የጋሊሊያው እየሱስ እምነትም ባይኖራቸው በሰቆቃ ለሚያልፉ ሁሉ ይቆማል
እየሱስ የእውነት አገልጋይ እንጂ የሃሰት አገልጋይ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ ለሕዝብ ከሚቆሙ ጋር አጋዥ
ይሆናል፡፡ ለተራበው፣ ፍርድ በመጉዋደል ለተጨናነቀው ፣ የቲሞች እና ፍርድ በመጉዋደል ከሚሰደዱ ጋር እንደሚሆን አውቃለሁ፡፡ እመሰክራለሁ፡፡ እግዚአብሄር ግሩፕ የማይፈልግ
ማሃበራዊ ስብሰባን የማይፈልግ ታላቅ እና ሀያል፤ አንድን ሰውን እንኩዋን ብቻውን የማይጥል አምላክ ነው እንኩዋንስ የፈጠረውን ሕዝብ፡፡
ይህንም አምናለሁ እመሰክራለሁ፡፡ እየሱስ ሙስሊም ክርስቲያን፤ ሴት ወንድ ሳይል ሀብታም ደሃ ሳይል፤ ለሁሉም በእውነት እና በመንፈስ
ይፈርዳል፡፡ እየሱስ በዚህ አለም ሳለን ማንንም ሰው እንድናገላታ እንድናሰቃይ ሰቆቃ እንድናደርግበት አይፈልግም፡፡ እየሱስ እሩህሩህ
መሆኑን እንወቅ፡፡ ለምሳሌ እየሱስ በቀራጩ ቤት ተገኝቶአል ደግሞም በተጣሉት በተገለሉት ሕብረተሰብ ጋር ተገኝቶአል፡፡ እየሱስ እምነታቸውን
አይቶ ሳይሆን፤ ሰቆቃቸውን በማየት እዛ ቦታ ተገኝቶአል፡፡ ስለዚህ አማኝ ቤት ብቻ ነው የሚገኘው የሚለውን እኔ አላምንበትም፡፡
ይህ ሁሉ የሚስረዳን እግዚአብሄር የፈጠረውን ሰው ሁሉ ሰቆቃውን አይፈልገውም፡፡ እደግመዋለሁ እግዚአብሄር ሆደ ቡቡ አምላክ ነው፡፡
በአለም ሳለን ሁሉም የሰው ልጅ የእግዚአብሄርን የሰቆቃ ማቅለያ መቻያ ጉልበት እና ሀይል ይሰጠዋል፡፡ ይህ መረጃችን ከብዙ አሰቃቂ
ሰቆቃ ተርፈው ለምስክርነት ሲበቁ እና ክፉ ሰዎች ላይ ሲያስፈርዱ እግዚአብሄር ያሳየናል፡፡ ሰውን እራሱ ይቅጣ እንጂ አንተ ማን
ነህእና ትቀጣለሕ ያለ ይመስላል፡፡ በዚህም የተነሳ የማምነው ሙስሊም ሁን ክርስቲያን የምታምን ሁን የማታምን በምታልፍበት የሰቆቃ
መንገድ እግዚአብሄር መቻልን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር እሩህሩህ እንጂ ጨካኝ አይደለም፡፡ በተፈጥሮ ማንም ሰው ሲሰቃይ አይኑ ወደሰማይ
እንደሚያይ ልብ ብላችሁ አስተውሉ፡፡ ሲሞት እንኩዋን ጥቁሩዋ የምናይባት አይን ወደላይ ሻጥ ትላለች፡፡ ወደላይ፡፡ በስቃይ ወደላይ
በመጨረሻው ወደላይ ሁላችንም እናያለኝ እና፤ አለምን የፈጠረው አንድ ፈጣሪ ለማንም አያዳላም፡፡ እየሱስ ንስሃ ገብተው ራሳቸውን ከሚያስተካክሉ ጋር ይቆማል ብዬ አምናለሁ፡፡
ልብ በል እየሱስ በእየሩሳሌም ታላለቅ ሀብታሞች እና መባ ተቀባዮች ጋር አላሳለፈም፡፡ ይልቅስ እሱ የተገኘው በእየሩሳሌም ባለሀብቶች
በእምነት መሪዎች ተገለው ተንቀው የተጣሉት ሕመምተኞች ደሃዎች በሚገኙበት ጋሊልያ በሚባል ስፍራ ነው፡፡ ለዚህ ነው ሰው ሲለምን
የጋሊሊያው እየሱስ ብሎ የሚለምነው፡፡ እኔም የምለምነው እሱን የጋሊሊያውን እየሱስ ነው፡፡ ሌላው ዮሀንስ መጥመቁ የቤተመንግስትን
ሚስጥር ስለተናገረ በሴት ውበት፣ ሰውነት እና ጭፈራ ህሊናው ለተሰለበው አመንዝራ ንጉስ ቤተሰብ ጉቦ ተሰጥቶ አንገቱን በሰይፍ መታረዱን እመን፡፡ የእግዚአብሄር
ምህረት እና ቅጣት ሁልግዜ በቤተመንግስት ውስጥ እና በታላለቅ የሄማኖት መሪዎች ወይም በባለሀብቶች አካባቢ ሲገለጥ የተደጋገመ ነገር
እናያለን፡፡ ስለዚህ ለእምነት ቅርብ ነኝ ለቤተምንግስት ቅርብ ነኝ
ብለሕ ወዳጄ ሆይ እንደልብህ አትሁን፡፡ እሱ ያለውን የፍርድ መመዘኛውን አታውቅም እና፤ በሀያማኖቱ ወይም በፖለቲካው አቁዋም የሰውን
ልጅ መዝነህ ለማጥፋት አትአቸኩል፡፡ ሁሉም ነብዮችም ሆኑ እራሱ ታላቁ እየሱስ ጌታችን እና መድሀኒታችን በመካከላችን ተገኝተው ያሳዩን እውነትን እንጂ አድሎ እና ፍርደገምድልነትን ወይም ሰዎችን ተናዳጅ የሚያደርግ
ንግግርን አይደለም፡፡ ሰውን የበለጠ ጉዋደኛ ገንዘብ እንዳለሕ እና ለመንግስታቶች ቅርብ ሆነሕ እንደፈለክ መሆን ሌላውን ለቅናት
እና ለቁጣ የሚጋብዝ በመሆኑ ሀጢያተኛ ነሕ፡፡ ልብ በል ወዳጄ ሆይ፤ ቀናተኛው ብቻ ሳይሆን፤ አንተ አስቀኝውም የሐጢያት አነሳሽ
ክብሪት ትሆናለህ እና አስተውል፡፡ የፈጣሪ ታምራቶች ተመስክረው እና ተጠንተው የቀረቡልን ከመሆን አልፎ፤ ዛሬም የእሱን መኖር ቆመን
ለመመስከር ብዙ ታአምራቶችን ያየን እና የሰማን ብዙዎች ነን፡፡
ስለዚህ ሰው በፈለገው ሀይማኖት ይጉዋዝ፤ በፈለገው የፖለቲካ ሪዮተ አለም፡፡ እኛ ግን ማንንም ወደሰቆቃ ማስገባት ከእግዚአብሄር
ይለፍ አልተሰጠንም፡፡ እግዚአብሄር ቢፈልግ የማይፈልገውን በአንድ ሰከንድ ማጥፋት የሚችል ጥበበኛ ፈጣሪ በመሆኑ እሱ ላደረገውን
አንተ ማነሕ እና በፍርድ ትጠመዳለሕ፡፡ ይህ አለም አላፊ ነው፡፡ ያንን እንኩዋን ማየት ባትችል አንተ ግን አላፊ መሆንህን ድባቅ
የሚከትህን አፈር ውስጥ የሚቀላቅልህን ሞት አስብ፡፡ እንግዲሕ
ጌታ ከተበዳይ ከተገፋ እንጂ ከገፊ ጋር አይሆንም እና ማንኛውንም እንቅስቃሴ
ልብ በል፡፡ እኔ ባሪያ ነኝ፤ ነጻነቴንም የማገኘው እናንተን ሁላችሁን በማፍቀር እንጂ በማሰቃየት አይደለም፡፡ ሁሉም ቆዳው እና
ጸጉሩን ቢላጭ ሰው አንድ አይነት የሆነ ሰው ነው፡፡ ሰውነትህን ለማወቅ፤ የግድ ቆዳህን እና ጸጉርህን መላጨት አለብንን?? በሰቆቃ
የመጣ እግዚአብሄር የሁሉም ወኪል ነው፡፡ ሰላም ይብዛላችሁ፡፡
ባዩሽ