ወገናዊነት ወገኔ ላላልከው ሕመም ነው
ዛሬ ለተበደለ በመቆርቆር
ከእምነት አገልጋዮች በላይ ፖለቲከኞች በልጠዋል፡፡ እርስ በእርሳቸው ሀጢያታቸውን ይገላለጣሉ እና፡፡ አህዛብ
የተባሉት በመገሳሰጽ እከሌ እና እነእከሌ ሐጢያት ሰርተዋል ከስልጣን ይውረዱ እያለ ይደክማል፡፡ እከሌ እርቦታል
ጠምቶታል ይላል፡፡ ስለተሳሳቱ ስላዳሉ የምድርን ስልጣን አይገባቸውም እያለ ይጮሃል፡፡ ዛሬ ግን ቤተክርስቲያን
ተስማምተው ወንጀልን በሚደባበቁ ቀሳውስቶች የእግዚአቤሄር ቤት የሀጢያት ደባቂ እየሆነች መጣች፡፡ እርስ
በእርሳቸው የወንጌላዊው፤ የፓስተሩ የዘማሪው ደጋፊ እና ቲፎዞ አበጁ፤ ለሰው የማይታይ ለእግዚአብሄር የማይታይ
መሰላቸው፤ ሰማዩን የሚያዘጋ መንፈስ ቅዱስን የሚያርቅ ስራ ፈጸሙ፡፡ ሐጢያት ዝም ሲባል ሁሉ ያደርገዋልእና ጤነኛ
መሰለ፡፡ እንዳውም ሀጢያት ያለ ነው ይሉን ጀመር፡፡ የሚሰርቀውንም እግዚአብሄር የመረጠው ነው ይሉን ያዙ፡፡ ለእነሱ
ለሰሩት ሀጢያት መቀጫ ይሆናል ብለው ግን ሊነግሩን ፈሩ አልያም አይደፍሩትም፡፡
የቤት ቁዝምዝም እቃ
ይፈጃል እንዲሉ፡፡ የክርስቶስ ሳይሆን የፓስተሮች የቄሶች ስም የነገሰባት ቤተክርስቲያን እየሆነች መጣች፡፡ ሰው
እንደፈለጋችሁ ልበሱ ጠጡ ብሎ ሁኑ የሚል፡፡ ሴቱ ቆዳውን መለጠጥ ጸጉርን መቀጠል እና ቂጡን መቀጠል፤ ለሰው የቀናው
እግዚአብሄር የለወጠው መስሎ እንዲታይ ተደረገ፡፡ ከቶም በተሰጣቸው ስጋዊ ማንነት፤ በአፍንጫቸው አፈሩ፤
በሰውነታቸው በጸጉራቸው ተሸማቀቁ፡፡ በእግዚአብሄር ትእዛዝ ሳይሆን በሰው ትእዛዝ የምትመራ ቤተክርስቲያን፡፡
ያለባበስ ችግር እና የመልክ ችግር ሆነ እና የሰው ልጅ ችግሩ፡፡ በእሱስ ነጻ አወጡን፡፡ እኛም አማርን
አሸበረቅን፡፤ ባታችንን ዳሌያችንን ይህ ነው እኔ እበልጣለሁ የሚሉ ውድድር ውስጥ ገባን፡፡ በቢሮም በትዳርም ተፈላጊ
እሱዋ እንድትሆን፤ ተመከረ፡፡ በአፍሪካ ሁሉን በማያዳርስበት ሚካፕ ጸጉር ቅጠላ፤ ያሸበረቀ ለብስ፤ ሰውን ሰውን
የሚያበላልጥ አዋጅ ታወጀ፡፡ ማድረግ ያልቻሉ እውቀታቸው ሳይሆን ሰውነታቸው መመዘኑ አይቀርም እና፡፡ በአይን
የሚበላበት አገር እያፈራን መጣን፡፡ ይህ ሁሉ ሙስና ጋባዠ መሆኑ ግን የገባው እና የተረዳው የለም፡፡ ያለበሰችው
ተናቀች ተሰደበች፤ ባላገር የማትሰለጥን መበል መጣ፡፡ ሁሉም ለንዋይ እሩጫ ሆነ፡፡ መንፈሳዊው ግን እንደታሰረ
ሳይፈታ አለም ልታልፍ መሆኑን ለማየት አሳወሩን፡፡ እሱ ከባድ ነው እና እሱ ገሳጭ ነውእና ፡፡ እንዳውም ለአገር
ለወገን የሚጠቅመው፤ የሰው የስጋ ልብሱ ሳይሆን፤ የመንፈሳዊ ልብሱ ነበር፡፡ እሱ ግን ክልክል ነው፡፡ሌባን ሌባን
ማለት አይቻልም፤ አይገሰጽም፡፡ የሚገርም የሚደንቅ መንገድ ተያዘ፡፡ለንዋይ ውድድር፤ ሰው እራሱን ሸጨ፡፡
እንደእውነቱ ሽሕ ምእመናን ከሚደናገረው እና መደነጋገር ላይ ከሚወድቅ፤ በአንድ ሰውም የተነሳ ዝማሪያችሁ እና
ጸሎታችሁ ሰማይ የሚያዘጋ እንዳይሆን፤ ከማሃልህ ያለውን የፓስተር፣ የቄስ የዘማሪውን ሰው ነውር አጋልጠው፤ ለየው
በአደባባይም እንዲጸጸት እና ንስሃ እንዲገባ አድርገው፡፡ መልሰህም ያንን ቦታ አትስጠው፡፡ አርአያነቱን አጉሎአል
እና፡፡ ተወካይነቱን ንዶአል እና፡፡ ይህንን በቤቱ ካደረክ አርአያ ቤተክርስቲያንህ ትሆናለች፡፡ እንዳው ምእመናኑ
ቁጥሩ እንዳይቀንስብኝ፤ እያለክ፣ አየሁ አላየሁም ብለህ የምታልፍ ከሆነ፣ ምእመናን ውስጥ ጉዳዩን ቀብረሃል፤
ወገናዊነት ወገኔ ላላልከው ቁስል ነው፡፡ እንኩዋን አዲስ ሰው ልትስብ፤ የያዝከውም ስጋው እንጂ መንፈሱ
ተለይቶሃል፡፡ ሰማይን የሚያዘጋ ስራ ሰርተሃል፡፡ አድራጊው ብቻ አይቀጣም፤ እያየውም ያልገሰጸው፤ እየሰማም ልቡ
ያመረቀዘው ሁሉም ሀጢያት ሰርቶአል፡፡ ከሀሰት ጋር የምትተባበር ቤተክርስቲያን የጌታ ጣት ያለባት አትሆንም፡፡ እሱ
የመሰረታት የተለየች ነች፡፡ ወዳጄ ሆይ በጌታ የተመረጠው የመጽሃፍ ቅዱስ ዳዊት እንኩዋን ነውሩ በመጽሃፍ ቅዱሱ
ተጽፎ ቀርቦአል፡፡ አንተም እየተማርክበት እና እያስተማርክበት ነው፡፡ ሌላው ግን በአንተ ጽድቅህ እንጂ ሀጢያትህ
እንድንማርበት የማትፈልገው አንተ ማነሕ? ምነው ወንጌል በብዛት ተሰበከበት በተባለችበት ኢትዮጲያ፤ የሰው ልጅ
በትእቢት የተወጠሩ፤ ጉቦ የሚበሉ፣ የሚያዳሉ፣ በዘር የሚለዩ በሀሰት የሚፈርዱ ዳኞች፣ ሰውን የሚደበድቡ ፖሊሶች፣
ሰራተኞች በምድሩ ላይ በዛ? ንዋይ ያሳበደው ዜጋ ተተካ ፡፡ ህንጻው ያማረ ውስጥ ኑዋሪ፣ የሚያብረቀርቅ ልብስ
ለባሽ የቆሸሸ ህሊና ተሸካሚ ለምን ሆነ? እራስህን ከሌላው ሀይማኖት ጋር ለማወዳደር ለምን ትሮጣለሕ፤ ወዳጄ ሆይ
አንድ ነገር ልበልህ፤ ቤትህን የምታጸዳው ሌላው ሲያጸዳ አይተህ ነው እን? እኔስ የምጠብቀው እንግዳ ካለቀጠሮ
ይመጣል እና ልዘጋጅ አትልም?
ቤተክርስቲያን ደግሞ ለምእመናኑዋ ትግለጠው፡፡ ሀጢያት መማሪያ መሆኑን፤
ከዳዊት ነፍስ ገሎ ተደብቆም መደበቅ አለመቻሉን አንተ ተምረሃል በእሱም አስተምርሃል፡፡ አንተ ሀጢያትን
ካላወጣህ፤ ነገ የእግዚአብሄር እብድ የተባለው እሱ እራሱ በመረጠው አስነስቶ በሚልከው ይገልጠዋል፡፡ አንተ
በጉዋዳህ የደበከው ለለአደባባይ ነገ ይታወጃል፡፡ ነውርን የደበቀች ወይም የምትፈጽም፤ የምትተባበር የሌባ ደባቂ
እንጂ፤ እሱም የአባቱ ን ቤት ሊያጸዳ ይነሳል፡፡ አፍርሶም ይገነባታል፡፡ ስለእዛ አንተ በቤትህ ስሙን አጥፍተህ
እንዲሸማቀቅ ያደረከው ትክክለኛ አማኝ፤ እግዚአብሄር ተነስቶ አንተን ደግሞ በአደባባይ እንድትዋረድ ያደርጋሃል፡፡
እግዚአብሄር ትናንት ይህን ሰርቶአል፡፤ ዛሬም ይሰራል ነገም ይቀጥላል፡፡ አለም እስከምታልፍ፤ እሱም የእሱ
ይሆኑትን እስከሚሰበስብ ድረስ ህዝቡን አይጥልም፡፡ የማያምን ሰው እንኩዋን ቢሆን እግዚአብሄር ሀሰትን ስሩበት
አላለም እና፤ ለማያምንም ሊፈርድ ይነሳል፡፡ እሱ የእውነት አምላክ ነውእና፡፡ ሰላም ይብዛላችሁ፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen