በኢትዮጲያ የ20 አመቱ የስነልቦና ውጊያ
አንድ ግዜ ስለጥንቆላ
ብዙ አወሩኝ፡፡ ይገላል፤ ያሳብዳል፤ ደሃ ያደርጋል እያሉ፡፡ በዚህም የተነሳ የምኖርበትን አካባቢ የጠንቁዋይ አገር እንደሆነ ነገሩኝ፡፡
እኔም እረጅም ግዜ ፈረንጅ አገር ቆይቼ የተመለስኩ በመሆኔ፤ ግራ ተጋባኝ፡፤ በልጅነቴ ስለዚህ አካባቢ እንዲሕ ሲወራ አልሰማሁም
ነበር፡፡ አሁን ግን የምሰማው የሚያስፈራ እና አካባቢውን እንድጠላ የሚያደርግ ነበር፡፡ በቃ ወሬው ሁሉ አካባቢው እንዳይታመን የሚያደርግ
ሆነብኝ፡፡ የጥንቆላውንም መንገድ አስረዱኝ፡፡ እሱም ከቆሸሸ ልብስ ላይ ጨርቅ በጥቀው ይወስዳሉ የሚል ነበር፡፡ እጅጉን ገረመኝ፡፡
አንድ ነገር አሰብኩ፡፡ ሰይጣን የሚፈልገው የቆሸሸ ነገር መሆኑእና እግዚአብሄር ደግሞ የጸዳ ነገር መሆኑ ልዩነቱ እርኩስ በእርኩስ
በቆሸሸ እንደሚሰራ ልብ አልኩ፡፡ ይሁንእና ግን የቆሸሸ ልብስ እንዴት መጠበቅ እንዳለብኝ ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡ በበኩሌ ከእርኩስ
መንፈስ እራሴን የምደብቀው ልብስ በመደበቅ መሰለኝ፡፡ ጊዜዬን የሚሻማ፣
አይምሮዬን የሚበላ፣ ተጠራጣሪ የሚያደርግ፣ አካባቢውን እንዳላምን የሚያደርግእና የእራሴኑ ብሄር እንዳላምን የሚያደርግ
የቤት ስራ እንደተዘጋጅልኝ ግን ማመን አልቻልኩም፡፡ የሚገርመው ይህንን ሆነ ብላ ከምታስረዳኝ ሴት ጋር ግን ግንኙነቴ አላቁዋረጥኩም
ነበር፡፡ ምክናያቱም ሰው የተሰጠውን ኢንፎርሜሽን የሚያምነው በነጋሪው ብርታት እንጂ በወሬው እውነትነት በማረጋገጥ እንዳልሆነ ከእኔ
ሕይወት ከእኔ ስህተት ልትማሩት ይገባል፡፡ ይህንን ውስጤን ሽብር
የሚለቅብኝ ነገር የምትመግበኝ ሴት ላይ ፍጹም የሆነ እምነቴ ወደቀ፡፡
የሚገርመው ተቆርቁዋሪዬ
አሳቢዬ አድርጌ በእምነት አይን እመለከታት ነበር፡፡ የህንን ኢንፎርሜሽን
ጠንቁዋይ የሚያምን ሰው ሊነግረኝ አይችልም በማለት ሕይወቴ ስለእሱዋ ክፍት ሆነ፡፡ ከዛም አልፎ እከሌም እከሌም ጠንቁዋይ አምላኪ
መሆኑን እና የእከሌን የእከሌን ልጅ አሳብደዋል በማለት ሰዎችን በእራሱ አድራሻ በመስጠት እንዳላምናቸው ታደርገኝ ነበር፡፡ እነዚህ
ሰዎች ግን ከቤተክርስቲያን የማይለዩ ሰዎች ነበሩ፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሄር የሚታይባቸው እና ፍጹም በኦርቶዶክስ እምነት ባህል የሚኖሩ
መሆናቸውን አየሁ፡፡ የእኔ አለመብሰልን የምታሽከረክረው ሴት ግን ከእነዚህ ሰዎች ፍጹም እንድርቅ የሚያደርግ እንዴት ይህን ያደርጋሉ
በሚል ውስጤ እንዲጠላቸው በማድረግ እንድፈርድባቸው በሀጢያት ባህር አሰመጠችኝ፡፡ ከረጅም ግዜ በሁዋላ አገሬ ወጣ ገባ ማለት የጀመርኩት
ሴት፤ ኦርቶዶክስ ነኝ ልበል እንጂ ሰይጣን የማይታመን ልፍስፍስ መሆኑን ግን የማቅበት የመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት ብስለት አልነበረኝምእና
ከኦርቶዶክስም እንድለይ እየሆንኩ መጣሁ፡፡ በዚህ የተነሳ ጠንቁዋይ ይወዳሉ፤ የሚባሉትን ሰዎች ሁሉ አምርሬ ለመሸሽ ወሰንኩ፡፡ ፈረንጅ
አገር ስኖር ይህን አይነት ነገር ሰምቼ ባለማወቄ እና የኖርኩበት ባህል እውነቱን እውነት ሀሰቱን ሀሰት ብሎ የሚናገር በመሆኑ ኢትዮጲያ
ተመልሼ ስኖር፤ የሚነግሩኝን ሁሉ የማምን ሆኘ ነበር፡፡ ዛሬ በተቃራኒው እውነቱንም እንዳላምን የሚያደርገኝ ነገር ከአገሬ እንዳካብትኩ
እና ለጀርመኖችም አዲስ የማላምን ባህሪ ይዠ እንደተመለስኩ እውን ሆኖአል፡፡
የሰው አገሩ የሰጠኝ የማመን ተሰጥትኦ አገሬ ስገባ ገደል እንዲገባ ያደረገው፤ የሰው ልጅ ምን ያህል በሚያወራው ኢስብአዊነት
የለለው የአንድ አገርን ህልውና የሚፈጥር ጠንቁዋይ የሚለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ነበር፡፡
እኔም የተነገረኝን
እንዳምን ያደረገኝ የማይዋሸው በውጭ አገር የነበረው አብሪያቸው ያሳለፍኩት ፈረንጅ ጉዋደኞቼ ባህሪ እና ባህል ነበር፡፡ አንደኛው
የእራሴ ውድቀት በእምነት ያለመብሰሌ ጉዳይ የእግዚአብሄርን ሀያልነት እና መቻል ባለመረዳቴ ለጥንቆላ መርበትበቴ ነበር፡፡ ይህን
ግን የሚያዝናናቸው አውሪዎች ለእኔ አይምሮ መናጃ የተዘጋጁ እና ሰው እርስ በእርሱ እንዳይተማመን ለመኖር ብርታት እንዳያገኝ የተደረገ
መሰሪ ጉዳይ መሆኑን መረዳት ያልቻልኩት እኔ በሽብር መኖሬን ቀጠልኩ፡፡ ሳይውል ሳያድር ግን ቡታንታ/ግልገል ሱሪ አልያም የውስጥ
ሱሪ ወይም ፓንት/ ካልስ የካኒተራ በብትብቻው በኩል ሱሪ ሌላም ሌላም እስከአንሶላ ድረስ እየተቆረጠ ማየቴን ቀጠልኩ፡፡ ይህም ሽብሬን
ሊያጠብቀው ቻለ፡፡ ነጋሪዎቼንም እውነተኞች ናቸው ማለት ጀመርኩ፡፡ ፈቅሬንም አጠበኩ፡፡ ማን እንደሚቆርጠው ግን ማየት ተሳነኝ፡፡
አካባቢየንም ለመጥላት የምገደድበት እና ምን አይነት ባህል ነው ማለት ጀመርኩ፡፡ ሰው ተወልዶ ካደገበት አገር የትም አይሄድምእና
ልቤ በውነት እየተሰበረ፤ እንደእውነቱ እያመመኝም ሄደ፡፡ ፍርሀቴ እንደሚያሳምምኝ እንደሚረብሸኝ ባለማወቄ ጠንቁዋዩ በተቆረጠው ልብሴ
ሰርቶአል ማለት ጀመርኩ፡፡
በዚህም የተነሳ እግዚአብሄርን
ምን አደረኩህ እያልኩ መውቀስንም ተያያዝኩት፡፤ እግዚአብሄር ግን ያደረገኝ ነገር የለም፡፡ ጆሮዬን ለወሬ እና ለመደነጋገር የከፈትኩት
እራሴ መሆኔን ዘነጋሁ፡፡ለእኔ እግዚአብሄሬ እንዲደነጋገረኝ የተላኩት ሰዎች ነበሩ፡፡ ለነገሩ ጠንቁዋይን በጠንቁዋይ፤ ደብተራን በደብተራ መምታት ይቻላል ቢባልም
እኔ ግን በጭራሽ ወደጠንቁዋይ መንገድ ልመራ አልቻልኩም፡፡ አስቀድሞ አለ ተጠንቀቂ ተብሎ የተነገረኝ ከአቅም በላይ በሆነው የልብስ ቆረጣ ምክናያት የምይዘውን የምጨብጠውን አሳጣኝ፡፡
ጭንቀቴም ደሜን እየጨመረ ጠቅላላ ትዳሬንም ሆነ ኑሮዬን መበጥበጥ ያዘ፡፡ ከዚያም አልፎ ደሜ እየጨመረ እና መኪናም መንዳት እስከሚያቅተኝ
ኑሮዬ በዚህ መልኩ ቀጠለ፡፡
ዛሬ ግን
አንድ ነገር ተረዳሁ፡፡ ልብሴን የሚቆርጠው ጠንቁዋይ ሳይሆን ወይም ሳትሆን፤
1. ስውር አጀንዳ ያለው፤ አካባቢውን ብሄሩን ስሙን ጠንቁዋይ በማለት ስሙን የሚያስጠፋ፣ ማንነቱን የሚጥል፣ እንዳይታምን
የሚያደርግ ፕሮፖጋንዳ ሲሆን፡፡ ከሌላው ማህበረሰብ ወይም ጎጥ ተለይቶ እና አንሶ እንዲታይ እንዲሸሽ የሚያደርግ 2. ከእኔ ጋር ብቸኛ ጉዋደኝነትን ከጥቅም አንጻር የፈለገ ወይም የፈለገች
ሲሆኑ 3. እነዛም ጠንቁዋይ የተባሉ ሰዎች ደግሞ በአካባቢው እንዳይታመኑ የተደረጉበትንም ምክናያት ስረዳ ፤ ተልካሻ የፖለቲካ ታርጌት
እንዳይደመጡ እና እንዲገለሉ፤ የሚያደርግ ሆኖ አገኘሁት፡፡
እኔ
አዳማጩዋ የሀበሻ ፈረንጅ፤ የተነገረውን የሚያምን ስሆን፤ ነጋሪዎቼ
ደግሞ ሰይጣን ያሰማራቸው እና የከፈላቸው ሆድ አደሮች ሆነው አግኝቻለሁ፡፡ ጠንቁዋይንም አስጠንቁዋይኑም በአይምሮ ያስቀመጠልኝ የጥላት
ወዳጆች እግዚአብሄር ይሁናቸው፡፡ በአንድ አካባቢ ላይ የሚደረግ ዘመቻ
የብዙ ሰዎችን አይምሮ በመበከል እንዳይታመን ይሆናል፡፡ በዚህ የተነሳ በማንኛውም እምነት በመዞር መንፈሳዊ ጥንካሬ ይሰጡኛል የምላቸውነገሮች
ሁሉ ስማር ቆየሁ፡፡ እንግዲሕ ያለፉትን 20 አመታት የተዘጋጀልኝ የማይጨበጠው ሽበር ፈጣሪ ጠንቁዋይ ለአይምሮዬ የቤት ስራ ሆኖ
ቆይቶአል፡፡ ጥንት ምንም አይነት ነገር ሲወራ የማይሰማበት አካባቢ ለምን ባለፉት ጥቂት አመታቶች ጥንቆላ ደብተራ የሚለው ነገር
እንግዲህ እንደገነነ በዚህ ተረዱ፡፡ ሰይጣን የለም ልላችሁ አልችልም፡፡ እርኩስ መንፈስ የለም ልላችሁም አልችልም፡፡ ግና የእኔ
መደነጋገር የተፈጠረው ሰው ሰራሽ ድራማ መሆኑን ልታውቁት ይገባል፡፡ ለብሴም የሚቆረጠው ለጥንቆላ ሳይሆን ለሽበር እኔን ለመለየት
ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ የእኔን አይምሮ ለመበረዝ እና ከሰዎችም እንድለይ የሚያደርግ በመሆኑ እናንተም ወሬ ስትሰሙ ከምን መነጨ ከምን
ተነሳ ብላችሁ አስቡ፡፡ እንግዲሕ የእናንተ የቤት ስራን ይዞላችሁ የመጣው፤ እህት ወንድም፤ ቤተሰብ፤ ጉዋድኛ አልያም ስራ ባልደረባ፤
ፖሊስ ወይስ ሌላ? አንድ ነገር ግን እላችሁዋለሁ፡፡ መልስ ከማታገኙለት የቤት ስራ ውጡ፡፡ ወደፊት መሄድ ካሰባችሁ ማለቴ ነው፡፡
በአይምሮአችሁ በተለያየው ነገር የበረዘውን የቤት ስራ መልስ የለውም እና ለቤት ስራ ሰጪው እንዳለ መልሱለት፡፡ እግዚአብሄር ይርዳን
አይናችንን ለመክፈት፡፡ ደብተራ የሚለውን ቃል እንዲጋነን ያደረገው የቤት ስራው ነውእና፡፡ ሁለም ንስሃ ይግባ፡፡ ዛሬ ከዚህ መደነጋገር
ውስጥ ወጥቼ ነገሮችን አመዛዝኘ መልስ እንዳገኝ ላደረገኝ ፈጣሪ አምላክ ክብር ምስጋና ይሁን፡፡ ባዩሽ አበበ ነኝ፡፡