Sonntag, 28. Dezember 2014

በኢትዮጲያ የ20 አመቱ የስነልቦና ውጊያ



በኢትዮጲያ የ20 አመቱ  የስነልቦና ውጊያ

                  አንድ ግዜ ስለጥንቆላ ብዙ አወሩኝ፡፡ ይገላል፤ ያሳብዳል፤ ደሃ ያደርጋል እያሉ፡፡ በዚህም የተነሳ የምኖርበትን አካባቢ የጠንቁዋይ አገር እንደሆነ ነገሩኝ፡፡ እኔም እረጅም ግዜ ፈረንጅ አገር ቆይቼ የተመለስኩ በመሆኔ፤ ግራ ተጋባኝ፡፤ በልጅነቴ ስለዚህ አካባቢ እንዲሕ ሲወራ አልሰማሁም ነበር፡፡ አሁን ግን የምሰማው የሚያስፈራ እና አካባቢውን እንድጠላ የሚያደርግ ነበር፡፡ በቃ ወሬው ሁሉ አካባቢው እንዳይታመን የሚያደርግ ሆነብኝ፡፡ የጥንቆላውንም መንገድ አስረዱኝ፡፡ እሱም ከቆሸሸ ልብስ ላይ ጨርቅ በጥቀው ይወስዳሉ የሚል ነበር፡፡ እጅጉን ገረመኝ፡፡ አንድ ነገር አሰብኩ፡፡ ሰይጣን የሚፈልገው የቆሸሸ ነገር መሆኑእና እግዚአብሄር ደግሞ የጸዳ ነገር መሆኑ ልዩነቱ እርኩስ በእርኩስ በቆሸሸ እንደሚሰራ ልብ አልኩ፡፡ ይሁንእና ግን የቆሸሸ ልብስ እንዴት መጠበቅ እንዳለብኝ ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡ በበኩሌ ከእርኩስ መንፈስ እራሴን የምደብቀው ልብስ በመደበቅ መሰለኝ፡፡ ጊዜዬን የሚሻማ፣  አይምሮዬን የሚበላ፣ ተጠራጣሪ የሚያደርግ፣ አካባቢውን እንዳላምን የሚያደርግእና የእራሴኑ ብሄር እንዳላምን የሚያደርግ የቤት ስራ እንደተዘጋጅልኝ ግን ማመን አልቻልኩም፡፡ የሚገርመው ይህንን ሆነ ብላ ከምታስረዳኝ ሴት ጋር ግን ግንኙነቴ አላቁዋረጥኩም ነበር፡፡ ምክናያቱም ሰው የተሰጠውን ኢንፎርሜሽን የሚያምነው በነጋሪው ብርታት እንጂ በወሬው እውነትነት በማረጋገጥ እንዳልሆነ ከእኔ ሕይወት ከእኔ ስህተት ልትማሩት ይገባል፡፡ ይህንን ውስጤን ሽብር  የሚለቅብኝ ነገር የምትመግበኝ ሴት ላይ ፍጹም የሆነ እምነቴ ወደቀ፡፡

                የሚገርመው ተቆርቁዋሪዬ አሳቢዬ አድርጌ በእምነት  አይን እመለከታት ነበር፡፡ የህንን ኢንፎርሜሽን ጠንቁዋይ የሚያምን ሰው ሊነግረኝ አይችልም በማለት ሕይወቴ ስለእሱዋ ክፍት ሆነ፡፡ ከዛም አልፎ እከሌም እከሌም ጠንቁዋይ አምላኪ መሆኑን እና የእከሌን የእከሌን ልጅ አሳብደዋል በማለት ሰዎችን በእራሱ አድራሻ በመስጠት እንዳላምናቸው ታደርገኝ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ግን ከቤተክርስቲያን የማይለዩ ሰዎች ነበሩ፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሄር የሚታይባቸው እና ፍጹም በኦርቶዶክስ እምነት ባህል የሚኖሩ መሆናቸውን አየሁ፡፡ የእኔ አለመብሰልን የምታሽከረክረው ሴት ግን ከእነዚህ ሰዎች ፍጹም እንድርቅ የሚያደርግ እንዴት ይህን ያደርጋሉ በሚል ውስጤ እንዲጠላቸው በማድረግ እንድፈርድባቸው በሀጢያት ባህር አሰመጠችኝ፡፡ ከረጅም ግዜ በሁዋላ አገሬ ወጣ ገባ ማለት የጀመርኩት ሴት፤ ኦርቶዶክስ ነኝ ልበል እንጂ ሰይጣን የማይታመን ልፍስፍስ መሆኑን ግን የማቅበት የመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት ብስለት አልነበረኝምእና ከኦርቶዶክስም እንድለይ እየሆንኩ መጣሁ፡፡ በዚህ የተነሳ ጠንቁዋይ ይወዳሉ፤ የሚባሉትን ሰዎች ሁሉ አምርሬ ለመሸሽ ወሰንኩ፡፡ ፈረንጅ አገር ስኖር ይህን አይነት ነገር ሰምቼ ባለማወቄ እና የኖርኩበት ባህል እውነቱን እውነት ሀሰቱን ሀሰት ብሎ የሚናገር በመሆኑ ኢትዮጲያ ተመልሼ ስኖር፤ የሚነግሩኝን ሁሉ የማምን ሆኘ ነበር፡፡ ዛሬ በተቃራኒው እውነቱንም እንዳላምን የሚያደርገኝ ነገር ከአገሬ እንዳካብትኩ እና ለጀርመኖችም አዲስ የማላምን ባህሪ ይዠ እንደተመለስኩ እውን ሆኖአል፡፡  የሰው አገሩ የሰጠኝ የማመን ተሰጥትኦ አገሬ ስገባ ገደል እንዲገባ ያደረገው፤ የሰው ልጅ ምን ያህል በሚያወራው ኢስብአዊነት የለለው የአንድ አገርን ህልውና የሚፈጥር ጠንቁዋይ የሚለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ነበር፡፡

                እኔም የተነገረኝን እንዳምን ያደረገኝ የማይዋሸው በውጭ አገር የነበረው አብሪያቸው ያሳለፍኩት ፈረንጅ ጉዋደኞቼ ባህሪ እና ባህል ነበር፡፡ አንደኛው የእራሴ ውድቀት በእምነት ያለመብሰሌ ጉዳይ የእግዚአብሄርን ሀያልነት እና መቻል ባለመረዳቴ ለጥንቆላ መርበትበቴ ነበር፡፡ ይህን ግን የሚያዝናናቸው አውሪዎች ለእኔ አይምሮ መናጃ የተዘጋጁ እና ሰው እርስ በእርሱ እንዳይተማመን ለመኖር ብርታት እንዳያገኝ የተደረገ መሰሪ ጉዳይ መሆኑን መረዳት ያልቻልኩት እኔ በሽብር መኖሬን ቀጠልኩ፡፡ ሳይውል ሳያድር ግን ቡታንታ/ግልገል ሱሪ አልያም የውስጥ ሱሪ ወይም ፓንት/ ካልስ የካኒተራ በብትብቻው በኩል ሱሪ ሌላም ሌላም እስከአንሶላ ድረስ እየተቆረጠ ማየቴን ቀጠልኩ፡፡ ይህም ሽብሬን ሊያጠብቀው ቻለ፡፡ ነጋሪዎቼንም እውነተኞች ናቸው ማለት ጀመርኩ፡፡ ፈቅሬንም አጠበኩ፡፡ ማን እንደሚቆርጠው ግን ማየት ተሳነኝ፡፡ አካባቢየንም ለመጥላት የምገደድበት እና ምን አይነት ባህል ነው ማለት ጀመርኩ፡፡ ሰው ተወልዶ ካደገበት አገር የትም አይሄድምእና ልቤ በውነት እየተሰበረ፤ እንደእውነቱ እያመመኝም ሄደ፡፡ ፍርሀቴ እንደሚያሳምምኝ እንደሚረብሸኝ ባለማወቄ ጠንቁዋዩ በተቆረጠው ልብሴ ሰርቶአል  ማለት ጀመርኩ፡፡

              በዚህም የተነሳ እግዚአብሄርን ምን አደረኩህ እያልኩ መውቀስንም ተያያዝኩት፡፤ እግዚአብሄር ግን ያደረገኝ ነገር የለም፡፡ ጆሮዬን ለወሬ እና ለመደነጋገር የከፈትኩት እራሴ መሆኔን ዘነጋሁ፡፡ለእኔ እግዚአብሄሬ እንዲደነጋገረኝ የተላኩት ሰዎች ነበሩ፡፡  ለነገሩ ጠንቁዋይን በጠንቁዋይ፤ ደብተራን በደብተራ መምታት ይቻላል ቢባልም እኔ ግን በጭራሽ ወደጠንቁዋይ መንገድ ልመራ አልቻልኩም፡፡ አስቀድሞ አለ ተጠንቀቂ ተብሎ የተነገረኝ  ከአቅም በላይ በሆነው የልብስ ቆረጣ ምክናያት የምይዘውን የምጨብጠውን አሳጣኝ፡፡ ጭንቀቴም ደሜን እየጨመረ ጠቅላላ ትዳሬንም ሆነ ኑሮዬን መበጥበጥ ያዘ፡፡ ከዚያም አልፎ ደሜ እየጨመረ እና መኪናም መንዳት እስከሚያቅተኝ ኑሮዬ በዚህ መልኩ ቀጠለ፡፡

                    ዛሬ ግን አንድ ነገር ተረዳሁ፡፡ ልብሴን የሚቆርጠው ጠንቁዋይ ሳይሆን ወይም ሳትሆን፤  1. ስውር አጀንዳ ያለው፤ አካባቢውን ብሄሩን ስሙን ጠንቁዋይ በማለት ስሙን የሚያስጠፋ፣ ማንነቱን የሚጥል፣ እንዳይታምን የሚያደርግ ፕሮፖጋንዳ ሲሆን፡፡ ከሌላው ማህበረሰብ  ወይም ጎጥ ተለይቶ  እና አንሶ እንዲታይ እንዲሸሽ የሚያደርግ  2. ከእኔ ጋር ብቸኛ ጉዋደኝነትን ከጥቅም አንጻር የፈለገ ወይም የፈለገች ሲሆኑ 3. እነዛም ጠንቁዋይ የተባሉ ሰዎች ደግሞ በአካባቢው እንዳይታመኑ የተደረጉበትንም ምክናያት ስረዳ ፤ ተልካሻ የፖለቲካ ታርጌት እንዳይደመጡ እና እንዲገለሉ፤ የሚያደርግ ሆኖ አገኘሁት፡፡

                        እኔ አዳማጩዋ የሀበሻ ፈረንጅ፤ የተነገረውን የሚያምን ስሆን፤  ነጋሪዎቼ ደግሞ ሰይጣን ያሰማራቸው እና የከፈላቸው ሆድ አደሮች ሆነው አግኝቻለሁ፡፡ ጠንቁዋይንም አስጠንቁዋይኑም በአይምሮ ያስቀመጠልኝ የጥላት ወዳጆች እግዚአብሄር ይሁናቸው፡፡  በአንድ አካባቢ ላይ የሚደረግ ዘመቻ የብዙ ሰዎችን አይምሮ በመበከል እንዳይታመን ይሆናል፡፡ በዚህ የተነሳ በማንኛውም እምነት በመዞር መንፈሳዊ ጥንካሬ ይሰጡኛል የምላቸውነገሮች ሁሉ ስማር ቆየሁ፡፡ እንግዲሕ ያለፉትን 20 አመታት የተዘጋጀልኝ የማይጨበጠው ሽበር ፈጣሪ ጠንቁዋይ ለአይምሮዬ የቤት ስራ ሆኖ ቆይቶአል፡፡ ጥንት ምንም አይነት ነገር ሲወራ የማይሰማበት አካባቢ ለምን ባለፉት ጥቂት አመታቶች ጥንቆላ ደብተራ የሚለው ነገር እንግዲህ እንደገነነ በዚህ ተረዱ፡፡ ሰይጣን የለም ልላችሁ አልችልም፡፡ እርኩስ መንፈስ የለም ልላችሁም አልችልም፡፡ ግና የእኔ መደነጋገር የተፈጠረው ሰው ሰራሽ ድራማ መሆኑን ልታውቁት ይገባል፡፡ ለብሴም የሚቆረጠው ለጥንቆላ ሳይሆን ለሽበር እኔን ለመለየት ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ የእኔን አይምሮ ለመበረዝ እና ከሰዎችም እንድለይ የሚያደርግ በመሆኑ እናንተም ወሬ ስትሰሙ ከምን መነጨ ከምን ተነሳ ብላችሁ አስቡ፡፡ እንግዲሕ የእናንተ የቤት ስራን ይዞላችሁ የመጣው፤ እህት ወንድም፤ ቤተሰብ፤ ጉዋድኛ አልያም ስራ ባልደረባ፤ ፖሊስ ወይስ ሌላ? አንድ ነገር ግን እላችሁዋለሁ፡፡ መልስ ከማታገኙለት የቤት ስራ ውጡ፡፡ ወደፊት መሄድ ካሰባችሁ ማለቴ ነው፡፡ በአይምሮአችሁ በተለያየው ነገር የበረዘውን የቤት ስራ መልስ የለውም እና ለቤት ስራ ሰጪው እንዳለ መልሱለት፡፡ እግዚአብሄር ይርዳን አይናችንን ለመክፈት፡፡ ደብተራ የሚለውን ቃል እንዲጋነን ያደረገው የቤት ስራው ነውእና፡፡ ሁለም ንስሃ ይግባ፡፡ ዛሬ ከዚህ መደነጋገር ውስጥ ወጥቼ ነገሮችን አመዛዝኘ መልስ እንዳገኝ ላደረገኝ ፈጣሪ አምላክ ክብር ምስጋና ይሁን፡፡ ባዩሽ አበበ ነኝ፡፡

Montag, 22. Dezember 2014

የሳተን እንዳንሆን፤ የእምነት ግዴታ እንወጣ




የሳተን እንዳንሆን፤ የእምነት ግዴታ እንወጣ

በጀርመን አገር የስደተኛው ብዛት ያሰጋው ክፍል ከአዲሱ ናዚ ግሩፕ ጋር በመቀላቀል አገራችን ሙስሊም እንዳይሆን ስደተኛው ይውጣልን ማለት እንደያዘ እና እነሱንም የሚቃወም፤ የተማረው የሚያስበው እና ችግራችን የስደተኛ ብዛት አይደለም የሚለው ሰብአዊነት የሚያጠቃው በፊት ለፊት ቆሞ ዘረኛ በማለት ሲቃወማቸው እና ሲበትናቸው ሰንብቶአል፡፡ በዚህም ዘረኝነት መንፈስ፤ ወ/ሮ አንጀላ መርክል ፖለቲካውን በመወከል ዘረኝነት በጭራሽ ዳግም ቦታ የለውም በማለት ሽንጣቸውን ይዘው ሲሙዋገቱ ታይተዋል፡፡ በብዙ ሺህ የሚቆጠርም ፖሊስ በመካከል ቆሞ ለማርገብ ሲሞክር ይታይ ነበር፡፡ ያም ሆነ ይህ አዎ ከሲሪያ ከኢራክ በአጠቃላይ ከአረብ አገር ወደጀርመን የሚፈልሰው ሕዝብም ቀላል አይደለም፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ከኢትዮጲያም ከኤርትራም ከሌላው አፍሪካ በነቂስ ጀርመንን ጥግ እየመረጠ መጥቶአል፡፡ ጭራሽ ኤርትራም እውን ወጣት እዛ አገር ላይ ቀርቶአል ወይ የሚያስብል አካባቢውን ሞልተውታል፡፡ የኤርትራ ወጣቶችም እንኩዋንም ተነፈሱ የሚለው ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ሰው ያዝንላቸዋል፡፡ በጣም ልጆች ናቸው፤ ወጣቶች ናቸው፡፡ ያላቸው ስርአት ደስ የሚል እና ባህሪያቸው ሁሉ የኢትዮጲያን የጥንቱን የመከባበር ስርአት በማየት እራሴ እንድደሰት ሆኛለሁ፡፡ በውነቱ ኤርትራ እና ኢትዮጲያ የአኑዋኑዋር ስርአታችንን አንድ ሆኖ ሳየው  እውን መገነጣጠላችን መልከም ነውን እን ብዬ እራሴን በመጠየቅ አዝናለሁ፡፡ የኤርትራ ወጣት የዘር ነገር ደግሞ የማያወራበት ምክናያት ሳስበው፤ እንዳው አቶ ኢሳያስ አፈወርቄ ቢፈልጉ ኖሮ ይህን ወጣት አንጎሉን በመረዙት እና በጥላቻ ባህሪ በሞሉት እል ነበር፡፡ በኢትዮጲያ ውስጥ በዘረኝነት መንፈስ ጥቂት የማይባለው ሲሙዋገት ሲሰዳደብ ሳይ፤ የኤርትራን ወጣቶች ከዘረኝነት መንፈስ ያወጣቸው ጉዳይ እያደር እየገረመኝ ነው፡፡አቶ  ኢሳያስ አፈወርቄ፤ እሳቸው አምባገነን ቢሆኑም እና ህዝቡ ቢሰደድም፤ በእሳቸው የስልጣን ዘመን የተወለደው ወጣት ግን በኢትዮጲያ ላይ የጥላቻ መንፈስ በጭራሽ የማይታይበት መሆኑ ገርሞኛል፡፡ ይህን ያየሁት በተሰደዱበት አገር በጀርመን ወጣቶቹ ባላቸው ባህሪ ነው፡፡ ኤርትርያን ወጣቶች ወደቤተክርስቲያን ሲሄዱም የኤርትራ የኢትዮጲያ ብለው አይመርጡም፡፡ „ ሀበሻ ነሽ“  ብለው የሚጠይቁኝ በዛ በልጅ አፍ በከርታታ አይን ፍቅራቸውን እንዳይ ሆኜአለሁ፡፡ ፖለቲካ ማንሳት ማውራትም አይፈልጉም፡፡ እጅ እጅ ያላቸው ይመስላል፡፡ አማረኛ ብዙዎቹ አይናገሩም፡፡ ይሁን እና ግን በአጠቃላይ ኢትዮጲያውያኖችን የሚሸሹ ሳይሆኑ የሚቀርቡ መሆናቸውን በማየቴ ልቤ በፍቅራቸው እረክቶአል፡፡ ፍቅርን ቁዋንቁዋ አይገድበውም እና፤ የፍቅር መግለጫው የስብእና መግለጫው ቁዋንቁዋ ሳይሆን እግዚአብሄር የሰጠን ማስተዋል ነው፡፡ በየአጋጣሚው የመንገድ መተላላፊያ መንገድ ላይ አልያም የከተማ ባቡር ላይ ሳገኛቸው  ማዘር ብለው ሲጠሩኝ ልቤ ዘወትር ሲባርካቸው ይሰማኛል፡፡ አዎ መልካም ባህሪ የተላበሱት ወጣቶችም ይህ የስደት አለም እና የማተርያል ውቅያኖስ  ባህሪያቸውን እንዳይበክለው  እና ማንነታቸውን እንዳይወርሰው እመኛለሁ፡፡ የኦርቶዶክስንም ቤተክርስቲያን የሚያጨናንቁት እነሱ መሆናቸውን እሰማለሁ፡፡ በቃ ስደትም ያልቀየራቸው የኤርትራ ወጣቶች እንግዲህ የጅምላ ስደት መሰል ነገር ለኢሮፕ አብቅቶአቸዋል፡፡ እኔም እወዳቸዋለሁ፡፡ ሰው የሚኖረው ከሰው ጋር መሆኑን አውቃለሁ እና፡፡ የዘር ክፍፍልን አጥብቄ የምቃወመው ይህንን ባህሪ ማየት እጅግ አስደስቶኛል፡፡
በስተመጨረሻም ለግንዛቤያችሁ፤ የሰሞኑን የጀርመን ሁኔታ እንዲህ ልንገራችሁ፡፡  በጀርመን ክርስቲያኑ ሕብረተሰብ በተለይ ኢቫንጀሊስ የሚባለው፤ ዘረኝነትን በመቃወም በነቂሥ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሬዲዮ ዜና ዛሬ በጡዋት እንደሰማሁት፤ „እንዚህነ  አሰቃቂ የሆነ የስነልቦና ፈተና የተጋረጠባቸው እና እነሱም ተጠቂ የሆኑት የውጭ አገር ሰዎች አልያም ስደተኞች ላይ መነሳት እና መቃወም ማስደንገጥ ቤተክርስቲያንችን አጥብቃ ትቃወማለች“ ሲሉ ተደምጦአል፡፡  ሙስሊምም ቢሆን ጥግ ፈልጎ የመጣውን መቃወም ኢሰባአዊነት መሆኑን ቤተክርስቲያንም መቃወም ጀምራለች ማለት ነው፡፡  ለነገሩ ስናስበው ክርስቶስ ሀይማኖትን በመጥቀስ ሰውን እንድናሳድድ የሰጠን መመሪያ የለም፡፡ ስለዚህ ዘረኝነት እምነትን የሚወክል ባለመሆኑ፤ አማኝም የክርስቶስ መልእክት ባልሆነው ጥላቻ መሞላት ክርስቲያንነት ሳይሆን ሰይጣናዊ ነው፡፡ ክርስቶስ ፍቅር ነው፡፡ ሁሉንም የተቸገረን የተሰደደን እና ያጣን የራበውን እንድንጠይቅ በደንብ አድርጎ መድሀኒአለም ጠቅሶታል፡፡ ክርስቲያንነት ብዙ መስውአትነት የሚያስከፍል እንጂ አቅጣጫው የሳተውን ሁሉ  የጥላቻውን መንፈስ ተቀብሎ የሚያስተናግድ አለመሆኑን ሁላችንም ልንጋፈጠው የምንችለው ሀቅ ነው፡፡ የሚገሉንም እየማርን ሰማያዊ አለምን እንጠብቃለን እንጂ የጥላቻ መንፈስን ለሆዳችን እና ለእራስ ወዳድነታችን ምቾት ስንል በጥላቻ መንፈስ ተባባሪ መሆን አይገባንም፡፡ አዎ ክርስቶስ እውነት ነው፡፡ ክርስቶስ ፍቅር ነው፡፡ የምንጠብቀውም ከዚሕ አለም ሳይሆን እሱ ካቀደው አለም ነው፡፡ ሊነግረንም የወረደው ይህንን እንጂ አለምን ተስፋችን እንድናደርግ አይደለም፡፡ በአለም ተስፋ የለንም፡፡
ባዩሽ

Samstag, 13. Dezember 2014

„ገረድ“ ሴትን የሚረግጥ ቃል





 „ገረድ“ ሴትን የሚረግጥ ቃል

 አቶ ሀይለማርያም እውጭ በሚኖሩ ኢትዮጲያውያኖችን  የስድብ ትችት አቀረቡባቸው ተብሎ  በኢሳት ዜና የተዘገበውን ሰማሁ፡፡ የተላለፈው እውነት ነውን? እውን ከሆነ ያሳዝናል፡፡ ይገርማል፡፡ ከሆነ ብዬ የምናገረው ከአንድ የአገር መሪ ግራ በተጋቡ ወጣቶች ላይ ይህ አይነት ንግግር አሳፋሪ ነውእና ነው፡፡ አቶ መለስ ቢሳደቡም ወዝ ቀብተው ነው የሚሉ እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ግን አቶ ሀይለማርያም የደረቀ እና ለዛው የተሙዋጠጠ ሆነብኝ፡፡ እንዳውም የኢሕአዴግን መውደቅ የሚፈልጉ መሪ ሊሆኑ ይችላሉ የሚልም ጥርጣሬ ያዘኝ፡፡ ምክናያቱም የበለጠ እንዲጠላ የሚያደርግ የቃላት አወራወር ሆኖ ስላገኘሁት ነው፡፡ ለምን ቢሉ ፖለቲካ ሲሉ፤ ቃላትን ቆሞ የሚጠብቅ አለእና ነው፡፡  የመናገር ችሎታ በፖለቲካ አልም የሚጀምረው ማንኛውንም የሰው ልጅ በማክበር እንጂ በመዝለፍ አይደለም፡፡   ሰው የሚባል፣ በሚሰራው የስራ አይነት እና ልብስ መሰደብ መተቸት የለበትም፡፡ ይህ ስብእና ግብረገብነት የሚያስተምረን ትምህርት ነው፡፡ እኔ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበርኩበት በዛን ዘመን፤ ግብረገብ እንደ አንድ የትምህርት ክፍል የሚሰጥ ነበር እና፤ ሰው „ገረድ“ የሚል ለስራ ስም  እንዳንሰጥ ሁለተኛ ክፍል ያስተማሩኝ ትዝ ብሎኝ ነው፡፡  የሚችለውን እና ያገኘውን ሰርቶ ቤተሰብን ማስተዳደር አንዱ መብት ነው፡፡ ለዛውም  በኢትዮጲያ ለ90% ወጣት ስራ የለለበት አገር፡፡ ስራ አገኝ ብሎ ወጣቱ የአባቱን ቤትና ንብርት እያሲያዘ ለመነገድ፤ ተጨማሪ ትምህርት ለማግኘት እና እውድድሩ አለም ለመግባት ለኮሌጅ ከፍሎ በመማር ደግሞም ለውጭ አገር ደላላ/ አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ/ በመክፈል ወንዝን እሻገራለሁ ብሎ ለአዞ ለሚሰጠው ባለጀልባ በመክፈል ሕይወትና እና ኑሮ አስገድዶት፤ ኑሮ ግራ ያጋባውእና የሚራወጥ መሆኑን የኢትዮጲያ መንግስት ያውቀዋል፡፡ አቶ መለስ ቢሆኑ እንኩዋንም ስራ አገኘልኝ ይሉ ነበር የሚል ግምት አለኝ፡፡ ምክንያቱም እዛ ሆኖ ጉሮሮአቸው ላይ እንዲቆም አይፈልጉም እና፤ በብልጥነት ተጉዘዋል፡፡  ታዲያ ኢትዮጲያ ቢቀመጥ ወጣቱ ምን ያገኛል ነው የእኔ ጥያቄ፡፡ ምንአልባት ኢትዮጲያም ገንዘብ እና ስራ የሞላቸው ሰዎች አገርም እየለቀቁ እየወጡ ብናይም ይህም ቢሆን በአገራቸው ለመኖር ዋስትና ያሳጣቸውን ነገር መርምሮ መድረስ ተገቢ ነው፡፡ እነሱም እዚህ መጥተው ኮሌጅ ሳይሆን ስደተኛ ሆነው እጃቸውን ይሰጣሉ እና፡፡ ደግሞም በሌላ መልኩ፤ ከኢትዮጲያ የሚወጣው ሰው የቸገረው  እና ግራ የተጋባውም ወጣት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጲያን ትምህርት የናቀ ቤተሰብ ባበጠ የኢትዮጲያ ብር ለማስተማር ልጁን ወደአሜሪካ እና ኢይሮፕ የሚልክም እንዳለ በአፍሪካ ታሪክ ይታወቃል፡፡ አንድ ነገር እግረመንገዴን ልበል፡፡ የኢትዮጲያ ፖለቲከኞች እውን በኢትዮጲያ ትምህርቱን አሻሽለን ጥሩ አድርገነዋል ካሉ ለምንስ በውድ ገንዘብ ልጆቻቸውን ለማስተማር ወደውጭ ይልካሉ ነው የብዙዎች ጥያቄ፡፡

        ስደት ዛሬ የመንግስትን ሸክም ማቅለያ እና ከቶም ለኢሕአዴግ መገልገያ የፕሮፖጋንዳ ማሽን እንደሆነ ብዙዎች ይተቻሉ፡፡ ኢሕአዴግን የሚወደውም እጅግ ብዙ ስደተኛ እንዳለ እና ምንም አይነት የተቃዋሚ ነገር ላይ የማይገኝ እንዳለ ሆድ ያውቃል፡፡ እንግዲህ እነሱን መንካት መሆኑን ያልገባቸው አቶ ሐይለማርያም የማይመች ስብእናን የሚነካ ቃል ማውጣታቸውን እየሰማን ነው፡፡ኢሕአዴግንም ደግፈህ ግባ አልያም የእውነት የፖለቲካ ችግር ይኑርህ ስደተኛው ገረድ ከተባለ እና ዱቄት በሌታ ከሆነ ሁሉም ነው፡፡ ኢሕአዴግንም ደግፎ የመጣ እንደእውነቱ እውጭ አገር ላለው ለሰው አገሩ መንግሰት ምንም ከጤፍ የሚቆጠር አይደለም፡፡ እንዳውም ይህ ቢታወቅ ምን ልትፈልግ ታዲያ ስደተኛ ሆንክ ይመጣል፡፡ ስደተኛ ማለት ያለውን ገዢ ፓርቲ የጠላ፤ የተጣላ ማለት ነው፡፡  አቶ ሀይለማርያም ማወቅ የነበረባቸው ሁሉም እድሉን አግኝቶ በኢትዮጲያ ፊደል እንኩዋን ያልቆጠረ እንዳለ እና ይህም ክፍል ሰርቶ የመብላት መብት እንዳለው የተረዱ አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጲያ መደሰቻነትዋ  ከመካከለኛው መደብ በላይ ለሆነው ስለሆነ፤  „ገረድ“ መሰል ቁዋንቁዋ እና ሰው በሚበላው ተንቆ መነገሩ መልክትነቱ 70% በላይ የሆነውን ህዝብ በንቀት መታየቱን የሚገልጽ ነው፡፡ አሁንም የሰብአዊነት ክብሩ እየተገፈፈ የሚሄደው የታችኛው ክፍል እንደዛው እንደነበረ እና እንዳለ እየተሸጋገረ የሚሄድ ግፍ መሆኑ በእራሱ በአቶሀይለማርያም ከባዱን ቃላት ቀለል አድርጎ ማውጣት አለመቸገራቸውን ያስረዳል፡፡

 ለመሆኑ ዛሬ ዩንቨርሲቲም ጨርሱ የተባሉት በየትም ክልል ተገረዱም ዱቄትም በሉ በየትኛውም አለም ተበትነው፤ የእለት ኑሮአቸውን መግፋት ይዘዋል፡፡ የተማረውንም የስራ ቦታ እንደለለውእና ያለችውም ትንሹዋ ስራ ቦታ የሚያገኛት ማን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሙስና እና አድሎ በተስፋፋበት አገር ይህ የሚጠፋው አለ ብዬ አልገምትም፡፡ ውጭ የወጣ ሰው  ከእለት ጉርሱ አልፎ ኢትዮጲያ ያለውን ቤተሰብ በመርዳት አንቱ ያስባለው ቁጥሩ ቀላል አይደለም፡፡ ታዲያ የአንድ ፓርቲ የበላይነትን የሚያስተናግደው የኢትዮጲያን መንግሰት በውጭ የሚኖረውን ሰው ያቃለለ መሆኑን ልብ ያውቀዋል፡፡ ይህ እንዳው ስድብ ምሁሩንም ሆነ ወይም ያልተማረውን የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ስደተኛውን ስብእና የሚነካ ነው፡፡ አቶ ሓይለማርያም የተናገሩት እውን ከሆነ የውጩንም መንግስት የሚነካ ይሆናል፡፡ በተለይ በጀርመን አገር ለስደተኛው ደፋ ቀና የሚል ብዙ ሰብአዊ መብት ተሙዋጋች ስላለ አቶ ሃይለማርያምን የት ነው ዶቄት የሚበላው ብለው እንዲነግሩዋቸው ይጠይቁ ነበር፡፡ እውነት ያዩት ትክክል  ከሆነም፤ አቶ ሀይለማርያም የሕንን እይታ ለዘለፋእና ለፖለቲካ ፍጆታ ባልተጠቀሙበት ነበር፡፡ ምክናያቱም ለወጣቱ በኢትዮጲያ የሚያቀርቡለት ነገር አንዳችም የለም፡፡ እንዳውም ወጣቱን ለማሳደግ ቀርቶ፤ ጥቂት ያሳደጉዋቸው ምርጦቻቸው  ጋር እንዲወዳደር እና እንዲቀናና የማድረግ የመከፋፈል ተጽእኖ በኢሕአዴግ ዘመን ይታያል፡፡ አንዱን የሚረባ አንዱን ደግሞ የማይረባ አድርጎ የሚያቀርብ የፖሎቲካ አካሄድ የት እንደሚያደርስ ባናውቀውም ግን ኢሰብአዊነት መሆኑን የምናቀው ሀቅ ነው፡፡
ያልተማረም ገረድ የተባለችውም ሴት በአገሩዋ እኩል መብት ያላት መሆኑን ማወቅ ያልተረዱ የሚመስሉት አቶ ሀይለማርያም፤ በሕዝብ መካከል አዲስ መደብ እየፈጠሩ መሆኑን እያየን ነው፡፡ ይህ በእጅጉ የሴትን ስብእና የሚነካ ሁዋላ ቀር አነጋገር በውጭ አገር ያለው የሴቶች መብት ሊያስብበት እና ሊነጋገርበት የሚገባ ነው፡፡ በአገራችን  ሴት የቤተሰብ ሃላፊነትን ወስዳ በኑሮው ውድነት በተጨናነቀችበት ጊዜ ፣ያገኘችውን ስራ አግኝታ ሃላፊነቱዋን ለመወጣት ወደማታውቀው አገር በደመነፍስ በምትጉዋዝበት ግዜ እና ለሞት ለአስገድዶ መደፈር በተሰጠችበት ግዜ ስነልቦናዋን የሚገነባላት „ገረድ“ መባል ከሆነ ሁላችንም ልናፍርበት ይገባል፡፡ ከቶም ይህ ቃል ከኢትዮጲያ መጥፋት ያለበት እንጂ በመሪ በመዝናናት በማሾፍ የሚነገር መሆን ባለተገባው ነበር፡፡ ይህ የሚያሳየን ተናዳጅ ባህሪንፖለቲከኞች እየተላበሱ መምጣታቸውን ነው፡፡  እንኩዋን እሳቸው ተናገሩ የተባሉት ይቅር እና እኔ ለእራሴ ልሰማሁትም ከብዶኛል፡፡ ስርአት ካለው ቤታስብ ከወጣን ይህንን መልካም እንዳልሆነ እናውቃለንእና፡፡ ዛሬ ጌታ የሆነ ነገ ገረድ የማይባልበትም ምንም አይነት የሕየይወት ዋስትና እግዚአብሄር አልሰጠንም፡፡ ነግ በእኔ ማለት መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር ባህርን አቁሞ ከተማን ባህር ያደርጋል እና፤ ልብ ማለት መልካም ነው፡፡ ሮምም አንድ ወቅት የአለም ታላቅ ነበረች እና፡፡ በቸር የምላችሁ ባዩሽ ነኝ