እያየን ነው፡፡ ትናንት የእኔ መሬት እያልን ሽንኩርት እንኩዋን ሳንተክልበት ይዘን የነበረውን ጉዋሮ ዛሬም እንደዛው አድርጌ ልያዝ ለማለት አይቻልም፡፡ እንግዲህ በመሬት በኩል የሚያሙዋጉተን ነገር ዘመኑን ያገናዘበ ቢሆን ሙግታችን አለአግባብ ግዜ እንዳያባክንብን የረዳናል፡፡መሬት ለኢትዮጲያ እንደነዳጅ የሚታይ ነው፡፡ አንድን መሬት ሰው የሚወስደው ኢንቬስት ለማድረግ ሳይሆን መሬትን ሽጦ እንዲያተርፉበት መሆኑ የወረደእና ያዘቀጠ ብልጠት በኢሕአዴግ ዘመን ያየነው ነው፡፡ ይህን ችግር ለገዢው ፓርቲ ቁልጭ አድርጎ የታየው ተግባሩ ተፈጽሞ ወደማለቁ ሲደርስ ነበር፡፡ የባለስልጣናት መባለግ ያስከተለው የመሬት የጦፈ ንግድ መሬት ለኢትዮጲያ ነዳጅ እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ የተጠቀመ ተጠቅሞበታል፡፡ እንግዲህ ሰው ሕሊናውን ይወቅ፡፡ እንግዲሕ መሬት ሄደ ተቀመጠ ለአብዛኛው ሕዝብ የፈየደለት ፋይዳ የለም፡፡ መሬት ድሮም ቢሆን ከባላባትነት የመንግስትነት እያለ ሁልግዜ በገዢው ፓርቲ እጅ ሲሽከረከር የነበረ ህዝብ በአይኑ የሚያየው የጥቂት ሰዎች መጠቀሚያ ሆኖ አልፎአል፡፡ እኔ በበኩሌ መሬትን ለሰፊ ኢንቬስትሜንቶች ለወጣቱ የስራ ማምረቻ ታልፎ መሰጠቱን አልቃወምም፡፡ የምቃወመው ግን በውስጡ ያለውን የሙስና መሰሪ ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በኢሕአዴግ ዘመን ከቁጥጥር ውጪ የሆነ፤ ገዢው ፓርቲን በሕዝብ እይታ እና ትዝብት ያስገባ ከመሆኑ አልፎ ያስናቀውእና የማይታመኑበት ፓርቲ ሆኖአል፡፡ የመሬት ብልግና ሕዝብን ያሳረረ ኢሕአዴግንም ያስናቀ እንደነበር ፓርቲው እራሱ የማይክደው ሀቅ ነው፡፡ ይህ እድሀው ጉሮሮ ላይ ቆሞ መራመድ ነበር፡፡ መሬት የአንድን ግሩፕ ህይወት ለመቀየር ሳይሆን የህዝብን የአኑዋኑዋር ሁኔታ የሚቀይር እስከሆነ ድረስ፤ መሬትን ለኢንቬስትሜን ማዋልን እኔ በበኩሌ አልቃወምም፡፡ ለምሳሌ ለሰፋፊ የእርሻ ምርት ቢውል፤ምግብን ለማዳረስ ይረዳን ይሆናል፡፡ በሌላው ምልኩም ደግሞ ኢትዮጲያን የሸቀጥ ማራገፊያ ከማድረግ፤መሬታችንን ለኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ማዋል ኢምፖርት ከማድረግ ልንወጣ እንችላለን፡፡ እቃውን ለመጠቀም ገዝቶ ከማስገባት እዛው አገራችን ኢንቬስተሮች ገብተው ኢንዱስትሪውን ከፍተው ለወጣቱ የስራ እድል የሚከፍቱበትን ነገር ያመቻቸ ፖለቲካን ለመፍጠር መታገል ነው፡፡ እንግዲህ ይህ የእኔ አመለካካት ነው፡፡ መሬትን ከአንዱ ባለሀብት ወደአንዱ ማስተላለፍ እና ኪስን ማዳለብ ሳይሆን ለትውልዱ የሚተላለፍበትን መንገድ ላይ መታገል ነው፡፡ አንድ ሰው ከሚኖርበት ሰፊ መሬት የሚያመርትበት ትንሽ መሬት እንደሚበልጥ መገንዘብ ነው፡፡ ከአጉል ሕልም፤ ወደምርት የምንገባበትን ማየቱ መልካም ነው፡፡
አዎ በባንዲራው/በሰንደቅአላማችን ጉዳይ ብዙ አሰብኩበት፡፡ እኔ ተወልጀ ሳድግ ብዙ ግዜ የማየው ኢትዮጲያ ባንዲራ ላይ አንበሳ ስለነበር፤ በዛ ያደኩበት ሁኔታ ሁልግዜ በአይምሮዬ የማየው የኢትዮጲያ ባንዲራን አንበሳ ጋር አያይዠ ነበር፡፡ ሌላውን ምልከት ለመቀበልም ላለመቀበልም አስቤበት አላውቅም፡፡ አይምሮዬ ባለፈው ተይዞ ስለነበር ነው፡፡ ይህም የአንበሳ ባንዲራ ግን ሌላውን ለማብሸቅ ያደረኩት ሴራ ፍጹም አይደለም፡፡ በዚህ የተነሳ አንበሳ መውደዴ እንደልዩነት መፍጠር ሆኖ እንዲታይ አልፈልግም፡፡ሌላውንም ለመመሳሰል ብዬ ሌላም ምልከት ባደርግ ክፍፍል እንደሚፈጥር ተረዳሁ፡፡ ይህ መከፋፈል አላማዬ አይደለም፡፡ አላማዬ ሌላውንም መረዳት መፍጠር እና በአንድነት በሰላም ለመኖር ነው፡፡ ስለዚህ በበኩሌ የኢትዮጲያ
ባንዲራ ዝም ብሎ አረንጉዋዴ ቢጫቀይ ቢሆን ይሻላል ብዬ ገመቻለሁ፡፡ ይህም በሁሉም ውስጥ ልዩነትን ስለማልፈልገው ነው፡፡ አይምሮ ከጥላቻ በላይ የሚሰራው እጅግ ብዙ ስራ አለው፡፡  ባንዲራ የአገር ምልከት እንጂ የአንድ ፓርቲ ምልከት አይደለም፡፡ አንበሳውን ኢሕአዴግ እንደለወጠው ሁሉ፤ ነገ ኢሕአዴግ ሲለወጥ የሚመጣው ደግሞ ሌላ እንደሚያደርገው ከወዲሁ መገመት ነው፡፡ ይህ ያልተረጋጋ ባንዲራ መፍጠር በውጩ አለም ሀላፊነት የማይሰማን ህዝብ ሆኖ ሊያሳየን ይችላል፡፡ ትግሬም ሁን ኦሮሞ ወይም አማራ፤ አንዱን ከአንዱ የማያበላልጥ አገር ለመፍጠር ትንሽ እንደበሰለ አይምሮ ያለው ማሰብ ግድ ሊለን ይገባል፡፡ እኛ 100 አመት ወደሁዋላ ስናስብ፤ አለም መቶ አመት ወደፊት የምታስብበት ሲስተም ላይ ሳንወድ በግድ እንደምንገባ አፍጥጦ እየመጣ ያለው የግሎባሉ ሁኔታ እንድታዩ ማስተዋላችሁን ክፈቱ፡፡ የቤት ስልክ ምንነቱን የማያውቅ ክልል በድንገት የሞባይል ስልክ ተጠቃሚ ያደረገው የአለም ስልጣኔ የደረሰበት እንጂ የኢትዮጲያ ስልጣኔ የደረሰበት አይደለም፡፡ ባንዲራ የተፋቀረ ህዝብ ምልከት እንጂ በጥላቻ የሚተያይ የሚበቃቀል ፖለቲከኞች ምልከት መሆን አይገባውም፡፡  በሉ በቸር ልበላችሁ
ባዩሽ     

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen