Samstag, 13. Dezember 2014

„ገረድ“ ሴትን የሚረግጥ ቃል





 „ገረድ“ ሴትን የሚረግጥ ቃል

 አቶ ሀይለማርያም እውጭ በሚኖሩ ኢትዮጲያውያኖችን  የስድብ ትችት አቀረቡባቸው ተብሎ  በኢሳት ዜና የተዘገበውን ሰማሁ፡፡ የተላለፈው እውነት ነውን? እውን ከሆነ ያሳዝናል፡፡ ይገርማል፡፡ ከሆነ ብዬ የምናገረው ከአንድ የአገር መሪ ግራ በተጋቡ ወጣቶች ላይ ይህ አይነት ንግግር አሳፋሪ ነውእና ነው፡፡ አቶ መለስ ቢሳደቡም ወዝ ቀብተው ነው የሚሉ እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ግን አቶ ሀይለማርያም የደረቀ እና ለዛው የተሙዋጠጠ ሆነብኝ፡፡ እንዳውም የኢሕአዴግን መውደቅ የሚፈልጉ መሪ ሊሆኑ ይችላሉ የሚልም ጥርጣሬ ያዘኝ፡፡ ምክናያቱም የበለጠ እንዲጠላ የሚያደርግ የቃላት አወራወር ሆኖ ስላገኘሁት ነው፡፡ ለምን ቢሉ ፖለቲካ ሲሉ፤ ቃላትን ቆሞ የሚጠብቅ አለእና ነው፡፡  የመናገር ችሎታ በፖለቲካ አልም የሚጀምረው ማንኛውንም የሰው ልጅ በማክበር እንጂ በመዝለፍ አይደለም፡፡   ሰው የሚባል፣ በሚሰራው የስራ አይነት እና ልብስ መሰደብ መተቸት የለበትም፡፡ ይህ ስብእና ግብረገብነት የሚያስተምረን ትምህርት ነው፡፡ እኔ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበርኩበት በዛን ዘመን፤ ግብረገብ እንደ አንድ የትምህርት ክፍል የሚሰጥ ነበር እና፤ ሰው „ገረድ“ የሚል ለስራ ስም  እንዳንሰጥ ሁለተኛ ክፍል ያስተማሩኝ ትዝ ብሎኝ ነው፡፡  የሚችለውን እና ያገኘውን ሰርቶ ቤተሰብን ማስተዳደር አንዱ መብት ነው፡፡ ለዛውም  በኢትዮጲያ ለ90% ወጣት ስራ የለለበት አገር፡፡ ስራ አገኝ ብሎ ወጣቱ የአባቱን ቤትና ንብርት እያሲያዘ ለመነገድ፤ ተጨማሪ ትምህርት ለማግኘት እና እውድድሩ አለም ለመግባት ለኮሌጅ ከፍሎ በመማር ደግሞም ለውጭ አገር ደላላ/ አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ/ በመክፈል ወንዝን እሻገራለሁ ብሎ ለአዞ ለሚሰጠው ባለጀልባ በመክፈል ሕይወትና እና ኑሮ አስገድዶት፤ ኑሮ ግራ ያጋባውእና የሚራወጥ መሆኑን የኢትዮጲያ መንግስት ያውቀዋል፡፡ አቶ መለስ ቢሆኑ እንኩዋንም ስራ አገኘልኝ ይሉ ነበር የሚል ግምት አለኝ፡፡ ምክንያቱም እዛ ሆኖ ጉሮሮአቸው ላይ እንዲቆም አይፈልጉም እና፤ በብልጥነት ተጉዘዋል፡፡  ታዲያ ኢትዮጲያ ቢቀመጥ ወጣቱ ምን ያገኛል ነው የእኔ ጥያቄ፡፡ ምንአልባት ኢትዮጲያም ገንዘብ እና ስራ የሞላቸው ሰዎች አገርም እየለቀቁ እየወጡ ብናይም ይህም ቢሆን በአገራቸው ለመኖር ዋስትና ያሳጣቸውን ነገር መርምሮ መድረስ ተገቢ ነው፡፡ እነሱም እዚህ መጥተው ኮሌጅ ሳይሆን ስደተኛ ሆነው እጃቸውን ይሰጣሉ እና፡፡ ደግሞም በሌላ መልኩ፤ ከኢትዮጲያ የሚወጣው ሰው የቸገረው  እና ግራ የተጋባውም ወጣት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጲያን ትምህርት የናቀ ቤተሰብ ባበጠ የኢትዮጲያ ብር ለማስተማር ልጁን ወደአሜሪካ እና ኢይሮፕ የሚልክም እንዳለ በአፍሪካ ታሪክ ይታወቃል፡፡ አንድ ነገር እግረመንገዴን ልበል፡፡ የኢትዮጲያ ፖለቲከኞች እውን በኢትዮጲያ ትምህርቱን አሻሽለን ጥሩ አድርገነዋል ካሉ ለምንስ በውድ ገንዘብ ልጆቻቸውን ለማስተማር ወደውጭ ይልካሉ ነው የብዙዎች ጥያቄ፡፡

