Freitag, 21. November 2014

የአሮጊት ልጅአገረድ ፤ ሴቶች እና አካላቸው





አይድነቃችሁ፡፡ አለም የማን ጡት ይብለጥ ከሚለው ተነስቶ የማን ቂጥ ይበልጣል የሚለው ደረጃ ለያ ደርሶአል፡፡ በተፈጥሮ ትልቅ ቂጥ ያለው የታደለ ነው ለማለት ይቻላል፤ ስንቱ ቂጡ ላይ ሌላ ስጋ እየለጠፈ ወይም ሴሊኮን እየተወጋ ለማተለቅ ሲጥር ስናይ፤ ምነው ጌታ ሆይ ሰውን እንደወደድከው ሳይሆን እንደወደዱት ብትፈጥረው ለማለት ያስደፍራል፡፡  ብቻ ጥቂት የአለም ሴቶች እንጂ ብዙሃኑ የአለም ሴት ስላልሆነ መረጋጋት ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ይህንን ቴማ ያነሳሁት ትንሽ ሌሎች ነገሮችን በእሱ አካባቢ ያሉትን የአመለካከት ልዩነቶች ለመጥቀስ ፈልጌ ነው፡፡ በዚህ ውበት በሚለው መልኩ ሁሉም ፈረንጅ አንድአይነት አመለካካት ያለው እንዳይመስላችሁ፤ አንዳንድ ነገሮችን ጠቆም ላድርጋችሁ ፈልጌ ነው፡፡ ይህ የሚጠቅማችሁ ፈረንጆች አልያም ሴቶች እንዲህ ናቸው ብላችሁ ሀጢያት በሚያስገባው በጅምላ ፍርድ/Judgment/እንዳትጠመዱ ነው፡፡ ጅምላ መፍረድ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሚያስገባ ሁሉ፡፡ ጅምላ መፍረድ ሴቶች፣ ፈረንጆች፣ ጥቁሮች፣ ሙስሊሞች እና  ክርስቲያኖች የሚለውም እልም ያለ ሀጢያት ያስገባል፡፡ ምክናያቱም እኛ ዳኛ አይደለንም እና፡፡ ዳኛው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ አትግደል አትፍረድ…. ካለ የሚያደርገውን እሱ ያውቃል፡፡ ለነገሩ ሴት እርቃኑዋን ብትሄድ አካሉዋን በፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ብትለዋውጥ እኔን አይመለከተኝም፡፡ ዲሞክራሲ ማለት ሰው እንደፈለገው ይሁን፤ ሌላውን ግን እንደእኔ ሁን ማለት የለበትም ይመስላል፡፡ ሎጥ ብቻውን እስከሚቀር ድረስ አለምን ንቆ አሳለፈ እንጂ ውጊያውን የተዋጋው እራሱ እግዚአብሄር መሆኑን ያስረዳል፡፡ ለምሳሌ ሎጥ ልግደል ቢል ከእነዛ ከጠፉ ሰዎች መካከል አንድ ወይም ሁለት ብቻ አቅሙ ሊፈቅድ ይችላል፡፡ አቅም ለውጊያ ሊኖረው አይችልም፡፡ ሁሉም ጠፍተው ቀሪው እሱ ብቻ ነበር እና፡፡  የሚጠፋውን ግን የሚያውቅ እግዚአብሄር እንጂ እኔ ላውቅ አልችልም፡፡ የእራሴንም መዳን ለማወቅ ይከብዳል፡፡ ማመን ብቻ መዳን የሚመጣው በማመን ውስጥ ያሉትን ነገሮች ስትፈጽም ነው፡፡ ከባድ ፈተና፡፡ መጥገብም ሀጢያት ነውእና፡፡  ሰው የገዛ ገላውን እንደፈለገ ቢያደርግ የጠፍተዋል ማለት ያለብኝ ፍርድን ለመፍረድ እኔ ማንነኝ፡፡ ሰው በሕይወት እግዚአብሄር እንዲኖር ከፈቀደለት፤ የንስሃ ግዜም እየሰጠው መሆኑን እናውቃለንእና፡፡ በዚህ አለም ላይ መኖራችን ለንስሃ ብቻ እንጂ ከዚህ ያለፈ ሆኖ ለማግኘት ተቸግሬአለሁ፡፡ ሌላ አይደለም፤ ሞትን በእያንዳንዱ ፊት ተገትሮ ሲጠብቀው ስለማይ ነው፡፡ እኔንም ጨምሮ፡፡
         በዚህም የተነሳ ፍርድ እንዴት ሰውን ገደል እንደሚከት በአቅሜ ልተነትንላችሁ ወደድኩ፡፡ ይህን ስል ግን ሁሉን አውቄ ሳይሆን በአካባቢዬ የተመለከትኩትን እይታዎች ነው፡፡ አንዳንዶች ሰዎች ሰውነታቸውን እንደፈለጉ ሲቀዳደዱት እና እንደፍላጎታቸው ሲቀያይሩት እናያለን፡፡  አልያም እግዚአብሄር በሰጣቸው ውበትም በአደባባይ እርቃን አድርገው ሲወጡ ከማየት የቦዘነ የለም፡፡ ይህም ሁሉን ማስደሰት ቀርቶ  የፌዝ ሳቅ የሚስቁ፤ የሚተቹ ፤ ወይ ማበድ የሚሉ ቀላል ቁጥር አይደሉም፡፡  አንዳንዶች ደግሞ ምንም አይምሮዋ ውስጥ የለላት ናት ይህንን የምታደርግ ብለው እንደ ድንቁርና እና አይምሮዋ ያልሰለጠነ  በማለት በንቀት ችላ ይሉታል፡፡ የሚገርመው በሾው በማንኛውም በሚዲያም እየቀረቡ የሚሙዋገቱ ሴቶች ቀላል አይባሉም፡፡ በታረመ ቆዳም ቁንጅና የለም ብለው የሚነቅፉም ውበት አድናቂዎች አልጠፉም፡፡  ዛሬ ቆንጆ የሚባለው በብዛት በታረመ ፣በተቀደደ፣ በተለጠፈ፣ በተነፋ፣ አርቲፊሻል እና ሴሊኮን በመወጋት መንገድ እየሆነ መጥቶአል፡፡ ይህም ደግሞ „ጤነኛ መንገድ  ነው፤ በገዛ ገላዬ እንደፈለኩ ብሆን ምን አገባህ“ ብለው ሽንጣቸውን ይዘው የሚሙዋገቱ እና፤ „ለቀዶ ጥገናው ገንዘብ ባገኝ አሁኑኑ አደርገዋለሁ“ ብለው የስነልቦና መካሪዎች ላይ የሚያፈጡ አሉ፡፡ አንዳንዶች በገንዘብ እጦት የጠሉትን የሰውነት ክፍል ማስተካከል ያልቻሉም በዲፕሬሽን /በድብርት/ የሚሰቃዩ ቀላል አይደሉም፡፡ እረጅም አፍንጫ እንደእኔ ያለው ደግሞ  የሚጠላው ሞልቶአል፡፡ ተመስገን እላለሁ የእኔን ጌታ እንድወደው ስላደረገኝ እንጂ ብጠላው እኔም ለመተልተል እዘጋጅ እንደሁ ማን ያውቃል፡፡ ጥላቻ አይምሮን ያስታል እና፡፡   አጭር አፍንጫም ደግሞ የሚጠላ ሞልቶአል፡፡ በቃ የፈረደበት ሀኪም  ጥበቡን ተክኖ ካሸሩን ከፍቶ ካራውን ስሎ ቁጭ ብሎ ኮረዳዎችን በማስደሰት ተያይዞታል፡፡ በጠሉት የሰውነት አቀማመጥ ስነልቦናቸው የታመመም ከቀዶ ጥገናው በሁዋላ ይድናሉ፡፡ ብቻ ቀዶ ጥገናው ድንገት ጠማማ ነገር ካላመጣ፡፡ ብዙ ግዜ ከጀርመን ውጭ እርካሽ ስለሆነ ሄደው የሚስተካከሉ ሳካም ይዘው የሚመለሱ እና ተመላልጠው ተጋግጠው ካለፈው ጌታ ከሰጣቸው የጠሉት መልክ የባሰ የሚያሳብድ የሚያስደብቅ ጦጣን ማሪኝ የሚል መልክ ይዘው የሚያርፉም በሚዲያ በስሞታ የሚደረደሩ እያየን ነው፡፡ ሁልግዜ የመረጥከው መንገድ እንቅፋት የለውም ማለት ዘበት ነው፡፡ አንዳንዶች ጀርመንም ቢሆን ቀዶ ጥገናው ሊሰናከል እና በድግግሞሽ ካራ ሊያስከትል ይችላል፡፡ አይጣል ነው፡፡ ለማንኛውም ከፍተኛ ገቢ ያለው የሀኪም ክፍል፤ መልክ እና ቁመና ከሚያስተካክሉ ጥበበኛ ሀኪሞች ጋር ሆኖአል፡፡
 ሴቶች ይህን ማድረግ የሚገደዱበት ምክናያት ተመልካች በመኖሩ እና የውጩ አለም ውበትን ማየት ስለሚፈልግ ነው፡፡  ዛሬ አለም ውበት ለእይታ ብቻ የሚፈለግበት ዘመን ሆኖአል፡፡ ምግብ ቤትም ዴኩሬሽኑን እንጂ የምግብ ጣእሙ የጠፋበት ሳይሆን እንዳልቀረ ነው፡፡ ሁሉም ለውበት ሰፍ ያለ መስሎ የታየው የጥቂት ሴቶች የተሳሳተ አመለካከት የእራሳቸውን ሰውነት እንደ ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል ዴኩሬት አድርገው አስውበው ለአለም እይታ ገባያ ብቅ ይላሉ፡፡እውነትም ብዙ የተሳካላቸው ሴቶች እንዲህ ተስተካክለው የመጡም ናቸው፡፡ የበለጠ ለመለወጥም“ በገባያው እና በውድድሩ አለም ለማደግም፤  ከጀመሩ ጀምረው አባርተው አያውቁም፡፡ ከጀመሩ ጀምሮ እስከእለተ ሞት የሚቀጥል ፕሮሰስ  ነው፡፡ ሁልግዜ መስተካከል፡፡   ችግሩ ገንዘብ ብቻ የሆነባቸው አሉ እንጂ፡፡ ሌላዋ ፍላጎት ያለት የፊተኛዋ  ስትላላጥ እና ስትታመም አይሆኑ መልክ ይዛ ስትሰቃይ  እያዩ እርም የሚሉት ብዙም አይደሉም፡፡ ውበት የስራ መፍጠሪያ እንጂ የመደነቂያ መሆኑ ቀርቶአል፡፡ አንተ ሬስቶራንትም ሆነ ሌላ ነገር ለመስራት/ሰርቶ ለማደር/ ብዙ ነገር ኢንቬስት ታደርጋለሕ፡፡ ዛሬ እንግዲሕ የስራ ቦታ በተጣበበበት ወቅት ብዙ ሴቶች ሰውነታቸው ላይ ኢንቬስት በማድረግ ዳጎስ ያለ ብር ለማግኘት የሚያስገድዳቸው ውድድር ፍላጎት ነገር ተፈጥሮአል፡፡አንዳንዶች በእውነት በድህነት የተነሳ ብር ፍለጋ ሲሆን ሌሎች ግን እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ የሚለው ውድድር ሆኖአል፡፡  ወዳጄ የማን ቂጥ ይበልጣል፤ አለም የሰውን ልጅ ማጃጃል ይዛለች፡፡ ባለቂጡ እንዲታይ ብቻ ሳይሆን ፤ተመልካቹም ለማየት ኢንቬስት ያደርጋል፡፡
       ግና በላጩ ፈረንጅ ይህን አይነት አርቲፊሻል ጉዞ የማይቀበሉ ሲሆን፤ እኔን ካልነካኝ እንደፈለገች ብለው ጆሮ እና አይንን ሸፍነው የሚኖረው የበለጠው ቁጥር ነው፡፡  እኔም እንደዛ ልሁን የሚሉ አይደሉም፡፡ እንኩዋን መሆን ማየት የሚያስጠላቸው እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ እንኩዋን ሰውነታቸውን ተለጣጥፈው እራሳቸውን የሚያታልሉ  ሊሆኑ ቀርቶ በተፈጥሮም እግዚአብሄር የሰጣቸውን ውብ ሰውነት ቢለመኑም ከፍተኛ ገንዘብ እንከፍልሻለኝ ቢባሉም እርም እራቁት አደባባይ የሚሉ ሞልተዋል፡፡ ሁሉም የሞራል ጉዳይ ነውእና ሁሉም እንደሞራሉ ይጉዋዝ፤ እራቁቱንም የሄደ ልብስም የለበሰ አይመለከተንም ነው የሚለው የዲሞክራሲው አለም ሰው፡፡ ምንአገባኝ ሰላሜን የማደፈርስ፤ የተቃወምከው መልሶ ይቃወማሃል እና ነው ነገሩ፡፡ ፕላስቲክ ቀዶ ጥገናም አስፈላጊ የሆነበት ነገር የማንክደው ሀቅ፤ በእሳት ቃጠሎሰ አልያም በሆነ ጤና ጉድለትእና  በአደጋ አንድ አካላቸው የተጎዳ ሀኪሞች ትብብር በማድረግ ደግሞም የጤና ኢንሹራንስ ከፍሎ የሚስተካክልላቸው ነገር አለ፡፡ ግና ሰውነቱዋን ለማወዳደር ቅደዱኝ የምትል ኪሱዋ ዳጎስ ያለ መሆን አለበት፡፡ መከልከል ግን ማንም አይከለክልም ለአቅመ አዳም ካልደረሰች በስተቀር፡፡ ሰሞኑን አንዲት ተዋቂ ሴት ያበጠ ቂጡዋን ለማሳየት ብቅ ብላ ነበር፡፡ ብዙ ሚሊዬን ህዝብ አይቶታል፡፡ ግና ብዙውም የተተቸችበት መፈጠሩዋን እንዴት አያስጠላትም፤ እንዴትስ ቻለችው ያስብላል፡፡ ብዙዎችም ምንአልባት ልጁዋ አድጋ ትምህርት ቤት ስትሄድ የተማሪዎችን ትችት ትችል ይሆንን? በማለት፤ ጋዜጠኞች የልጁዋን ሞራል ያላስተዋለች ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ በነገራችን ላይ እንደእኔም ቆዳቸው ጨምደድ ያለ ያስነፉታል፤ ጡታቸውንም ብድግ ያስደርጉታል፡፡ እኔ የአሮጊት ልጅአገረድ እላቸዋለሁ፡፡ ለወጣቱ ስፍራ አለቅም ያሉ ይመስላሉ፡፡ አያድርስ ነው፡፡ ወይ ገንዘብ፡፡ እንዳው ሰዎች የተሰጣችሁን አካል ካልወደዳችሁ አይድርስ በሽታ ማለት እሱ ነው፡፡ ባዩሽ ነኝ