        ስደት ዛሬ የመንግስትን ሸክም ማቅለያ እና ከቶም ለኢሕአዴግ መገልገያ የፕሮፖጋንዳ ማሽን እንደሆነ ብዙዎች ይተቻሉ፡፡ ኢሕአዴግን የሚወደውም እጅግ ብዙ ስደተኛ እንዳለ እና ምንም አይነት የተቃዋሚ ነገር ላይ የማይገኝ እንዳለ ሆድ ያውቃል፡፡ እንግዲህ እነሱን መንካት መሆኑን ያልገባቸው አቶ ሐይለማርያም የማይመች ስብእናን የሚነካ ቃል ማውጣታቸውን እየሰማን ነው፡፡ኢሕአዴግንም ደግፈህ ግባ አልያም የእውነት የፖለቲካ ችግር ይኑርህ ስደተኛው ገረድ ከተባለ እና ዱቄት በሌታ ከሆነ ሁሉም ነው፡፡ ኢሕአዴግንም ደግፎ የመጣ እንደእውነቱ እውጭ አገር ላለው ለሰው አገሩ መንግሰት ምንም ከጤፍ የሚቆጠር አይደለም፡፡ እንዳውም ይህ ቢታወቅ ምን ልትፈልግ ታዲያ ስደተኛ ሆንክ ይመጣል፡፡ ስደተኛ ማለት ያለውን ገዢ ፓርቲ የጠላ፤ የተጣላ ማለት ነው፡፡  አቶ ሀይለማርያም ማወቅ የነበረባቸው ሁሉም እድሉን አግኝቶ በኢትዮጲያ ፊደል እንኩዋን ያልቆጠረ እንዳለ እና ይህም ክፍል ሰርቶ የመብላት መብት እንዳለው የተረዱ አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጲያ መደሰቻነትዋ  ከመካከለኛው መደብ በላይ ለሆነው ስለሆነ፤  „ገረድ“ መሰል ቁዋንቁዋ እና ሰው በሚበላው ተንቆ መነገሩ መልክትነቱ 70% በላይ የሆነውን ህዝብ በንቀት መታየቱን የሚገልጽ ነው፡፡ አሁንም የሰብአዊነት ክብሩ እየተገፈፈ የሚሄደው የታችኛው ክፍል እንደዛው እንደነበረ እና እንዳለ እየተሸጋገረ የሚሄድ ግፍ መሆኑ በእራሱ በአቶሀይለማርያም ከባዱን ቃላት ቀለል አድርጎ ማውጣት አለመቸገራቸውን ያስረዳል፡፡

 ለመሆኑ ዛሬ ዩንቨርሲቲም ጨርሱ የተባሉት በየትም ክልል ተገረዱም ዱቄትም በሉ በየትኛውም አለም ተበትነው፤ የእለት ኑሮአቸውን መግፋት ይዘዋል፡፡ የተማረውንም የስራ ቦታ እንደለለውእና ያለችውም ትንሹዋ ስራ ቦታ የሚያገኛት ማን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሙስና እና አድሎ በተስፋፋበት አገር ይህ የሚጠፋው አለ ብዬ አልገምትም፡፡ ውጭ የወጣ ሰው  ከእለት ጉርሱ አልፎ ኢትዮጲያ ያለውን ቤተሰብ በመርዳት አንቱ ያስባለው ቁጥሩ ቀላል አይደለም፡፡ ታዲያ የአንድ ፓርቲ የበላይነትን የሚያስተናግደው የኢትዮጲያን መንግሰት በውጭ የሚኖረውን ሰው ያቃለለ መሆኑን ልብ ያውቀዋል፡፡ ይህ እንዳው ስድብ ምሁሩንም ሆነ ወይም ያልተማረውን የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ስደተኛውን ስብእና የሚነካ ነው፡፡ አቶ ሓይለማርያም የተናገሩት እውን ከሆነ የውጩንም መንግስት የሚነካ ይሆናል፡፡ በተለይ በጀርመን አገር ለስደተኛው ደፋ ቀና የሚል ብዙ ሰብአዊ መብት ተሙዋጋች ስላለ አቶ ሃይለማርያምን የት ነው ዶቄት የሚበላው ብለው እንዲነግሩዋቸው ይጠይቁ ነበር፡፡ እውነት ያዩት ትክክል  ከሆነም፤ አቶ ሀይለማርያም የሕንን እይታ ለዘለፋእና ለፖለቲካ ፍጆታ ባልተጠቀሙበት ነበር፡፡ ምክናያቱም ለወጣቱ በኢትዮጲያ የሚያቀርቡለት ነገር አንዳችም የለም፡፡ እንዳውም ወጣቱን ለማሳደግ ቀርቶ፤ ጥቂት ያሳደጉዋቸው ምርጦቻቸው  ጋር እንዲወዳደር እና እንዲቀናና የማድረግ የመከፋፈል ተጽእኖ በኢሕአዴግ ዘመን ይታያል፡፡ አንዱን የሚረባ አንዱን ደግሞ የማይረባ አድርጎ የሚያቀርብ የፖሎቲካ አካሄድ የት እንደሚያደርስ ባናውቀውም ግን ኢሰብአዊነት መሆኑን የምናቀው ሀቅ ነው፡፡
ያልተማረም ገረድ የተባለችውም ሴት በአገሩዋ እኩል መብት ያላት መሆኑን ማወቅ ያልተረዱ የሚመስሉት አቶ ሀይለማርያም፤ በሕዝብ መካከል አዲስ መደብ እየፈጠሩ መሆኑን እያየን ነው፡፡ ይህ በእጅጉ የሴትን ስብእና የሚነካ ሁዋላ ቀር አነጋገር በውጭ አገር ያለው የሴቶች መብት ሊያስብበት እና ሊነጋገርበት የሚገባ ነው፡፡ በአገራችን  ሴት የቤተሰብ ሃላፊነትን ወስዳ በኑሮው ውድነት በተጨናነቀችበት ጊዜ ፣ያገኘችውን ስራ አግኝታ ሃላፊነቱዋን ለመወጣት ወደማታውቀው አገር በደመነፍስ በምትጉዋዝበት ግዜ እና ለሞት ለአስገድዶ መደፈር በተሰጠችበት ግዜ ስነልቦናዋን የሚገነባላት „ገረድ“ መባል ከሆነ ሁላችንም ልናፍርበት ይገባል፡፡ ከቶም ይህ ቃል ከኢትዮጲያ መጥፋት ያለበት እንጂ በመሪ በመዝናናት በማሾፍ የሚነገር መሆን ባለተገባው ነበር፡፡ ይህ የሚያሳየን ተናዳጅ ባህሪንፖለቲከኞች እየተላበሱ መምጣታቸውን ነው፡፡  እንኩዋን እሳቸው ተናገሩ የተባሉት ይቅር እና እኔ ለእራሴ ልሰማሁትም ከብዶኛል፡፡ ስርአት ካለው ቤታስብ ከወጣን ይህንን መልካም እንዳልሆነ እናውቃለንእና፡፡ ዛሬ ጌታ የሆነ ነገ ገረድ የማይባልበትም ምንም አይነት የሕየይወት ዋስትና እግዚአብሄር አልሰጠንም፡፡ ነግ በእኔ ማለት መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር ባህርን አቁሞ ከተማን ባህር ያደርጋል እና፤ ልብ ማለት መልካም ነው፡፡ ሮምም አንድ ወቅት የአለም ታላቅ ነበረች እና፡፡ በቸር የምላችሁ ባዩሽ ነኝ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen